Tuesday, January 19, 2016

የትግራይ ነጋዴዎችን ለመጥቀም አዲስ የበርበሬ አዋጅ በጎጃም

January 19,2016
berbere
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በተለይ በምዕራብ ጎጃም አካባቢ የደነገገው አዲስ የበርበሬ አዋጅ ችግር እያስከተለ መሆኑን የጎልጉል እማኝ ዘጋቢ (ireporter) በላኩልን መረጃ አስታውቀዋል፡፡ እንደ እማኝ ዘጋቢው ከሆነ አዋጁ የወጣው በ2002ዓም ሲሆን በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በዚህ ዓመት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ይህ በበርበሬ ላይ ብቻ የተደነገገው አዋጅ ዋና ምክንያቱን በውል ለማወቅ የሚያዳግት ቢሆንም እንደ እማኝ ዘጋቢው አስተያየት በርበሬው ወደ ትግራይና አዲስ አበባ የሚላክ በመሆኑ በተለይ የትግራይ ነጋዴዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመጥቀም ታስቦ እንደሆነ ከሚሰጡት ግምቶች የላቀው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
እማኝ ዘጋቢያችን የላኩልን መረጃ እንዲህ ይነበባል፡-
“በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ በፍኖተ ሰላም በሺንዲ ወረዳዎችና አካባቢዎች በበርበሬ ንግድ ላይ አዲስ አዋጅ አውጥተው ህዝቡን ለችግር ነጋዴውን ደግሞ ለኪሳራ እየዳረጉት ነው። አዲስ ያወጡት አዋጅ ለጎጃም ብቻ ሲሆን፡-
1ኛ. ሁሉም ነጋዴዎች በሚሸጡበት ቦታ ሁሉ ቅርንጫፍ እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ለምሳሌ የቡሬ ነዋሪ የሆነ ነጋዴ መቀሌ መሸጥ ቢፈልግ ቅርንጫፍ ሊኖረው ግድ ነው፤ አዲስ አበባ ቢሆን ሌላ ተጨማሪ ቅርንጫፍ ሊኖረው ያስፈልጋል፤ ሽሬም ቢፈልግ እንዲሁ፤
2ኛ. ማንኛውም ነጋዴ ከነጋዴ ላይ መግዛት አይችልም፤ ለምሳሌ 90 ኩንታል መጫን የፈለገ 85 ኩንታል ኖሮት 5 ቢጎለው 5 ከነጋዴ ላይ ገዝቶ መሙላት አይችልም፤
3ኛ. ቫት እንዲጀምሩ ማለትም በቫት እንዲገዙ፤
4ኛ. ከ6 ወር በላይ መከዘን ወይም ማስቀመጥ አይቻልም።
ለምሳሌ 1 ኪሎ 60 ብር ቢገዛና በቀጣይ ጊዜ ቢቀንስ 50 ብር ቢሆን ከስሮም ቢሆን መሸጥ ግዴታው ነው።”
በማለት የአካባቢው ነጋዴና ሕዝብ እየተጋፈጠ ያለውን ችግር እንድናሰማላቸው ልከውልናል፡፡ (ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ)

No comments: