Friday, March 29, 2013

ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪካ የኢሕአዴግን ስብሰባ በተኑ፤ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተደብቀው አመለጡ

images(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ ሮዝባንክ ከተማ የተጠራው የኢሕ አዴግ ሥብሰባ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ትግል መቋረጡንና መበተኑን የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘገበ። በልማት ስም የተጠራውና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተጠራው ይኸው ስብሰባ የስር ዓቱ ደጋፊ የሆኑ ከ20 የማይበልጡ ሰዎች ቢገኙም ስብሰባው ይደረግበት የነበረውን ሃያት ሆቴል የስር ዓቱ ተቃዋሚዎች በመሙላት ስብሰባው እንዳይደረግ አድርገዋል።
የድምጻችን ይሰማ፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና ደጋፊዎች በአንድነት የኢሕ አዴግን ስብሰባ እንዳይደረግ በማድረግ
- ከልማት በፊት የሕዝብ ነፃነት ይቅደም
- በቅድሚያ መገደብ ያለበት ወንዝ ሳይሆን የ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ነው በሚል ሕዝቡ ጩኸቱን በማሰማቱ ስብሰባው ተቋርጦ ደጋፊው ሕዝቡ ጥቃት ያደርስባቸዋል በሚል ፍራቻ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ደብቆ ከአዳራሹ አስመልጧል።
የኢሕአዴግ ስብሰባ እንዳይደረግ ያስተጓጎሉት ኢትዮጵያውያን ኢሕ አዴግ በከፈለበት የሃያት ሆቴል አድራሽ ስብሰባ በማድረግ በቀጣይ በአንድነት ስለሚያደርጉት የጋራ ትግል ዙሪያ መነጋገራቸውን፤ የተዘጋጀውን ውሃ እና መጠጥም የኛ ገንዘብ ነው በሚል እንደጠጡት የዘገበው የዘሐበሻ ሪፖርተር የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሃያት ሆቴል ስብሰባው ከተስተጓጎለበት በኋላ ደጋፊዎቹን በኢምባሲው ውስጥ መሰብሰቡ ታውቋል። ከኢትዮጵያ ኢምባሲ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከሮዝባንክ ከተማም ኢትዮጵያውያን ወደ ኢምባሲው በመሄድ ተቃውሟቸውን እንዳሰሙም ሪፖርተራችን ጨምሮ ዘገቧል።

ኢትዮጵያን ከወያኔ ስርዓት የማላቀቂያ ጊዜው አሁን ነው (ገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

  march 29/2013 

ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ

ወያኔ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን በሀይል መግዛት ሕዝብን በአፈናና በእንግልት ማሰቃየት ከጀመረ ሀያ ሁለተኛ ዓመቱን ለማክበር ባለበት በዚይ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጀ እያመራ እንዳለ የሕዝቡም የኖሩ አቀጣጫ እንደተለወጠ አፉን ሞልቶ ሲናገር እንስመዋለን ወያኔ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስረዘመ ይህንን ይበል እንጂ ሀቁ ግን ይህ አይደለም :: በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ አለም ዓቀፍ ጥናቶች እና ሐሀዞች እንደሚያሳዩት ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ሁለት አስር ዓመታቶች በአገሪቷ ላይ አስከፊ ድህነት እንደሰፈነ ፣ የስራ አጥ ቁጥር እንዳሻቀበ እና ፣ ሰበዓዊ እና ፣ ዲሞክራሳዊ መብቶች ክብር አልባ ሆነው ፣ የገአሪቷ ዜጕች የኖሮ ደረጃ ከቀነ ወደ ቀን እንዳሽቆለቆለ ነው::

      ወያኔ ኢሕአዴግ በሀገሪቷ ላይ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደል ይለፍልፍ እንጂ አሁንም እየታየ ያለው ሀቁ ግን እንደሚያሳየው በአገሪቷ ላይ የአንድ ብሔር  የበላይነት ብቻ የሚነጸባረቀበት መሪዎች የፖለቲካ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማካበቻ የሚጠቀሙበት ዘረኛ እና ጨቆኝ ስርዓት የነገሰባት ሀገር አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነች ነው :: ይህንንም ብልሹ እና አስከፊ ስርዓት የሚቃወሙ እና የሚተቹ ሰዎች በማን አለብኝነት በወያኔ የግፍ በትር በየእስር ቤቱ በስቃይ መከራ እየተንገላቱ እንደሚገኙ እና አብዛኛውም የአገሪቱ ሕዝቦች የተበላሸው የወያኔ ስርዓት በፈጠረው የኑሮም ሆነ የፖለቲካ ጫና በመሸሽ አገራቸውን ትተው ለስደት እና ለመከራ ሲዳረጉ አብዛኞቹም ያሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደዋዛ አልፉል :: መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን በብዛት አገሪቷን እየተወ ባገኘው አጋጣሚ ወደተለያዩ አገሮች ከሚሰደድበት አገር ተርታ እንደምትመደብ እና ወያኔ አገሪቱን ወደተሻለ የእድገት ደረጃ እየመራ እንዳለ ይናገር እንንጂ አገሪቷ ግን ከታች ካሉ የደሃ አገሮች ግንባር ቀደም እንደሆነች እና አገሪቷ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እያመራች እንዳለ ነው የሚያመለክተው::

         የዜጎች የመብት ረገጣ ፣ አፈና ፣ስቃይ ከመቼውም በላቀ ጊዜ ላይ ይገኛል:: ሀገሪቷም በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ ናት:: ለዚህም ነው የኢትዮጵያ ፊዲራላዊ አነድነት መድረክ መጋቢት 17 ቀን 2005 የሀገሪቱን ጊዚያዊ ሁኔታ አስመልከቷ በሰጠው ጋዚጣዊ መግለጫ ላይ አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች ያለው::

   አሁን ላይ እንደሚታየው የአገሪቷ ተጨባጭ ሁኔታ በጣም አስከፊ እና አሳሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነው :: ለተቀዋሚ የፖለቲካ ድርጅቷች ደግሞ ጥሩ መነሳሳት የሚሆን አጋጣሚ እና በወያኔ መንግስት ላይ ስር ነቀል ርምጃ ለመውሰድ የሚነሳሱበት ወቅት ነው :: በርግጥ በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ኢሕአዴግ መካከል አይለኛ የሆነ የእርስ በእርስ ሽኩቻ እና እርስ በእርስ የመናናቅ ፣ ያለመከባባር እና የመከፋፈል ትርምስ እንዳለ ለከፍተኛ ባለስልጣን ሳይቀር በድርጅቶ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ አሳሳቤ እንደሆነባቸው ምንጮች ገልጸዋል:: ይህ ሁሉ የሚያሳየው የወያኔ ኢሕአዴግ የስልጣን ዘመን እየተፍረከረከ መምጣቱን ነው :: በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ካድሪዎች ተደናግጠዋል ምን እየሰሩ እንዳለ እንኮን አንደማያቁ ነው ::  ሰሞኑን በባሕር ዳር በተካኤደው ዘጠነኛው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ ያየነው ይህንኑ ነው::


     የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ባለቤት አዜብ መስፍን ባለቤታቸው ያገኘው ሰለነበረው የወር ደሞዝ ስትናገር በጣም አሳፋሪ እና ሴትየዋንም ለትዝብት የሚዳርጋት ንግግር ነበር የተናገረቸው :: አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች እንደሚሉት ሴትየዋ ይህን ንግግር ልትናገር የቻለችበት ምክንያት ወደ ስልጣን እየመጡ ያሉትን አዳዲስ የኢሕአዴግ ሰዎችን ሸንቆጥ ለማድረግ የተጠቀሙበት ፕሮፑጋንዳ እንደሆነ ይናገራሉ:: በርግጥ ሲትዮዋ  ይህን ስትናገር በጉባኤው ላይ የተሰበሰብትም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግሮን ምን ያክል ውሸት እንደሆነ እንደሚያቁው ታውቀዋለች ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመረጃ ያልራቀ ሕዝብ ነውና:: ነግር ግን የአዜብ መስፍን ንግግር ኢሕአዴግ ባለስልጣኖች ምን ያክል በስጋት እና በድንጋጤ ውስጥ እየኖሩ እንዳለ አመላካች ነው :: በአሁኑ ሰዓት በማን አለብኝነት በኢሕአዴግ ውስጥ ትልቁን የፖለቲካ ሚና እየተጫወተ ያለው ህወሓት ሳይቀር ከወትሮው ጊዜ በተለየ መልኩ በታላቅ ክፍፍል እና ሽኩቻ ውስጥ እንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች እየጠቀሱ ባሉበት በእዚህ ወቅት የተጠናከረ እና የተደራጀ የፖለቲካ እና የሰው ኃይል ቢኖር ኢትዮጵያን ከወያኔ ስርዓት የማላቀቂያ ጊዜው አሁን እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ የተመነበት ሀቅ ነው ለዚህም ሁሉም የወያኔ ተቃዋሜ ድርጅቶች በአንድነት መነሳት ያለባቸው :: ሕዝቡም ለሁለት አስር ዓመታት በወያኔ የግፍ እና የጭቆና ስርዓት ውስጥ የኖረበት ጊዜ በቃኝ በማለት ለነጻነቱ እና ለዲሞክራሳዊ መብቱ መከበር ሲለ በወያኔ ስርዓት ላይ የተቃውሞ ድምጹን ማሰማት ይጠበቅበታል::

በቃ !!!



   ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ





  

Meles was a poor man who had no bank account - Azeb Mesfin

By Addis Fortune        
Editor's Note - Azeb Mesfin, the widow of Meles Zenawi, said her husband's net salary was 4,000 Birr a month, too little money that he had no need for a bank account. Azeb was mad that such an important fact was missing from the minds of those who write flawless tributes in honor of her late husband. Eulogy writers should heed her advice before she gets hold of them: First, she is a member of the powerful TPLF politburo; second, if money is power, Azeb is uber-rich, perched like an eagle's nest atop the mountain of gold called "EFFORT."
Delegates of the ninth convention of the ruling EPRDF party have shown their dissatisfaction over a eulogy written for their late leader, Meles Zenawi, while some were critical of the quality of its writing and completeness of the content.
Translated from Tigrigna, the eulogy was first presented to the congress of the TPLF, held in Meqelle two weeks ago, before it was presented to over 1,000 delegates at the conclusion of the ruling coalition's convention on Tuesday, held in Bahir Dar.
The first to voice such disappointment over the organisation of the eulogy and its content structure was Meles's widow. Elected to the political bureau of the TPLF for the second time and to the all too powerful Executive Committee of the EPRDF, Azeb Mesfin was displeased to see the eulogy incomplete.
Some of the points she argued as missed are Meles's place, role and the contributions he made as an Editor-in-Chief of the party's ideological organ, Addis Ra'ey. Azeb feels that the contributions Meles had made in originating the idea of forming a training facility for the rank and file, now directed by Addisu Legesse, and the manual he develop ought to be forcefully underlined.
Azeb defended her late husband's legacy in relations to how he had handled the conflict and the subsequent war with Eritrea. Despite condemnations from his political opponents due to his heritage, Azeb told delegates that Meles had never negotiated on the national interests of Ethiopia.
"Not even for a second," Azeb told delegates rather emphatically.
Azeb described Meles's conduct during the war with Eritrea in the late 1990s as "extraordinary" in not showing what he had felt of the accusations, but focused on defending his beliefs and political positions regardless.
She recalled her late husband as perhaps the only leader who had earned a little over 4,000 Br a month in net salary, but fought poverty with courage and resolve, while remaining selfless.
"Meles didn't have a bank account," Azeb said. "He had neither an ID card nor a driving licence."
These parts, Azeb argued, were not given their proper place in the eulogy, which was read by Hailemariam Desalegn, re-elected to chair the EPRDF twice since the death of Meles in August 2012.
Hailemariam's re-election was fait accompli, although he was made to pass the test of contest to the office. His deputy, Demeke Mekonnen of ANDM, and Alemayehu Atomsa of OPDO, were nominated by their respective parties for the chairmanship, while leaders of the TPLF have declined to nominate their leaders, Fortune learnt.
Hailemariam has won the chairmanship with a landslide, after bagging 176 votes of the 180 Council members of the ruling party, sources in the Council disclosed to Fortune.
Although the other two contenders have received two votes each against Hailemariam, Demeke too claimed the deputy chairmanship position with significant margin, claiming 146 votes against 25 given to his contender, Fortune learnt.
Emerging as uncontested non-combatant leader of the Revolutionary Democrats since the party's formation in the late 1980s, Hailemariam was seen endorsing the conciliatory proposition made by Addisu, who remains one of the 13 political bureau members of the ANDM but left out from the EPRDF's Executive Committee.
Addisu has argued that the eulogy is filled with repetition, is not well organised, and suffers from losses in translation, while its structure is weak. Addisu urged delegates to let the EPRDF's Executive Committee rewrite the eulogy before it gets adopted as the party's official document, a proposition Hailemariam had secured its adoption by the Congress unanimously.

Thursday, March 28, 2013

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው

ፍኖተ ነጻነት
የኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?
ግራዚያኒ በመርዝ ጋዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፏል፤ ከየካቲት 12 ጀምሮ ለቀናት በዘለቀው የበቀል ጭፍጨፋም በአካፋ ሳይቀር በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በግፍ ጨፍጭፏል፡፡ ግራዚያኒ በወቅቱ በሰጠው ትዕዛዝ የፋሺስት ወታደሮች ህይወት ያለውን ተንቀሳቃሽ ፍጥረትን ሁሉ ገድለዋል፡፡ ይህ እሩቅ በማይባል ጊዜ የተፈፀመ ድርጊት ነው፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለእንዲህ አይነቱ ጨፍጫፊ የተገነባን ሀውልት ለመቃወም በወጡ ዜጎች ላይ የወሰዱት የእስር ተግባር እውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው? አስብሎናል፡፡ ኢህአዴግ በስልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በተደጋጋሚ ጥፋት ፈፅሟል፡፡ ሀገራችንን የባህር በር ማሳጣትን ጨምሮ ሀገራዊ ስሜትን አንኳሶ ጠባብ የብሔር ስሜት እንዲንሰራፋ አድርጓል፣ ታሪክን ለስልጣኑ መደላድል ሲል በራሱ መንገድ የሚያዘጋጀው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያን ጠፍጥፎ እንደሰራት ሁሉ ደርግን ለመጣል ካደረገው ትግል ውጪ ያለውን የአርበኞች ተጋድሎ እውቅና ሲሰጥ አይታይም፡፡
መንግስት ለፋሽስቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተገነባውን ሀውልት በመቃወም የወሰደው እርምጃ አለመኖሩ ሳያንስ ግራዚያኒን ለማውገዝ የወጡ ዜጎችን በመደብደብና በማንገላታት ማሰሩ አሳፍሮናል፡፡ ለዜጎቻቸው እና ለሚመሯት ሀገር ክብር የማይሰጡ ይልቁንም የጦር ወንጀለኛና ፋሺስትን ለመቃወም የወጣን ዜጋ ማሰርራቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ወገንተኝነታቸው ለዜጎቻቸው ነው ወይስ ለፋሺስት? የሚል ዘግናኝ ጥያቄ እንድንሰነዝር ያስገድደናል፡፡
በሰልፉ ላይ የተገኙት ሀገር ወዳድ ዜጎች በማን አለብኝነት ሲታሰሩ ድባደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የታሳሪዎቹን የኢሜይልና የማህበራዊ ገፅ የይለፍ ቃል (password) በግዳጅ የሚቀበሉ የደህንነት ሀይሎች ተልከውባቸዋል፡፡ ይህን ቅጥ ያጣ አንባገነናዊ ድርጊት የፈፀመው ወይም እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጠው አካል ማንነት ተጣርቶ የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ በየምክንያቱ ዜጎችን ማሰር የለመደው አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ምን ያክል ኢትዮጵያዊነትን እየተዋጋ እንዳለም የሚያሳይ ድርጊት ነው፡፡ መሰረቱ ዜጎች በማንኛውም ጉዳይ ላይ የተቃውሞም ሆነ የድጋፍ ሰልፍ ማድረግ እንደሚችሉ ህገመንግስቱ ደንግጓል፡፡ ይህን መብት ዜጎች እንዳይጠቀሙ ያፈነው መንግስት፣ ኢህአዴግን የሚደግፉ አልያም በራሱ ከተጠሩ ሰልፎች ውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ በአሰራር ከልክሏል፡፡ ይህ የመብት ረገጣ ከመሆኑም በላይ በዜጎች መካከል 1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ዜግነትን ያስቀመጠ ነው፡፡
የኢህአዴግን ባናውቅም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዢዎች የተዋረደ ስነልቦና የለንም፡፡ ሆኖም የግል ጥቅማቸውን ለማደላደል ሲሉ ለቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ያደሩ ባንዳዎች እንደነበሩ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ ሸክፎታል፡፡ ይህን አሳፋሪ ተግባር በጣሊያን ወረራ ወቅት የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስተላልፉት አንገት ቀና የሚያደርግ ታሪክ አይኖርም፡፡
በዚህም ዘመን ተመሳሳይ ክህደት የሚፈፅሙ አካላት መኖራቸው አይጠረጠርም፡፡
የኢህአዴግ መንግስት በይፋ ለጦር ወንጀለኛውና ለፋሺሽቱ ሩዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን ሀውልት በይፋ ካለማውገዝ ባለፈ ለተቃውሞ የወጡትን ኢትዮጵያውያን በግፍ የማሰሩን ምክንያት ስንመረምር አንድ መራራ እውነት እንረዳለን፤ ይኸውም ጣሊያን ለኢህአዴግ መንግስት ዋንኛዋ ለጋሽ ሀገር መሆኗ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ መንግስት ተግባር በስልጣን ዘመኑ በኢትዮጵያዊነት ላይ ከፈፀማቸው ክህደቶች እኩል በታሪክ ጥቁር መዝገብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

The Pain of the Ogaden People

“Every night, they took all of us girls to [interrogations]. They would separate us and beat us. The second time they took me, they raped me… All three of the men raped me, consecutively”.
Human Rights Watch (HRW) report in Collective Punishment, along with 15 other female students, this innocent 17 year-old Ogaden girl, was held captive for three months in a “dark hole in the ground” and raped 13 times. This is just one of countless accounts of abuse, from within the Ogaden region of Ethiopia, where it is widely reported criminal acts like these are perpetrated by the Ethiopian military and paramilitary forces on a daily basis. Untold atrocities like this; past and present are awaiting investigation, amid what is a much-ignored, little known conflict in the Horn of Africa.
In an attempt to hide the facts from the rest of the world, in 2007 the Ethiopian government banned all international media, and expelled many humanitarian aid groups from the area. It is reputed that any Non-Governmental Organisations (NGO’s) allowed to stay do so on the condition that they sign a waiver document, agreeing not to report human rights violations by the government. Ethiopia, Leslie Lefkow of HRW states, “is one of the most difficult places to work for human rights groups or humanitarian agencies on the African continent”, and the Ogaden (a barren land, littered with military remnants from past conflicts), “is one of the most difficult places to work in Ethiopia.” There are “huge challenges to doing investigations on the ground because the security apparatus of the government is extremely extensive and permeates even the lowest levels, the grass roots, the village levels”, where regime spies and informers operate, reporting anything and anyone suspicious.
Information about life within the region comes from whispering sources on the ground, and from those who have fled the violence, and are now living outside Ethiopia. Many are in refugee camps in Kenya and Yemen, from where they recount stories of horrific abuse. Mohammed, from the Dhadhaab (or Dadaab) camp in Kenya, described to Ogaden Online (OO) 1/12/2012 how he was captured by the Ethiopian military, accused of being a supporter of the Ogaden National Liberation Front (ONLF) and mercilessly tortured. “They hogtied me”, he said, “and then flogged me while pinned down.” Mohamed’s face “was disfigured to the point where he can’t be recognized”. Refugees support Amnesty International’s (AI) findings of “torture and extrajudicial executions of detainees in the region” – women tell of multiple gang rapes, their arms, feet and necks tied with wire, for which they bear the scars, men speak of barbaric torture techniques at the hands of the Ethiopian military and paramilitary – the notorious, semi legal, completely barbaric Liyu Police, who, Laetitia Bader of HRW says, “fit into this context of impunity where security forces can do more or less what they want”.
The ONLF is cast as the enemy of the state, and regarded, as all dissenting troublesome groups are, as terrorists. They in fact won 60% of seats and were democratically elected to the regional parliament in the only inclusive open elections to be held, back in 1992. Civilians suspected, however vaguely of supporting the so-called ‘rebels’, are forcibly re-located from their homes. The evacuated villages and settlements, emptied at gunpoint HRW (CP) record, “become no-go areas” and in a further act of state criminality, “civilians who remain behind risk being shot on sight, tortured, or raped if spotted by soldiers”. Children, refugees report are hanged, villages and settlements razed to the ground and cattle stolen to feed soldiers: HRW record (CP), “water sources and wells have [also] been destroyed”. Systematic, strategic methods of violence and intimidation employed by the Ethiopian regime, that has, Genocide Watch (GW) state, “initiated a genocidal campaign against the Ogaden Somali population”.
Pervasive pernicious control
Spearheading the Governments campaign of terror in the region is the Liyu Police. A force of 10,000-14,000 18-20 year olds, with little or no knowledge of criminal law or human Rights, David Mepham UK Director of HRW told The Guardian 15/01/2013, that “for years we have documented egregious human rights abuses committed by the Liyu police, including the March 2012 extra-judicial execution of 10 men in their custody and the killing of nine other villagers”. Established in 2005 the Liyu initiative was the brainchild of a group led by the current regional President. His Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) regime was and remains, at war with the ONLF, who are seeking self-determination for the five million ethnic Somali’s, in line with their constitutional rights under the governments Ethnic Federalism policy.
The EPRDF is a highly controlling repressive regime, which has extended its pervasive reach in the nine districts of the Ogaden, to where, HRW (CP) records, “security committees, which exist at every administrative level [and]… include members of the armed forces, military intelligence, security officials.” The local Ogaden administration “does nothing but carry out Ethiopian dictates and represents the interests of the present, centralised regime,” the Ogaden Women’s Relief Association (OWRA) record in their study, A Place to Call Home. Dictates’ of government brutality and intimidation regimentally carried out by the Ethiopian military apparatus, fully equipped by their principle donor, America, who GW recommend, should “immediately cease all military assistance”.
Terrifying tools of oppression and imprisonment
The current regime operates under the premiership of Hailemariam Desalegn, who, true to his inaugural word, is following in predecessor Meles Zenawi’s shoes – has expanded the EPRDF’s repertoire of violence and control and, in addition to the range of violent measures employed, is imposing additional economic pressures, intimidation and extortion the name of the game. It is widely reported that In the midst of the current dry (or Jilaal) season, new taxes are being levied on water drawn from wells for livestock and domestic use. Sums of up to $150 are reportedly being charged to people living in rural areas, already burdened by an economic and aid embargo, which is causing civilians great hardship.
Additional tax demands are also being made – OO (8/03/2013) carry the story that, “reliable reports…. confirm the imposition of what the locals term an illegal ‘head tax’, imposed on the civilian population as well as on their livestock”. A local elder, whose “family consists of eight children and he and his wife” received an arbitrary charge of “150 Ethiopian Birrs ($8) per individual regardless of age or gender”, a total of 1200 birr ($56) – far beyond his means.
Kidnapping, with subsequent ransom demands, is another applied tool of terror. Family members, abducted and imprisoned, are released upon receipt of ransom payments, made either by relatives inside Ethiopia or those living overseas. Levels of extortion vary, with those in the west paying anything from “$300 to $1,500”; the McGill Report found “in some cases those amounts were contributions to total collected ransoms of more than $10,000”. This criminal practice is widespread: civilians are arrested and imprisoned, without regard to due process, often repeatedly as Ifraah, a 25 year-old Ogaden Somali woman, told the OWRA: “To be released, you have to pay the Ethiopian military from 1,000 ($56) to 2,000 birr ($112). And the price keeps going up. If they suspect that the family has money, they raise the price. Poor people often stay in prison much longer because they can’t raise the ransom. It happened to me twice. The first time I wasn’t yet married. I spent a couple of months in prison and had to pay 500 birr ($28); the second time, I had to pay 1,000.” It’s a business in human suffering, “arrests also benefit the military; it’s a flourishing trade. Innocent people are captured and have to come up with a lot of money to free themselves.” This illegal income, it is widely believed, is being used to supplement the paramilitary soldiers salaries’. “There are women thrown into prison five times, and each time they have to pay to get out. But economic factors are not the only ones. There’s also torture and rape”.
Civilians like Ifraah indiscriminately accused of supporting the ONLF are detained without charge. Leslie Lefkow of HRW makes clear that, “the way the EPRDF targets people, is an enormous problem from a human rights point of view”. HRW have been monitoring the situation in the region for the past five years, and have seen and documented a range of Human Rights abuses, including “arbitrary detaining [of] family members, often for long periods of time, sexual violence against women and girls, sometimes if they are viewed as being members of the ONLF or supporters or simply because they are family members [of ONLF supporters]. There is a kind of ‘guilt by association’ that is used to target the family members”, punishable by “summary executions… where suspected ONLF supporters have been executed in cold blood.”
Incarcerated in what are often makeshift prisons (e.g. deserted school buildings), prisoners held in appalling conditions, are tortured, abused and intimidated. Ina and Halima, two young women from the town of Saga, were, OO 21/01/2011 report, “suspended in the air by their ankles with their legs spread wide, while the soldiers poured water mixed with red chilli powder over them [and] applied [it] in and around the victims’ genitalia, causing severe burns.” In ‘prison’ there are no medical facilities and, Ifraah says, no food: “You get your food from relatives. If you don’t have anyone nearby, your relatives send money to people who live there so they can buy you food”; or inmates share what little they have. Abdullahi, held amongst, others without trial for nine months, related to OWRA how their captors “locked us in an underground room” Young girls are regarded as Liyu property, kidnapped, held captive and repeatedly raped, often falling pregnant in the process. “Little girls”, record OWRA, “13 to 15-year-olds, in prison and suddenly pregnant….at night you hear the girls screaming when soldiers take them from their cells” – their dignity and childhood stolen from them.
Government genocide
The government’s so-called counter-insurgency policy in the Ogaden is, in truth, a form of genocide and is regarded as such by GW. Is it ethnic hatred, fear and loathing of the ‘other’, or simply greed for the regions natural resources – the oil and natural gas that drives the government’s violent, multi-pronged approach? An approach that HRW (CP) makes clear, aims “at cutting off economic resources, weakening the ONLF’s civilian support base, and confining its geographic area of operation”. In pursuing these duplicitous goals, the Ethiopian regime seems to exist on an island of impunity, hidden from the international community; as The Unrepresented Nations and Peoples Organization (UNPO) state, “there is a shocking lack of international attention directed at the situation” and, despite the “substantial documentation of the violations committed…published by human rights NGOs, governments and media outlets”, nothing is being done.
Let us be clear and state, unequivocally the findings of Human Rights groups: that the Ethiopian military and paramilitary is committing wide-ranging Human Rights violations in the Ogaden, which constitute war crimes and crimes against humanity. “The situation” should, as GW demand, be “referred by the UN Security Council to the International Criminal Court (ICC)”.
Such Human Rights violations are not confined to the Ogaden region. GW consider “Ethiopia to have already reached Stage 7 (of 8), genocide massacres, against many of its peoples, including the Anuak, Ogadeni, Oromo, and Omo tribes”. The EPRDF, unsurprisingly, plead innocent to all such accusations of abuse and state criminality and dismiss allegations of human rights abuse substantiated by reports from international human rights group such as Human Rights Watch and Amnesty International. The Ogaden regional president claims, they “peddle lies and propaganda from our enemies”. However, if the Ethiopian government has nothing to hide, why don’t they allow independent investigators and journalists access to the Ogaden region?
The shocking accounts of violence and abuse are endless. The situation is clearly extremely critical and demands the immediate attention of Ethiopia’s main benefactors – America and sister donor nations, the European Union and Britain. To continue to ignore the evidence of state criminality and to blindly support the Ethiopian government in the face of such persecution, is to be complicit in the murder and violent abuse of the innocent people of the Ogaden region.
Graham Peebles is director of the Create Trust. He can be reached at: graham@thecreatetrust.org

ሰበር ዜና "ባለስልጣናት በሃብት የተንበሸበሹ ናቸው::" የሙስና ኮሚሽን ሰራተኞች

byMINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ)



በወያኔው የባህር ዳር ስብሰባ ላይ ወይዘሮ አዜብ መስፍን የባለቤቴ ደሞዝ 6000 ብር ሲሆን ተቆራርጦ የሚደርሰው 4000 ብር ነው በማለት መለክቱ በውል ያልታወቀ ምናልባት ራሳቸውን ከሙስና እናትነት ለማውረድ እና መጪው ተተኪ የወያኔ ትውልድ ተጠያቂ እንዳያደርጋቸው ለማስፈራራት የተጠቀሙበት ብልሃትይሁን አይታወቅም ሆኖም በአለም አቀፍ ደረጃ የሙስና እናት ተብለው የሚታወቁት ወይዘሮ ተናገሩ ...የሚሰማ የለም::
ይህ እኮ የኢትዮጵያ ሃብት ብቻ አይደለም በእርዳታ በብድር እንዲሁም በተለያዩ ቢዝነሶች የሚገኙ ገንዘቦች ናቸው :: ከብሄራዊ ባንክ እጅ በእጅ የተዘረፉ አይደሉም::
የሙስና ኮሚሽን ጥናት እና ምዝገባ ግን የሚለው ከእሳቸው የተለየ ነው ያንብቡት::

ባለፉት 21 አመታት የከበሩ ባለስልጣናት ስም ዝርዝር ከሙስና ኮሚሽን ምዝገባ ክፍል
የውስጥ አዋቂ ምንጮች ባደረሱን ዘገባ መሰረት እንደሚከተለው ይቀርባል::
ይህ በውጭ አገር የተቀመጠ እና በሃገር ውስጥ በተለያዩ መንገዶች የተመዘገቡ አካውንቶች
እና ንብረቶች ዝርዝር ግምት ያካተተ ሲሆን በቤተስቦቻቸው ስም የተመዘገቡ ማናቸውንም
ነገር አይጨምርም::
-ሟች አቶ መለስ ዜናዊ ..... 4.5ቢሊዮን ዶላር
-ወ/ሮ አዘብ መስፍን....... 4.1 ቢልዮን ዶላር
-አቶ ስብሃት ነጋ .........3.8 ቢልዮን ዶላር
-ሳሞራ የኑስ............3.6 ቢሊዮን ዶላር
-ባጫ ደበሌ...........3.4 ቢሊዮን ዶላር
-ስዩም መስፍን...........3.3 ቢሊዮን ዶላር
-አባዱላ ገመዳ..........3.33 ቢሊዮን ዶላር
-በረከት ስምኦን........3.22 ቢሊዮን ዶላር
-አቶ አባይ ጸሀዬ.......2።9 ቢሊዮን ዶላር
-ካሱ ኢላላ...........2.8 ቢልዮን ዶላር
-ብርሃነ ገብረክርስቶስ......2.8 ቢልዮን ዶላር
-አርከበ እቁባይ.........2.4 ቢልዮን ዶላር
-ጂነዲን ሳዶ.........2.34 ቢሊዮን ዶላር
-ግርማ ብሩ..........2.0 ቢሊዮን ዶላር
-አባይ ወልዱ-ወ/ሮ ትርፉ ኪ/ማ...2.0 ቢሊዮን ዶላር
-ሰሎሞን እንቋይ.......1.8ቢሊዮን ዶላር
-ታደስ ሃይሌ..........1.8 ቢልዮን ዶላር
-ዶ\ቴዎድሮስ ሃጎስ.......1.8 ቢሊዮን ዶላር
-አቶ አዲሱ ለገሰ.......1.8 ቢልዮን ዶላር
-አቶ ንዋይ ገብረአብ... 1.2 ቢሊዮን ዶላር
-አቶ ኩማ ደመቅሳ.....1 ቢሊዮ ዶላር
-አቶ ደመቀ መኮንን....800 ሚሊዮን ዶላር
- አቶ ድሪባ ኩማ.....600 ሚሊዮን ዶላር
-አቶ ሬድዋን ሁሴን.....580 ሚሊዮን ዶላር
- አቶ ሽፈራው ሽጉጤ....400 ሚሊዮን ዶላር
-ዶ/ደብረጺሆን ገ/ሚ.....240 ሚሊዮን ዶላር
-አቶ አባዲ ዘሙ........200 ሚሊዮን ዶላር
-አቶ ወርቅነህ ገበየሁ......150 ሚሊዮን ዶላር
ይቀጥላል...
ዝርዝሩ የሚቀጥል ሲሆን በሚቀጥለው ጹሁፍ ባለስልጣናት ከነጋዴዎች ጋር ተሻርከው እየሰሩ
ስላለው ቢዝነስ ሰፊ ዘገባ ይዘን እናቀርባለን::ይከታተሉን::

ጋዜጠኛ እስክንድርና አቶ አንዱለአም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና አቶ አንዱአለም አራጌን ፍርድ ቤት ሳያቀርብ ቀርቷል። የፍርድ ቤቱ ፖሊስ ለእስር ቤቱ ሀላፊዎች ደብዳቤ ማድረሷን ገልጻለች።
የፌደራል ጠ/ፍርድ ቤት በ አቶ አንዱ አለም አራጌ የክስ መዝገብ በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ወንጀል የተፈረደባቸውን የ አንድነት ፓርቲ ም/ል ሊ/መንበር እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አንዱአለም አራጌ ፣ የአንድነት አመራር አባል ናትናኤል መኮንን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የቀድሞው የፓርላማ ተማራጭ አቶ አንዱአለም አያሌው ፣ የመኢዴፓ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ ፣ አቶ ዮናስ ተረፈ፣ እና ሻምበል የሽዋስ ይሁን አለም የይግባኝ አቤቱታ በአግባቡ አለመመርመሩን ገልጿል።
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ለማድመጥ የተከሳሽ ቤተሰቦች ፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች እና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በርካታ ወጣቶች የተገኙ ቢሆንም ፣ ዳኛው አቃቢ ህጉንና የተከሳሽ ጠበቆችን ጠርተው በማነጋገር ጥቂት ጋዜጠኞች ብቻ ችሎቱን መታዘብ እንዲችሉ አድርገዋል።
በእለቱ ችሎት የተሰየሙት ዳኛ አቶ ዳኘ መላኩ ብቻ የነበሩ ሲሆን የእስረኞች ጠበቃ አቶ ደርበው ተመስገን ፣ አቶ አበበ ጉታ እና የመንግስት ጠበቃ አቶ ሳሙኤል አባተም ተገኝተዋል። ዳኛው ዳኘ መላኩም ለጠበቆች “እናንተ ምንም የምታምኑት ነገር የለም፣ አቃቢ ህግ ያለምንም የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ክስ ስላቀረበ ብቻ ነው የተፈረደባቸው ፣ እኛ በ አግባቡ ተከላክለን እያለ ነው የተፈረደባቸው ስላላችሁ መዝገቡን በአግባቡ ሀ ብለን እየመረመርን ነው፣ በዚህም ላይ የፌደራል ፍርድ ቤት መዝገቡን አዘግይቶ ነው የላከልን ስለዚህ ለእናንተም በአግባቡ ቢመረመር ጥሩ ነው” በማለት ተናግረው፣ እስር ቤቱ እስረኞችን ለምን እንዳላቀረባቸው የእስር ቤቱን ፖሊስ አዛዥም እንጠይቃለን ብለዋል።
አንዲት ፖሊስ ቀርባ ” እኔ የማቅረቢያ የጥሪ ወረቀቱን ለማረሚያ ቤቱ ጸሀፊዎች በአግባቡ ሰጥቻለሁ ለምን እንዲቀርቡ እንዳላደረጉ አልገባኝም፣ ወረቀቱ አልደረሰንም በማለት ሸምጥጠው ክደዋል፣ በማረሚያ ቤቱ እንዲህ አይነት መካካድ ያለ ነው ” በማለት ተናግራ ፣ ዛሬ የመጣሁት ተለዋጭ ጊዜ ቀጠሮ ለመውሰድ ነው ብላለች።
ፍርድቤቱም ተከሳሾች ባልቀረቡበት ችሎት ለመጋቢት 30 ቀን 2005 ዓም የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ችሎቱ ከተበተነ በሁዋላ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ፖሊሶች እነ አቶ ናትናኤል መኮንንን፣ አንዱአልም አያሌውን፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበን ፣ አቶ ዮሐንስ ተረፈንና፣ ሻምበል የሽዋስ ይሁን አለምን ይዘው የመጡ ሲሆን፣ ቢሆንም ወዲያው መልሰው ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና አቶ አንዱአለም አራጌን ግን ማረሚያ ቤቱ ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው ቀርቷል።
ጠበቆች ለኢሳት እንደገለጡት እስረኞች ምንም አይነት የሽብርተኝነት ወንጀል ያልሰሩ መሆናቸው እየታወቀ መንግስት ስለከሰሳቸው ብቻ ወንጀለኞች ተብለው በግፍ ለእስር ተዳርገዋል።

Wednesday, March 27, 2013

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ


የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።
ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በዘረኝነት ገመድ አስሮ እየረገጠ የሚገዛዉ ወያኔ ለዚህ የበቃዉ በዘረኝነትና በጥላቻ አነሳስቶ ያሰታጠቃቸዉ ገበሬዎች በከፈሉት መስዋዕትነት ነዉ ያለዉ ይሄዉ ህዝባዊ ኃይል ሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከእነዚህ የቀን ጅቦች ለማላቀቅና አገራችንን የእኩሎች አገር ለማድረግ ማንኛዉንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት አለበት ብሏል። የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረዉ የፍትህ፤የነጻነትና የዲሞክራሲ ትግል ግቡን እንዲመታ የመጀመሪያዉን እርምጃ የወሰደዉና ትግሉ የሚፈልገዉን የደም መስዋዕትነት ለመክፈል የትግሉ ግንባር የመጀመሪያዉ ደጃፍ ላይ የተሰለፈዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ካሁን በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ የወያኔን ዘረኝነት፤ዝርፍያ፤ጥላቻና ንቀት ለማስቆም መፍትሄዉ ከአገር እየተሰደዱ በየባህሩና በየበረሀዉ መሞት ሳይሆን ለስደታችን፤ ለመዋረዳችንና ለመረገጣችን ቀንደኛ ምክንያት የሆነዉን የወያኔ ስርአት እዝያዉ አገር ቤት ዉስጥ ፊት ለፊት በመጋፈጥ ብቻ ነዉ ብሏል።
የወያኔ እህአዴግ ዘመን አብቅቷል፤ከአሁን በኋላ ዘመኑ የኛ የኢትዮጵያዉያን ነዉ ያለዉ የግንቦት ሰባት ዝብባዊ ኃይሎች ቃል አቀባይ ይህንን የኛ የሆነዉን ዘመን እዉን የምናደርገዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ከዘረኝነት ነጻ የምናወጣዉ እንደአንድ ሰዉ ቆመን በጋራ ስንታገል ነዉ እንጂ የአገር ማዳኑንና የመስዋዕትነቱን አደራ ለተወሰኑ ወገኖች ብቻ በመተዉ አይደለም ብሏል። በመቀጠልም ወያኔን ፊት ለፊት ተፋልሞ ወንድሞቹንና እህቶቹን ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአባቶቹ በአደራ የተረከባትን ኢትዮጵያን ለልጆቹ ለማስተላለፍ የሚናፍቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከዛሬ በኋላ ዬት ሄጄ ወያኔን ልታገል የሚል ስጋት እንዳይሰማዉ አሳስቧል።ባለፈዉ ታህሳስ ወር እራሱን ለህዝብ ይፋ ይደረገዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ አያሌ ኢትዮጵያዉያን በየቀኑ እየተቀላቀሉት ሲሆን ይህንን የህዝብ ተገንና አለኝታ የሆነ ኃይል በመቀላቀል የአዲስቷ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ለመሆን የምትፈልጉ በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዉያን ህዝባዊ ኃይሉ በተከታታይ ለሚያወጣቸዉ መግለጫዎችና ህዝባዊ ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት እንዲትተባበሩ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ጥሪዉን ያስተላልፋል።

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”

ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡
ተቃወቅሞውን ለማቅረብ ያነሳሳችሁ ዋነኛ ምክንያት ምን ነበር?
አቶ ታዲዎስ፡- ብዙውን ጊዜ እኔ በጋዜጦች ስለ አርበኞች ታሪክ ያነበብኩትንና ያወቅሁትን እፅፋለሁ፣ እመረምራለሁ፡፡ የጣሊያኑ ፋሽስት ግራዚያኒ ሀገራችንን በመውረር በአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ላይ የፈፀሙት የግፍ ግድያ አሰቃቂ እንደነበር ስለተረዳሁ፤ ያ ሲቆጨኝ ደግሞ አሁን በጣሊያን ሀገር ለእሱ ሙዚየምና ሐውልት የመሰራቱን ወሬ ከኢንተርኔት ምንጮች ስላየሁ በጣም ተናድጄ እንደውም ተቃውሞ ማሰማት አለብን ብዬ ተነሳሁ፡፡ በኋላ ደግሞ እኛም የአንተ ዓይነት ሐሳብ ነበረን ብለው የባለ ዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር አነጋገሩን፡፡ ከዛ በመቀጠል ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንስራ የሚል ጥያቄ አቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያት ሶስቱ አካላት በጋራ ሰልፉን ለማድረግ ዝግጅት ማድረግ ጀመርን፡፡ ስለዚህ ለኢትዮጵያ ጠላት አይደለም ጣሊያን ሀገር ጨረቃም ላይ ቢሆን ሀውልት እንዲሰራ አንፈቅደም፡፡
በጊዜው ሩዶልፍ ግራዚያኒ ወንጀለኛ በመሆኑ የነበረው ፊልድ ማርሻል ማዕረግ ተገፎ ከወታደርነቱ ተባሮ በጦር ወንጀል ተከሶ 19 ዓመት ተፈርዶበት ቅጣቱን ሳይጨርስ ከእስር ቢለቀቅም እ.አ.አ. በ1955 ዓ.ም. ሞቷል፡፡ ታዲያ ይህ በጊዜው ወንጀለኛ ለተባለው ሰው ሐውልትም ሆነ የመታሰቢያ ሙዚየም ማሰራት ኢትዮጵየውያንን መናቅና የአባቶቻችንን ክብር የሚነካ በመሆኑ ሊሰራለት አይገባም፤ እንደውም ለፈፀመው እልቂት ጣሊያን በቂ ካሳ ስላልከፈለች ካሳ መክፈልና በይፋ ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል አቋም ይዘን ነው የወጣነው፡፡ ስለዚህ ግራዚያኒ ከነ አዳፋ ታሪኩ ሌላው እንዳይደግም ሲወሳ መኖር አለበት እንጂ እንደ ጀግና ሐውልት ሊሰራለት፣ሊወደስና ሊመሰገን አይገባም እንላለን፡፡
በወቅቱ የደረስው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
አቶ ታዲዎስ፡- በወቅቱ ግራዚያኒ በፊርማው በግፍ ኢትዮጵያውያንን ያስጨፈጨፋቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ከነደብዳቤው አለ፤ የዚህ ቅጂ እኔም ጋር አለ ይታወቃል፡፡ በተለይ የካቲት 12-14 ቀን 1929 ዓ.ም. ከ30 ሺህ በላይ ዜጎቻችንን በግፍ አዲስ አበባ ላይ እራሱ ግራዚያኒ አስጨፍጨፏል፡፡ ከ250 በላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ጨምሮ መነኮሳትን አስጨፍጭፏል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በ1938 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው አለም አቀፍ ጉባኤ ያቀረበው ሰነድ እንደሚያስረዳው 760,300 ሺህ ዜጎች ወዲያው ሲገደሉ 525,000 ደግሞ ከነቤት ንብረታቸው እንዲቃጠሉ ተደርጎ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሁለት ሺህ በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው መነኮሳት ተገድለዋል፣ በርካታ ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል፡፡ በርግጥ ከተዘረፉ ቅርሶቻችን መካከል እስካሁን የተመለሰው የአክሱም ሐውልት ብቻ ነው፤ ሌሎቹ ግን አሁንም እዛው ናቸው፤ ሊመለሱልንም ይገባል፡፡ ከዛ ውጭ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች በወቅቱ ተዘርፈው ተወስደዋል፤ 7 ሺህ ግመሎችም ተገድለውብናል፡፡ ይህም በሰነድ በተደገፈ ማስረጃ ለዓለም አቀፉ የሰላም ጉባዔ የቀረበ ነው፡፡ በወቅቱ ሰነድ ያልቀረበባቸውና ሰፊ ጥናቶች ሊደረግባቸው የሚገቡ በርካታ ጥፋቶች ተፈፅመዋል፡፡
ይህንን ተቃውሞ በዋነኝነት ማቅረብ የነበረበት መንግስት ነበር የሚሉ ወገኖች አሉ፤ እርስዎስ ምን ይላሉ?
አቶ ታዲዎስ፡- እኔም እስማማለሁ፤ ነገር ግን መንግስት ማዘጋጀት ካልቻለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማዘጋጀት ይችላል፡፡ እኔ እንደሚገባኝ መንግስት ተቃውሞ ያላቀረበው ከጣሊያን የሚያገኘው ዕርዳታ ይቀርብኛል በሚል ይመስለኛል፡፡ እኔ እስከማውቀው ይሄ መንግስት ዕለታዊና የፖለቲካ ገበያ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ወደፊት ትውልድ የሚኮራበትን ስራ የመስራት ዓላማ የለውም፡፡ ከዚህ በፊት የቀደሙ አባቶቻችን የሰሩትን በጎ ታሪኮች ሲያንቋሽሽ የኖረ መንግስት ስለሆነ እንዲህ ዓይነት የአባቶቻችንና እናቶቻችን አርበኞች ታሪክና ክብር የሚያስጠብቅ ስራ ይሰራል ብዬ አላስብም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው፣ ብሔራዊ ስሜትን የጠበቀ ህዝባዊ መንግስት ቢሆን ኖሮ ህዝቡን አስተባብሮ ይሄንን ስራ በቀዳሚነት መስራት የነበረበት እሱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ባያደርግም ዜጎች ይህንን ሰልፍ የማድረግ መብት ስላላቸው እኛም ሰልፉን አድርገናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የሀውልት ግንባታውን አለመቃወሙ ምን ያስረዳናል?
አቶ ታዲዎስ፡- ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በእጅ አዙር ለሀውልት ግንባታው እውቅና እንደሰጠ ይቆጠራል፤ ይህንን እኔም አምናለሁ፡፡ ከዚህም በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች የነበሩ ናቸው፡፡ እንደውም ነፃነታችንን ባወጅንበት ሁለት ዓመት ሳይሞላ በአርበኞች ላይ ጦርነት የከፈቱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለግራዚያኒ የጀግና ሐውልት መሰራቱን ባይቃወሙ አይገርመኝም፤ ምክንያቱም እነሱ የማን ልጆች ናቸው? እስኪ በስልጣን ላይ ካሉት (ከኢህአዴግ) መካከል ለሀገሩ እና ለወገኑ ብሔራዊ ስሜት፣ ነፃነትና ክብር የተዋጋ የአርበኛ ልጅ አንድ ሰው ካለ ንገረኝ? አንድም ሰው የለም፡፡ ስለዚህ የባንዳ ልጅ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ በእጅ አዙርም ሆነ በቀጥታ እውቅና በመስጠት ድጋፍ ቢያደርጉ አያስደንቀኝም፡፡
እናንተ ሰላማዊ ሰልፉን ከማድረጋችሁ አንድ ቀን በፊት መጋቢት 7 ቀን 2005 ዓ.ም ስምንት ሰዎች መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ክስተት በሰልፉ ወቅት እስር እንደሚኖር አልጠቆማችሁም?
አቶ ታዲዎስ፡- እሱን አውቀንም ነው ሰልፍ የወጣነው፡፡ አንድ ቀን አስቀድሞ ሌሎች ቢታሰሩም መውጣት አለብን ብለን ነው የወጣነው፤ እኛም ብንታሰር ሌሎችም እንደሚወጡ እናውቃለን፡፡ ችግር ይፈጠራል ብለን አልተውንም ፤መተውም የለብንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሀገርና የወገን ጉዳይ ነውና፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰልፉ ላይ የተገኙትን ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
የታሰራችሁት ምን ወንጀል ሰርታችኋል ተብላችሁ ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ፍቃድ አልጠየቃችሁም ፣ አላስፈቀዳችሁም በሚል ነው፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ በነበሩ የአጼ ኃይለስላሴ፣ በደርግ ዘመንም ሆነ አሁንም በወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ፈቃድ ይጠየቃል የሚል የተፃፈ ህገመንግስትም ሆነ አዋጅ አልነበረም፤የለምም፡፡ ዋናው ከእኛ የሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንደምናደርግ ማሳወቅና አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ ማድረግ እንጂ ፈቃድ መጠየቅ አይደለም፡፡ ይህንንም ለእኛ ጥቅም እንጂ እነሱን ለማስደሰት አይደልም፡፡ እኛ ደግሞ የሀገሪቱን የተፃፈ ህግ ተከትለን ሰልፉን ከማድረጋችን 10 ቀናት አስቀድመን አሳውቀናል፡፡
ኢትዮጵያውያንን በግፍ ለጨፈጨፈው ግራዚያኒ የተሰራለትን ሐውልት በመቃወማችሁ በኢትዮጵያ መንግስት መታሰራችሁ ምን ስሜት ፈጠረባችሁ? ለእኛ የበለጠ የተነሳሽነት ስሜት ሰጥቶናል፡፡ ጉዳዩንም አጠናክረን እንድንሄድ ትልቅ የሞራል ድጋፍ ሆኖናል፡፡
ከእስር ሲለቋችሁ ምን ብለው ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- ምንም ሳይሉን ለሁለት ሰው አንዳንድ ዋስ በማስጠራት ለቀውናል፡፡ ምክንያቱን ግን አልነገሩንም፤አላወቅንም፡፡ ከዛ ስትፈለጉ ትመጣላችሁ ብለው በዋስ ለቀውናል፡፡
በታሰራችሁበት ወቅትስ የገጠማችሁ ችግር አለ?
አቶ ታዲዎስ፡- በርግጥ እኔ ላይ ድብደባ አልፈፀሙም እንጂ ተመትተው ፊታቸው በተለይም አፋቸው አካባቢ የደማ ወጣት አይቻለሁ፡፡ ፊታቸው ያባበጠ ወጣቶችንም አይቻለሁ፡፡ ሌሎችንም ወጣቶች እንደደበደቧቸውም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ደህንነቶች ማታ መጥተው በግል እያስጠሩ በቢሮ ያናግሩ ነበር፡፡ ስራው ግን የፖሊሶች እንጂ የደህንነቶች አልነበረም፡፡ በታሰርንበት ዕለት ያለምግብና ውሃ ቀን ሙሉ እንድንውል ተደርገናል፡፡ በተለይ እስር ቤቱን ስቃይ አራዳ ፖሊስ መምሪያና ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ያለውን ስታይ ዕቃ ለማስቀመጥ ሆነ ለሌሎች እንሰሳቶች ለአንዲት ደቂቃ እንኳን እንዲቆዩበት አይመችም፡፡ እስር ቤቱን ስታይ በጣም ያሳዝናል፤ እዛ የገቡ እኮ ጤነኛ ሆነው የመውጣታቸው ዕድል እራሱ አነስተኛ ነው፤ለበሽታ የሚያጋልጡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ብቻ በጣም ያሳዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ የወንበዴ ስራ ነው፤ ይሄንን መንግስት ማረም አለበት፡፡ ሌላው መርማሪ ፖሊሶችና ደህንነቶች ያልተገቡና ከእስሩ ጋር የማይገናኙ የግል ህይወትን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፣ የኢ-ሜይል የይለፍ ቃል ይጠይቃሉ፣… ብቻ ብዙ ነው፡፡ በግል እኔን ደግሞ ፊታቸውን በኮፊያ የሸፈኑና ጥቁር መነፅር ያደረጉ ደህንነቶች ዋስ ጠርቼ ከወጣሁ በኋላ አንተ የአርበኞችን ታሪክ እያነሳሳህ ወጣቶችን እያነሳሳህ ስለሆነ ብታርፍ ይሻልሃል፤ በግል ልናናግርህ እንፈልጋለን እያሉ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ እኔ ግን በህጋዊ ደብዳቤ ያውም ያመንኩበት ካልሆነ ብትጠሩኝ አልመጣም፤ አላናግርም ብያለሁ፡፡
ከዚህ በኋለስ ይህን ተቃውሞ ለመቀጠልስ እቅዱ አላችሁ?
አቶ ታዲዎስ፡- አዎ አለን፡፡ ይህ ተቃውሞ ምላሽ አግኝቶ ያሰብነው እስኪሳካ እንቀጥላለን፡፡ ነገር ግን ዝርዝር ሁኔታውን በተመለከተ እያጠናን ስለሆነ ወደፊት ሀገር ውስጥ ያለነው ውጭ ካሉ ወገኖቻችን ጋር በመመካከር ምን መልክ መያዝ እንዳለበት ስንወስን ይፋ እናደርጋለን፡፡
በመጨረሻም የሚሉት ነገር ካለ ዕድሉን ልስጥዎት
አቶ ታዲዎስ፡- ህዝቡ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተለመደ ድጋፉን ከመስጠት ወደ ኋላ እንዳይል አደራ እላለሁ፡፡

Tuesday, March 26, 2013

የአማራው ስቃይ ቀጥሎል ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ 59 የአማራ ተወላጆች በመኪና መገልበጥ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

ከኢሊባቡር ክፍለ ሃገር በወያኔያዊ አጠራር { ቤኒሻንጉል ክልል] ኢትዮጵያዊነታቸው ተረስቶ ጎሳቸውን በማየት ብቻ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ከ 60 በላይ “አማራዎች ” ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ከተሳፋሪዎች ውስጥ 59ኙ ሲያልቁ አንዱ ብቻ ለመትረፍ እንደበቃ ኢሳት ዘገበ:: ይሀው በክልልህ ኑር የ ሚለው እና በመላ አገሪትዋ ተሰባጥረው በ ሚገኙ አማራው ብሄር ተወላጆች ላይ ብቻ ያነጣጠረው የማፈናቀል ዘመቻ ቀጥሎ ውሎ የማግዋግዋዙ ድርጊት ሲፈጸም አደጋው እንደደረሰ ዘገባዎቹ አስረድተው …ያለ ክልል ተብዬ ውጪ የሚኖር አማራ ብቻ ነው ወይ? ብዙ ትግሬዎች ብሎም ሌሎች ብሄሮች ይህንኑ ያደርጉ የለም ወይ? እንዴት አቅሙ በማይመጥን በጭነት መኪናስ እንዲግዋግዋዙ ይደረጋል? ሹፌሩስ ማን ነበር ?ለምንስ ከነሱ ተለይቶ በህይወት ተረፈ? በ እንዲህ አይነት ሁኔታስ እስከመቼ ይቀጥላል? ህንዶች እና ቻይኖች በክልሉ ሰፋፊ መሬቶች እየተሰጣቸው “አንድ ኢትዮጵያዊ ግን በገዛ አገሩ መኖር የማይችለው ለምንድን ነው ነው? የሚሉ ጥያቄዎች በአሁኑ ሰአት አደጋውን በሰሙ ሰዎች ዘንድ ያሳደረ ሲሆን :ምናልባትም ስለ ሁሉም ነገር ዝርዝር ይኖራልም ተብሎ ይጠበቃል…
ኢሳት ዜና:-ከአካባቢው ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው የተፈጠረው፣ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው መኪና ትክሻ በምትባል ቀበሌ ውስጥ ጀዴሳ በሚባል ወንዝ ውስጥ ገብቶ ነው።
ከትናንት ወዲያ በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ ለሞቱት ሰዎች የደረሰላቸው ሰው አለመኖሩን ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገልጽ የፈለጉ ተፈናቃይ አርሶደሮች ተናግረዋል።
ከሞቱት መካከል ህጻናትና ሴቶችም ይገኙበታል። በአደጋው ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
በተመሳሳይ ዜናም በዛሬው እለት በርካታ አርሶ አደሮች በክልሉ ልዩ ሚሊሺያ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት የሚፈናቀሉት ሰዎች በህገወጥ መንገድ ወደ ክልሉ የገቡ ናቸው ሲሉ ለአዲስ አድማስ መናገራቸው ይታወሳል።
የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን በተለከተ አስተያየታቸውን የሰቱት የሕግ ባለሞያ አቶ ግዛው ለገሠ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 32 “የመዘዋወር ነፃነት” በሚል ርእስ ስር ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ፤ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት መብት እንዳለው መደንገጉን ለጋዜጣው ገልጸዋል።

የመድኀኔዐለም መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ተቃውሞቸውን አሰሙ!!!

by
Image
ዛሬ የመድኀኔዐለም መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ከባድ ተቃውሞ አሰሙ:: በዚህ ተቃውሞ ላይ ከት/ቤቱ ተማሪዎች ከግማሽ ያላነሱ ተሳትፈዋል:: የዚህ ተቃውሞ ምክንያት የሆነው በትላንትናው እለት በተማሪዎች የመግቢያ ሰዐት ላይ ማሻሻያ ከተደረገ ቡሀላ ነው:: ማለትም ከዚህ በፊት ተማሪዎቹ የት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙት ከ2:40-2:50 ዛሬ ግን ባልተለመደ መልኩ የት/ቤቱ አመራሮች 2:30 አካባቢ ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቹ የሚገቡበትን በር በመዝጋት እንዳይገቡ ከልክለዋል:: ተማሩዎቹም ከዚህ በፊት ችግራቸውን የተናገሩ ቢሆኑም ድምፃቸውን የሚሰማቸው አተዋል:: ለማርፈዳቸው እንደ ትልቅ ምክንያት ካቀረቡት ውስጥ ፒያሳ ከሚገኘው ከማስታወቂያ ሚኒስቴር ጀምሮ እስከ ዊንጌት አካባቢ እየተሰራ ባለው መንገድ ምክንያትና ጊዮርጊስ ቤ/ክ አካባቢ በሚሰራው የባቡር ትራንስፖርት ግንባታ የተነሳ በዚያ አካባቢ ጉዞአቸውን የሚያደርጉ መኪኖች መስመራቸውን በማስታወቂያ ሚኒስትር በኩል ስላደረጉ የትራፊክ ፍሰቱ እጅግ አዳጋች እንደሆነ ተናጋረው ነበር:: ዛሬ ተማሪዎቹ ወደ ክፍል እንዲገቡ በሰላም ጠይቀው ቢሆንም የሚሰማቸው በማጣታቸው ከፍተኛ ጩኸቶችን እና የት/ቤቱን ር/ምህር የሚነቅፉ መፈክሮችን አሰምተዋል:: ከነዚህ መካከል
ሺበሺ ሌባ ነው!
ሺበሺ ጋዳፊነው!
ሺበሺ ይታሰር!
የሚሉት በሰፊው ተስተጋበተዋል:: ከአንዳንድ ተማሪዎች እንዳጣራሁት ከሆነ ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ነጭ ጋዎን ያደረገው አቶ ሺበሺ ብሩ የሚባለው ር/መምህር በት/ቤቱ ተማሪዎች እጅግ የሚወገዝ መሆኑን ነግረውኛል:: ለዚህ ምክንያት ተማሪዎችን እንደ ሚያመናጨቅና ያልተገቡ ቃላትን እንደሚጠቀም ነግረውኛል:: በሌላም በኩል ይህ ሰው ባለፉት ሳምንታት አንድ ተማሪን አግባብ ያልሆነ ምት መቶት የተማሪው ጆሮ በእጀጉ እንደተጎዳ ታውቆአል:: ፍርድ ቤትም ቀርቦ አንደ ነበር ለማወቅ ተቸልዋል::

አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ ግፊት እየተደረገ ነው/ወያኔዎች ተደናግጠዋል!!


Imageአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው:: በወያኔ ውስጥ የተደረገውን የስልጣን ሽግሽግ ተከትሎ አዳዲስ ለውጦች እየታዩ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የበላይነት ጎልቶ ለመውጣት እያቆበቆበ መሆኑን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ከአከባቢው የህወሃት አክራሪዎች መወገድ እና የአቶ ደብረጺሆን የግለኝነት አትኩሮት ለአቶ ሃይለማርያም እድሉን ገርበብ አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የአቶ ደብረጺሆን ግለኝነት በሙስና ስም ሊደፈቅ እንደሚችል ያከባቢው ገማቾች ሲናገሩ ወታደራዊው አካል ራሱን ለማዳን ሲል በተጠንቀቅ ከሃይለማሪያም አዲስ ካበበው ቡድን ጋር እንደሚሰለፍ አንዳንድ ፍንጮች ታይተዋል:: አቶ ሃይለማርያም በሙሉ መንፈስ ባይሆኑም ድፍረት እንዳገኙ ከደቡብ ጉባዬ በሁዋላ እየታየ ሲሆን የደቡብ ባለስልጣናት አንድነት ወያኔን አስደንግጦታል::
የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ባለስልጣናት በአቶ ሃይለማርያም ዙሪያ ጥያቄ በማንሳት ላይ ቢሆኑን በባህር ዳር በተደረገው ጉባዬ ላይ ያላቸውን የበላይነት እንዲያሳዩ ከፓርቲያቸው ግፊት እንደተደረገባቸው ምንጮች ጠቁመዋል::የደቡብ ባለስልጣናት አብዛኛዎቹ በግል አቶ ሃይለማርያምን በደቡቡ ጉባዬ ወቅን አግኝተው ያናገሯቸው ሲሆን በአንድነት ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እና ከሕወሓት የበላይነት እንዲላቀቁ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መክረዋል::ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚረዳቸው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አስታከው ተወያይተውል::
በህወሓት ውስጥ ያለው ፍትጊያ በአባይ ወልዱ የበላይነት ያበቃ ነው ብለን መደምደም እንደማንችል እና መሃል ሰፋሪ ሆነው ወዳሸናፊው ለማዘንበል የግለኝነት ሚና እየተጫወቱ ያሉት ደብረጺሆን ደቡቦችን አመቻችቶ መያዝ አስፈላጊ እንደሆን ስለተረዱት በሃይለማርያም ድፍረት ጀርባ ሆነው ጨዋታውን ማጋጋል ተይይዘውታል::
ምንጮቹ በአከባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በማየት እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይለቃል ጭምር የሚደፋፈራቸው የደህንነት አማካሪው አለቃ ጸጋይ ከፓርቲው መነሳቱን ተከትሎ በደብረጺሆን ተዘዋዋሪ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከጠ/ሚ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ እንደት ከስልጣን እንደሚባረር ታቅዶለታል::
በስበሃት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋይ የነበሩት እና በአሁን ሰአት በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በማሰባሰብ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ እና ከሕወሓት ሰው ጠፍቶ ነው ወይ ከደቡብ ለትግሉ አስታውጾ ያላበረከቱ ሰዎች የሚመሩን ነገ ስጋት ሆኖብናል የሚሉ ታጋዮች ይህን ፕሮፓጋንዳ ይዘው በአቶ ስበሃት በኩል መሰለፋቸው በዚህ ሰሞን እንደገና ተረጋግቷል የተባለውን የወያኔ ክፍፍል እንደ አዲስ አግሎታል::
የሃይለማርያም ስልጣን መያዝ ያልጣማቸው አክራሪ ሕወሓቶች ከባህር ዳር መልስ አዲስ አበባ ውስጥ በስበሃት ነጋ ሰብሳቢነት  አርከበ እቁባይ ;ብርሃነ ገብረክርስቶስ ;አዲሳለም ባሌማ;አባዲ ዘሙ ;አለቃ ጸጋይ በርሄ; ቅዱሳን ነጋ; ሃይለኪሮስ እና ሌሎችም ተሰባሰበው በህወሃት ውስጥ ስለለው ሁኔታ እና ራሳችን በፈጠርናቸው ደቡቦች ልንዋጥ ነው የሚል እደምታ ያለው ውይይት አካሂደው ነበር:;
በአንድ ወገን ሆነው በአባይ ወልዱ መሪነት ብኣዴንን አስከትለው የስብሃትን ቡድን እየተዋጉ የሚገኙት አዜብ መስፍን እና ሌሎች..ሳሞራ የኑስን እንደመከታ አድርገው ቢተሙም ሳሞራ ሁኔታዎችን ከመከታተል ዉች ተሳትፎው የተልፈሰፈሰ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ወይም በስበሃት አጠራር የከተማ ጮሌዎች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከን መምጣታቸው እያንገበገባቸው ሲሆን መለስ ዜናዊ ላልሰለጠኑ አናሳ ብሄሮች ሸጠን በማለት በሟቹ ላይ ከንፈር ነክሰው እየሞገቱ ሲሆን ይህም አልበቃ ብሎ ከድርጅታችንን መመሪያ እና ደንብ ዉጭ በተለያየ ቦታ የመለስን ምስል ማየት ሰለቸን በሚል ምስሉ እንዲነሳ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ምናልባት ሁኔታዎችን ያረግብ ይሆናል በሚል አቶ አዲሱ ምስሉ እንዲነሳ ቢናገሩም አቶ በረከት ጠላት እና ወዳጅን አጥርቶ ለመለየት በሚል እንዲቆይ አድርገዋል..
የስበሃት ቡድን ዉስጥ ውስጡን በትግራይ ለሚገኙ የሕወሓት የበታች አመራሮች እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ ለሚገኙ የህወሓት መኮንኖች በሚያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ በበረሃ ወንድም እና እህት ታጋዮችን ሰውተን ደማችንን አፍሠን የልጅነት ወዛችንን ጨርሰን ለዚህ የደረስነው ለደቡብ  ሰዎች እና ለከተማ ጮሌዎች ስልጣን ለመስጠት አይደለም አብረውን የታገሉ ኦሆዴዶች እንኳን ያላገኙትን ስልጣን ነው ያገኙት በማለት እና ለነገ የፖለቲካ ኪሳራ ያመጡብናል የሚያዘነብሉት ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ነው ለኛ አደጋ ስለሆኑ ከአሁኑ ልናሶግዳቸው ይገባል   በማለታቸው የወያኔ የውስጥ ቀውስ ግሎ ይገኛል::
በአሁን ሰኣት የደህንነት መዋቅሩን እና የጦር ሰራዊቱ ባለስልጣናት አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት እየሰሩ የሚገኙት ደብረጺሆን አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ እያደፋፈሯቸው ሲሆን ከጎናቸው እንደሚሆኑ እና ምንም እንደማይመጣ እየመከሯቸው ሲሆን ለሁለት አመት ነው ያስቀመጥንህ የሚለውን የአለቃ ጸጋይ ዛቻ ከአሁን በኋላ ሰሚ የሌለው ጩሀት እንደሆነ መናገራቸውን ምንጮቹ አስቀምጠዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ማሰብ/ድፍረት መጀመር; የህወሃት ክፍፍል መጋል; የኦህዲድ አህያዊ ሞኝነት; የብኣዴን በዝምታ ነገሮችን መከታተል; የኢሕኣዴግ ባልተጠበቀ መልኩ ቀውስ ውስጥ መግባት እና ሌሎች ተደማምረው የወያኔን ውድቀት የሚያመላክቱ ሲሆን በሃገሪቷ ላይ የፖለቲካ ለውጥ እንዲኖር ለማየት የሚጓጓውን ህዝብ ስል ነቀል ለውጥ እንዲያደርግ መስራት ደሞ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው::

Monday, March 25, 2013

በማእከላዊ እስር ቤት የታሰሩ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ተይዘው የታሰሩ ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ብዙዎቹ ቶርች ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት መዳረጋቸውም ታውቋል።
የተለያዩ ታማሪዎች በየጊዜው እየተያዙ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን በማእከላዊ እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው ከሚገኙት መካከል የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆኑት ኑርየ ካሲም እና ካሊድ ሙሀመድ፣ የጅማ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሲን ፈይሞ፣ ሙሀመድ አሚን ከድር፣ እና ጁነዲን ሁሴን፣ የሚዛን ተፈሪው አብዱላኪም አህመድ፣ የወሎ ዩኒቨርስቲዎቹ ጣሂር ሙሀመድ ፣ ሙሀመድ አብዱራሂም እና ሰኢድ ሙሀዲን፣ የጎንደር ዩኒቨርስቲዎቹ ሰኢድ አብርሀም ፣ኦማር ሙሀመድ፣ እና ሊና ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው አብዱላዚዝ ሰኢድ እንዲሁም የአዋሳ ዩኒቨርስቲዎቹ አብደላ ሙሀመድ ይገኙበታል።
የሙስሊም ጉዳይ አምደኛ የነበረው ሶሎሞን ከበደ፣ የከሚሴው ዳኢ ጀማል ከበደ፣ የሻሸመኔው ዳኢ አብዱረዛቅ ሼህ አህመድ፣ የከሚሴው ዳኢ ኢክርሀም አብዱ፣ የሀረርጌው ሁሴን ሮባ፣ የድሬዳዋው ሙሀመድ ሀሰን፣ የከምሴው ሁሴን አሊ እና አደም አህመድ አሊ በማእከላዊ እስር ቤት ታሰሩት ከፍተኛ ስቃይ ከደረሰባቸው መካከል ይገኙበታል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር መንግስታቸው እርምጃ እንደሚወስድ ሰሞኑን በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።

የመለስ ዜናዊ ራዕይና መተካካት ያልተንጸባረቀበት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ተጠናቀቀ

News, Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy.የመለስን ራዕይ ከግቡ ሳናደርስ እንቅልፍ አይወስደንም ብለዉ ሲዝቱ የከረሙት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች “መተካካት” የሚለዉን ዋናዉን የመለስ ፖሊሲ ወደ ጎን ትተዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዷቸው ስብሰባዎች በአብዛኛው ነባር አመራራቸዉን መርጠዉ ድህረ መለስ ጉዟቸዉን መጀመራቸዉን ዘጋቢዎቻችን ከአዲስ አበባ በላኩልን ዜና ገለጹ፡፡ በዚህ ባሳለፍዉ ሳምንት ዉስጥ አዋሳ፤ መቀሌ፤ አዳማና ባህርዳር ላይ በተካሄዱት የየፓርቲዉ ጉባኤዎች ላይ መለስ ዜናዊ መተካካት ብሎ የጀመረዉ ነባር የፓርቲ ሹማምንትን በአዲስ የመተከት ፖሊሰ እምብዛም በተግባር ባይዉልም አራቱም ድርጅቶች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አንዳንድ ነባር አባላቶቻቸዉን ከፓርቲዉ የስራ አስፈጻሚ ከሚቴ አስወግደዋቸዋል፤ በዚህም መሠረት ደአህዴን ተሾመ ቶጋን፤ ህወሀት ስዩም መስፍንን፤ብርሀኔ ገ/ክርስቶስንና አርከበ ዕቁባይን፤ኦህዴድ አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩንና ኩማ ደመቅሳን ብአዴን ደግሞ ብርሃን ኃይሉን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት አሰናብተዋቸዋል።
ሟቹ መለስ ዜናዊ በቀየሰዉ ዕቅድ መሰረት መተካካት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ ከ2007ቱ ምርጫ በሁዋላ ነባር የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ ይለቃሉ ተብሎ የተገመተ ቢሆንም በሰሞኑ የፓርቲዎች ስብሰባ እንደታየዉ ግን ነባር ታጋዮች ስልጣናቸዉን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተደርፈጓል። በ2003 ዓ.ም በተደረገዉ የመተካካት ሹምሽር የኃላፊነት ቦታዉን አጥቶ የነበዉ የብአዴኑ አዲሱ ለገሰ ተመልሶ ወደ ስልጣን የመጣ ሲሆን በቅርቡ በወጣት መሪዎች ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ በረከት ስምኦን፤ ህላዊ ዮሴፍና፣አባይ ወልዱ ጭራሽ ስልጣናቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸዉ ታዉቋል።
በ2003 ዓም በተደረገዉ መተካካት የመንግስትና የፓርቲ ኃላፊነታቸውን የለቀቁት ስዩም መስፍንና ሌሎች ዘጠኝ የህወሃት አባላት ከጤና ጋር በተያያዘ በራሳቸው ፈቃድ ድርጅቱን ለመልቀቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የተሰናበቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ግን የእነዚህን ሰዎች መሰናበት ከመተካካት ጋር አያይዞ ዘግቧል። በአጠቃላይ ብዙ ዉጣዉረድና ድራማ የታየበት የዘንድሮዉ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስብሰባ ሲጀመር የመለስ ዜናዉን ራዕይ ከግቡ እናደርሳለን በሚል መሪ ቃል የተጀመረ ሲሆን ሲፈጸም ግን በመርገጥ “መተካካት” የሚለዉን የድርጅቱን መስራች አላማና ራዕይ በሌላ ነገር በመተካት ተፈጽሟል።
ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማቅረባቸው አጋጣሚ ሳይሆን ከመለስ ህልፈት በሓላ በህወሃት ውስጥ ከተፈጠረው ልዩነት ጋር በተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጫችን ቢጠቅስም ይህን በተመለከተ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ብዙዎች እንደሚገምቱት ከአርከበ እቁባይ ጋር ጤነኛ ግንኙነት ያልነበራት አዜብ መስፍን በዚህ ጉባኤ በድል አድራጊነት ወጥታለች።
ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከ 17 ቀን 2005 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው የኢህአዴግ ጉባዔ ኃይለማርያም ደሳለኝን በሊቀመንበርነት፣ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት በድጋሚ ይመርጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
የወያኔ ኢህአዴግ ድርጅቶች ያደረጉትን ሹም ሽር በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አንድ የቀድሞ የሀወሀት ነባር ታጋይ ፡ ምርጫውን “ውሀ ቢወቅጡት ነው” ብለውታል። “ከእነዚህ ሰዎች ምንም የሚጠበቅ ነገር የለም፣ ምን አዲስ ነገር እንደማይፈጥሩም ይታወቃል። የአፈና ስርአቱ እንደሚቀጥል ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል ታጋዩ።

Oil attack on Ethiopian maid

Sharjah: A female employer of an Ethiopian housemaid who works illegally in the UAE has been summoned by the Sharjah police for
A female employer of an Ethiopian housemaid
The victim suffered first and second-degree burns on her head and back.
questioning in connection with allegations that an assailant poured hot cooking oil on the maid’s head and back, causing serious burns across the victim’s body.
The housemaid is scheduled to undergo skin grafting surgery on Monday, more than a month after being hospitalised following the incident in her sponsor’s Mirdif villa in early February.
The employer could not be reached on her telephone by Gulf News by press time on Sunday.
Al Qassimi Hospital officials said the maid has been fighting for her life in the intensive care unit (ICU) after suffering first- and second-degree burns. The victim has been heavily medicated as the ICU team helps nurse her back to health.
Source: golfnews.com

29 Ethiopian commando soldiers defect to Eritrea

March 24, 2013 — A total of 29 Ethiopian commando forces, who were trained in Blaten Special Force Institute, have defected toA total of 29 Ethiopian commando forces, who were trained in Blaten Special Force Institute, have defected to neighboring Eritrea. neighboring Eritrea.
The soldiers vowed they will liberate Ethiopia from what they say is an oppressive and ruthless dictatorship, according to their communiqué released on Saturday.
Ethiopia is no stranger to high profile military defections. in 2005, eight Ethiopian air force pilots, who were training in Israel, defected and claimed asylum at an Eritrean embassy in Israel.
Similarly, In 2006, over 300 Ethiopian troops, including Brigadier General Kemal Gelchu, who along with his trusted colonels, defected to Eritrea

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው

በቤተክህነቱ በዚሁ ጉዳይ ላይ ስብሰባ እየተደረገነው

img_4680

ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡
የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት መቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስምቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛም በቅድስት ስላሴና በየሆስፒታሎቹ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አባ እያሱ ሰብስቤ የተባሉ ተማሪ በየካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም ደቀመዝሙር በኃይሉ ሰፊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አረጋጧል፡፡ አመሻሹ ላይም ገ/እግዚያብሄር የተባሉ ተማሪ በአምቡላንስ ከኮሌጁ ተወስደዋል፡፡ ተማሪዎቹ በደል አድርሰውብናል ከሚሉዋቸው የኮሌጁ ሀላፊዎች ውስጥ መምህር ፍስሀፂዮን ደሞዝ አካዳሚክ ዲን እና መምህር ዘላለም ረድዔት የቀን ተማሪዎች አስተባባሪ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል፡፡
ደረሰ ስለተባለው ችግር ለማጣራት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል በኮሌጁ ጉዳይ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተናግረው የነበረ ቢሆንም ተሰብሳቢ ባለመሟላቱ ስባሰባው እንዳልተደረገ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Sunday, March 24, 2013

ለአቤቱታ የመጡ የደቡብ ክልል ዜጎች መታገታቸው ተዘገበ

የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ ለአቤቱታ የወጡ ከ1000 ያላነሱ ሰዎች በፖሊስ ታግተው መዋላቸውን የአካባቢው ሰዎችን ዋቢ በማድረግ ኢሳት ዘግቧል።
እንደ ኢሳት ዘገባ ከፍትህ ፣ ከመልካም አስተዳዳር እና ከመብት እጦት ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎችን ላለፉት 8 አመታት ሲያቀርቡ የቆዩት የቁጫ ወረዳ ነዋሪዎች፣ 7 ወኪሎቻቸው መታሰራቸውን በመቃወም ትናንት አቤቱታ ለማቅረብ ሲሰባሰቡ በፌደራል ፖሊሶች መታገታቸው ከነኝህም ታሳሪ ዜጎች ድበደባ የደረሰባቸው ሰዎች መኖራቸውም ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረበላቸው የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ክልል ተወካይና የምክር ቤት የሆኑት አቶ ዳንኤል ሽበሺ በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች የሚታየው ችግር የቆየ መሆኑን አውስተው፣ የትናንትናው ተቃውሞ ግን የሽማግሌዎች መታሰር መሆኑን ገልጸዋል።
ኢሳት አክሎ እንደዘገበው አቶ ዳንኤል በሰላም በር የታሰሩት ሰዎች ህዝብን ታነሳሳለችሁ ተብለው መሆኑን መግለጻቸውን በአጠቃላይ በክልሉ ያለው የመልካም አስተዳደርና ፍትህ እጦት መባባሱን ጠቅሷል።
የአገር ሽማግሌዎች ለምን ታሰሩ? ለአቤቱታ የመጡ ሰዎችስ ለምን ታገቱ በማለት ኢሳት ጥያቄ ያቀረበለት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ አኒሳ ፣ ሰዎቹ ጥያቄ ያቀረቡበት መንገድ አግባብ አይደለም በሚል መታሰራቸውን አምኖ፣ ሰልፈኞቹ የመጡበት መንገድ ተገቢ ባለመሆኑ እንደመለሱዋቸውም ተናግረዋል ብሏል ኢሳት።

ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት

መጋቢት 18/2005 ዓ.ም የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ በዚህ መዝገብ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይግባኝ ከጠየቁ አምስት ወር አልፏቸዋል፡፡
ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡
የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው፡-
‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡››
አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡ ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡
ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ
‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!››
ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ
‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡ ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡
በእንዲህ አይነት ሁኔቴ መዋዘገቡ በመካረሩ መግባባት አልቻሉምና ጉዳዩ ሚንስትሮች ምክር ቤት ደረሰ፡፡ በሚንስትሮች ም/ቤትም ስብሰባውን የመራው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን ሲሆን፣ ዳኛውም አብሮ ቀርቧል፡፡ አቶ ደመቀ መጀመሪያ ዳኛው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ፡፡ ዳኛውም ስለክሱ አጠር አድርጎ ካብራራ በኋላ እንዲህ ሲል ደመደመ፡-
‹‹እስክንድር ነጋን ‹አሸባሪ› ብሎ ለመፍረድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ በሚቀጥለው ቀጠሮ በነፃ አሰናብተዋለሁ፤ እንዲህ ማድረግ አትችልም የምትሉኝ ከሆነ ግን ክቡራን ሚንስትሮች በዕለቱ በችሎት ለመሰየም ፍቃደኛ አለመሆኔን በትህትና ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ!››
ከዚህ በኋላ ሚኒስትሮቹ መወያየት ጀመሩ፡፡ ተከራከሩ፤ በመጨረሻም አቶ ደመቀ እንዲህ አለ፡-
‹‹እኔም ከአቶ አማረ ጋር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰውዬ /እስክንድር/ የተነሳ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህም ብንፈታው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ፡፡››
አንድ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹በመሰረተ ሃሳቡ ላይ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን እስከዛሬ አስረነው ‹ነፃ ነህ› ብለን ብንለቀው የፖለቲካ ኪሳራ ስልሚያስከትልብን፣ ከፍርዱ ላይ ቅንስናሽ አድርገን ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ብናደርግ የተሻለ ነው፡፡››
ሌላ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹እስክንድርን እኔ አውቀዋለሁ፤ የአሜሪካን ሀገር መኖሪያ ፍቃድ እና ብዙ ሀብት እያለው እዚህ ነገር ውስጥ የገባ ሰው ነው፡፡ እናም በፍፁም ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አይሆንም››
ሌላኛው ሚንስትር ቀጠለ፡-
‹‹ኧረ ለመሆኑ መለስ አለም አቀፍ ጫና እንደሚያስከትል እያወቀ ለፓርቲያችን ጥቅም ብሎ የገባበትን ጉዳይ፣ ዛሬ እርሱ አልፏል ብለን ጫና ይምንፈራበት ምክንያት ከየት የመጣ ነው? በቃ! መለስ አደገኛ ሰው ነው ብሎ አስሮቷል፡፡ አለቃ! እዛው ይበስብስ!››
የሚንስትሮች ምክር ቤትም ቢዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ሳይችል በመቅረቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት አቶ ተገኔ ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡
…በእርግጥ ከአቶ ተገኔ ማብራሪያ በኋላ የሚኒስትሮች ም/ቤት ምን አይነት አቋም ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ሊሳካ አልቻለም፡፡ መረጃውንም እስከ ዛሬ ያቆየሁት ለዚህ ነበር፡፡ አሁን ግን የቀጠሮ ቀን ሰለደረሰ ልነግራችሁ ተገደድኩ፡፡
እናም የፊታችን ረዕቡ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚከተሉት አራት ነገሮች አንዱን እናያለን ብዬ አስባለሁ፡፡
1. የሚንስትሮች ም/ቤት ጫናው ስለከበደው በነፃ ይለቀዋል፣
2. መለስ እያወቀ የገባበትን ጫና አንፈራም! (ራዕዩ እናስቀጥላለን እንደማለት ነው) በማለት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ያፀናሉ፣
3. ከተፈረደበት 18 ዓመት ላይ ቅንስናሽ አድርገው፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወደ ማግባባቱ ይሄዳሉ፣
4. ዳኛው አሞኘ እንደፎከረው ከችሎቱ ይቀርና አሁንም ‹‹የመጨረሻ›› ቀጠሮ ይሰጣል፡፡
የሆነ ሆኖ እንዲህ የሚል አንድ እውነት ‹‹በመሪዎቻችን›› ግንባር ላይ ተቸክችኳል፡፡ ‹‹ሲቪሉ ጀግና እስክንድር ነጋ እያርበደበደው ነው!››
አዎ! እኔም እላለሁ፣ የእስክንድር እና መሰሎቹ የግፍ እስር አርብድብዶ ብቻ አይተዋችሁም!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ውድቀት ለአምባገነኖች!!