Friday, August 1, 2014

የህወሃት ሽብር መቆም አለበት!

August1/2014
ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለ አሸባሪ ወያኔና ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው፣ መንግስት በመተቸታቸው በግልጽ በመጻፋቸውና በአደባባይ በመናገራቸው ከዚህም አልፎ በጥርጣሬ በተለይም በብሄረሰብ ማንነታቸው እያሳደደ የሚያፍን የሚያሰቃይና የሚገል የሽብር ተቋም ካለ ወያኔ ብቻ ነው። በኢትዮጵያ መሬት ላይ ሰላማዊ ዜጎችን ኢላማ ያደረገ የተቃውሞ ሃይል በተግባርም ሆነ በአስተሳሰብ ከወያኔ ውጪ አንዳች ሃይል የለም።
አፋኙ የወያኔ ስርአት በተለየም የህዝቡን ሀብትና ንብረት እየዘረፉ የሚቀማጠሉት የህወሃት መሪዎችና ሎሌዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ በሰሙ ቁጥር እንደሚሸበሩና እንቅልፍ አጥተው እንደሚያድሩ ይታወቃል። አፍነውና ዘርፈው ገለው የሚገዙት ህዝብ ግፍ በዛብኝ ብሎ በተናገረ ቁጥር የሚሸበሩት እነሱ ብቻ እንጂ ህዝቡ አይደለም።
በኢትዮጵያ ምድር ያለው አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ሺ ምሳሌዎችን ጠቅሶ ማስረዳት ይቻላል። ሶስት አመት ሙሉ የሰላም እጃቸውን እየዘረጉ ከልመና ባልተለየ ሁኔታ መብታቸውን የጠየቁና ድምጻችን ይሰማ ያሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማንንም ዜጋ አላሸበሩም። የተገላቢጦሽ እነሱ አሸባሪ ተብለው የግፍ ሰቆቃ ይፈጸምባቸዋል። ጋዜጠኞችና ጦማሪዎቹ መንግስት ያወጣውን ህግ እንዲያከብር ስለጠየቁ በአደባባይ ስለጻፉ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። እነሱ ያሸበሩት ሀገርና ህዝብ የለም። ከመንገድ ላይ ጎትተው እንደ እባብ ቀጥቅጠውና ፈነካክተው በማግስቱ ፍርድ ቤት ያቀረቧት ወየንሸት ሞላ የተባለች ባለ ተስፋ ወጣት የወያኔ አረመኔዎች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ጭፍጨፋ እግር ጥሏት ከማየትና ከመታዘብ ውጪ ያሸበረችው ሰው፣ ሀገር የለም። በየወህኒ ቤቱ እና አፈና ጣቢያው ታስረው የሚቀጠቀጡት የኦሮሞ ልጆች ለጥያቄያቸው መልስ ሲጠብቁ ከመጨፍጨፍ ያለፈ የፈጸሙት እብሪት የለም። በየክልሉ ቀና ብለህ ባለስልጣን ተናገርክ፣ ጥያቄ ጠየቅክ፣ ባለስልጣን ደፈርክ፣ ተሰብስበህ አየንህ ወዘተ እየተባለ የሚገረፈው እንደ እንስሳ እየተገደለ የሚጣለው ገበሬ የሰራው ወንጀል የለም። አሸባሪም አይደለም! በየቦታው ቦንብ እየቀበረ አፈንድቶ ንጹሃንን ገድሎ ሊያፈነዱ ሲሉ ፈንድቶባቸው ራሳቸውን ገደሉ ብሎ በአደባባይ የሚሳለቀው አሸባሪው ህወሃት እንጂ ንጹሃኑ አይደለም።
የኛ መሪ አንዳርጋቸው ከልጅነት እድሜው ጀምሮ ራሱን ለህዝብ ነጻነት የሰጠ አርበኛ እንጂ አሸባሪ አይደለም። በተመሳሳይ ውንብድና ከጎረቤት ሀገር ድረስ በአለም አቀፍ የወረበሎች ውንብድና መንገድ ወያኔ እያፈነ የገደላቸው አሮሞዎችና፣ ሱማሌዎች፣ አኙዋኮች፣ አማሮችና ሌሎችም ነጻነት ከመፈለግ ውጪ ያሸበሩት ህዝብና ሀገር የለም።
በኢትዮጵያ ምድር የነጻነት ድምጽና ኮሽታ በሰማ ቁጥር የሚሸበረው ህወሃትና በለሟሎች ብቻ ናቸው። ይህ የነጻነት ድምጽ ደግሞ እየጎላ መሄዱ የማይቀር ነውና ወያኔ ሰፈር ሽብር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወጣት፣ ሴት፣ ሽማግሌ፣ ገበሬ እና በየቦታው ያላችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ! አሸባሪህ ወያኔና ወያኔ ብቻ መሆኑን አውቀህ በገዛ ሀገርህ ላይ ነጻነት በተመኘህና በጠየቅህ ጊዜ ሁሉ ለሽብር ጥቃቱ ኢላማ ያደረጉህን ወያኔ ተባብረን ከላያችን ለማውረድ ተነስ! በያለህበት እምቢ በል! ለወያኔ የሚጠቅም የመሰለህን ነገር ሁሉ አታድርግ! አትተባበር! ሸቀጣቸውን አትግዛ! ወያኔዎችን ከማህበራዊ ሂወትህ አግል! የቻልክ ሁሉ ደግሞ የነጻነት አርበኞችን ዛሬ ነገ ሳትል አሁን ተቀላቀል!!! ነጻነታችን ያለው በእጃችን ላይ መሆኑን አትዘንጋ። ግንቦት 7 ሁልጊዜም ከመቼውም ጠንክሮ ከጎንህ ነው።
የወያኔን ሽብር በተባበረ ሃይል እናቁመው!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን በሰሜን ጎንደር የዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል

August 1/2014
end genocide now


የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አቅዶ ሲነሳ፣ የግቡ መረማመጃ ያደረገው የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ተቋሞችን፣ ኃይማኖቶችን፣ ዕሴቶችን እና በተለይም «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ ተወላጆች ነጥሎ ማጥፋት የሚል ሥልት በመከተል እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የጥፋቱ ቅድሚያ ዒላማ ያደረገው ለትግራይ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ ደራሽ እና የተራበ አንጀታቸውን ዳሳሽ በሆነው የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምትና የሠቲት ወረዳዎች ሕዝብ ላይ ነው። ወያኔ በእነዚህ የትግሬ አዋሣኝ ወረዳዎች ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን የዘረጋው በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያውና ታላቁ ምክንያት የእነዚህ ወረዳዎች ሕዝብ ዐማራ በመሆኑ እና የትግራይ አዋሳኝ ስለሆነ የትግራይን ታሪክ ክፉውንም ሆነ ደጉን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት የዚያ አካባቢ ሕዝብ የትግሬ-ወያኔ ለተነሳለት ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ዐማራ እንቅስቃሴ የማይተኛ እንደሆነ ስለሚረዳ ይህን ሕዝብ ብቻውን አቁሞ ማጥፋት ለወደፊቱ ግሥጋሴው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው በማመን የችግር ጊዜ ደራሻቸውን ሕዝብ ያለርኅራኄ ጨፍጭፈውታል።
ሁለተኛው ምክንያት «ታላቋን ትግራይ» ለመመሥረት ባላቸው ዕቅድ ለውጭ ግንኙነታቸው መውጫ መግቢያ እንዲሆናቸው ከሱዳን ጋር የሚዋሰኑትን እነዚህን ወረዳዎች ወደ ትግራይ ማጠቃለል ስለነበረባቸው ነው። ሆኖም የአካባቢው ሕዝብ «ነገዳችን ዐማራ፣ ጠቅላይ ግዛታችን ጎንደር ነው።» እያለ እንዳያስቸግራቸው በቅድሚያ ነባር ነዋሪውን ጎንደሬ አጥፍቶ በሠፋሪ ትግሬ ማስያዝ ለዓላማቸው ሥምረት ያገለግላል ብለው በማመናቸው ነው።
ሦስተኛው ምክንያት የሠቲት፣ የወልቃይት፣ የጠገዴ፤ እና የጠለምት ወረዳዎች ለሠፋፊ የእርሻ በተለይም ለጥጥ፣ ለሰሊጥ፣ ለማሽላ፤ ለዱር ሙጫ፣ ወዘተርፈ ምርት የሚያመች የለም እና ሠፊ መሬት ባለቤት በመሆኑ ነው። ስለዚህ የእነዚህ የሚያጓጉ የተፈጥሮ ኃብቶች ተጠቃሚ ለመሆን ተቀናቃኙን የጥንት ነዋሪውን ሕዝብ የግድ ማጥፋት አለብን ብለው በማመናቸው ነው።
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በዐማራ ነገድ አባሎች ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸም የጀመረው  ድርጅቱ ገና «ተጋድሎ  ሓርነት ሕዝቢ ትግራይ (ተሓሕት)» ተብሎ ይጠራበት ከነበረበረበት የጨቅላነቱ ዘመን ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ታሪክ ያስረዳል። በተለይም የትግራይ አዋሣኝ በሆኑት የሰሜን ጎንደር ታሪካዊ አካሎች በነበሩት ወረዳዎች ነዋሪ የሆኑ ዐማራዎችን ለማጥፋት ተሓሕት-ሕወሓት ፕሮግራም ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው ከ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ የድርጅቱ ነባር አባሎች ያስረዳሉ። የሰሜን ጎንደር ለም እና ድንግል ወረዳዎች የሚባሉት፦ ወልቃይት፣ ሠቲት፣ ላይ እና ታች አርማጭሆ፣ ጠገዴ እና ጠለምት ናቸው። በሕወሓት ታሪክ ውስጥ «የዲማ ኮንፈረንስ» በመባል የሚታወቀው እና ከ፻፶ (አንድ መቶ ሃምሣ) ያላነሱ አባላቱ ተካፋይ በሆኑበት በየካቲት ወር ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. «ጸደቀ» የተባለው ፕሮግራም ወልቃይትን፣ ሠቲት፣ ጠገዴን እና ጠለምትን ከዐማራ በማጽዳት ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ መጠቃለል እንዳለባቸው ያስገነዝባል።
t1ይህ ፕሮግራም ዐማራውን ከማውገዝ አልፎ፣ በትግሬ ደመኛ ጠላትነት በመፈረጅ በግልፅ ቋንቋ «የትግላችን ዓላማ ፀረ-የዐማራ ብሔራዊ ጭቆና ነው» ይላል።ከዚህ በተጨማሪም ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅም እና የሕዝቧን አንድነት በእጅጉ የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን፣ አገሪቱ እንደአገር እንዳትቀጥል የሚያደርግ ዓላማ ያለው መሆኑ በፕሮግራሙ መሠረት ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በመፈጸም ላይ ያሉት ተግባሮች ሁነኛ እማኖኞችና ነቃሾች ናቸው።
በ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የጸደቀውን የድርጅቱን ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድረግ አርከበ ዕቁባይ «ወደ ታላቋ ትግራይ ረፐብሊክ ሊካተቱ ይገባል» የተባሉትን ከጎንደር ወልቃይትን፣ ጠገዴን፣ ጠለምትን፣ ሠቲት፤ እንዲሁም ከወሎ ክፍለሀገር ደግሞ ራያና ቆቦን፣ አላማጣን፣ ወልድያን፣ ጨምሮ እስከ አሸንጌ ኃይቅ ድረስ ያሉትን ሥፍራዎች የሚያካትት ካርታ አዘጋጀ (ተያያዥ ካርታዎችን ከ፩-፬ ይመልከቱ)። በዚህ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ የምትመሠረተው «የትግራይ ረፐብሊክ» ከሱዳን ጋር የሚያገናኛት የመሬት አካል እንድታገኝ ሆነ። በዚህም መሠረት በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. ተሓሕት-ሕውሓት ያለ የሌለ ኃይሉን ከጎንደር ክፍለ ሀገር ነጥቆ ወደ ትግራይ ባካለላቸው ጥንተ-ነዋሪ የዐማራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ክንዱን አነሳ።
t2
ካርታ ፩፦ የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ ካርታ (እስከ ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ድረስ)
ከሁሉ አስቀድሞ መታወቅ ያለበት ጉዳይ የትግሬ-ወያኔ ዐማራን ማጥፋት የጀመረው ኢትዮጵያዊነትን በሁለንተናዊ መልኩ ከትግራይ ሕዝብ አዕምሮ እንዲጠፋ ካደረገ እና የዓላማው ተቃዋሚ የሆኑ የራሱን ነገድ አባሎች ከትግራይ ምድር ካጸዳ በኋላ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ በ፲፱፻፷፱ ዓ.ም. የተሓሕት-ሕወሓት አመራር አባላት የሆኑት ስብሐት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ሥዩም መሥፍን፣ ስዬ አብርሃ እና አውአሎም ወልዱ «በትግራይ ክፍለሀገር ውስጥ የሚኖሩ ዐማሮች፣ ኦሮሞዎች እና የሌሎችም የኢትዮጵያ ነገዶች ተወላጆች ከትግራይ መሬት ለቀው ይውጡ፤ ትግራይ የትግሬዎች ብቻ ናት!» ብለው ሲወስኑ በወቅቱ ይህን ውሣኔ ተቃውመው የቆሙት ግደይ ዘርዓፅዮን እና ዶክተር አታክልቲ ቀጸላ ብቻ እንደነበሩ ስለሁኔታው የሚያውቁት አቶ ገብረመድህን አርአያ በተለያዩ አጋጣሚዎች አሣውቀዋል። ያ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኖ፣ ዛሬ ትግሬዎች ትግራይን በብቸኝነት፣ ቀሪዋን ኢትዮጵያ ደግሞ በገዥነት ተቆጣጥረው ይገኛሉ።
t3
ካርታ ፪፦ አዲሱ የትግራይ «ክልል»
ተሓሕት-ሕወሓት  የሰሜን ጎንደር አካል በሆኑ ወረዳዎች ነዋሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመፈጸም  እንዲሁ ዘሎ ወደ አካባቢው አልገባም። ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነበረበት። ለዚህም ሁኔታዎች እስኪመቻቸቹ ድረስ ጊዜ መግዛት ነበረበት። አንደኛ፥ ጠለምት፣ ወልቃይት እና ጠገዴ በኢሕአፓ ተዋጊዎች የተያዘ ስለነበር፣ አቅሙ እስኪጎለብት እና ኢሕአፓን መጓባት እስኪችል መጠበቅ ግድ በማለቱ፤ ሁለተኛ፥ በወቅቱ የአካባቢው ሕዝብ እንደማይቀበለው ያውቅ ስለነበር፣ ሕዝቡን አሸማቆ እና ረግጦ መቆጣጠር የሚችልበት አቅም መፍጠር ስለነበረበት፤ እንዲሁም ከሁሉም በላይ የአካባቢውን ሕዝብ ማንነት የሚያውቅ ባንዳ መልምሎ ማሰልጠን ጊዜ የሚጠይቁ በመሆናቸው ነበር። ይኽም ሆኖ፣ ተሓሕት-ሕወሓት በተጠቀሱት ወረዳዎች  በመሽሎክሎክ አሻራውን ከማስቀመጥ አልቦዘነም።
t4
ካርታ ፫፦ የትግራይ «ክልል» ከጎንደር የወሰዳቸው ወረዳዎች
t5
ካርታ ፬፦ የትግራይ «ክልል» ከወሎ የወሰዳቸው ወረዳዎች
በ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ላይ ለተሓሕት-ሕወሓት ዓላማ መሳካት የሚያመች አጋጣሚ ተፈጠረ። ይኸውም በሻዕቢያ እና በጀበሓ፣ እንዲሁም በኢሕአፓ እና በተሓሕት መካከል የተደረጉት የጦፉ ውጊያዎች ነበሩ። በጦርነቱም ሻዕቢያ እና ተሓሕት-ሕወሓት የድሉ ባለቤቶች ሆኑ። ጀብሓ እና ኢሕአፓ ተበታትነው የትጥቅ ወረዳቸውን ለቀው በቡድን እና በተናጠል ወዳፈተታቸው አካባቢ አመሩ። ወረዳዎቹን ሁለቱ አጥቂ ኃይሎች ተቆጣጠሯቸው። ከሁሉም በላይ የኢሕአፓ ተዋጊ የነበሩት፦ ያሬድ ጥበቡ፣ ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሠ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ታደሰ ጥንቅሹ፣ ሕላዌ ዮሴፍ፣ ካሣ ተክለብርሃን እና በአጠቃላይ በቁጥር ፴፯ (ሠላሣ ሰባት) የሚሆኑት ለተሓሕት-ሕወሓት በሎሌነት አደሩ። እኒህ ቀደም ሲል ከተሓሕት-ሕወሓት ጋር ግንኙነት መሥርተው ስለነበር፣ የኢሕአፓን ተዋጊ ኃይል እንዲጠቃ የባንዳነት ሥራ ሠሩ። በዚህም የተነሳ የኢሕአፓ ተዋጊ ኃይል በተሓሕት ተገደለ፣ ተማረከ፣ ዕድለኛ የሆነውም በስደት ሱዳን ገባ። ይህ ሁኔታ ለተሓሕት-ሕወሓት ዐማራን የማጥፋት ተልዕኮው ሠፊ በር ከፈተለት።
በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሠቲት እና ጠለምት ዐማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት  ወንጀል እንዲፈጸም አመራር የሰጡ የተሓሕት-ሕዋሓት መሪዎች፦
(1) ስብሐት ነጋ (በወቅቱ የተሓሕት-ሕወሓት ሊቀመንበር የነበረ)፣
(2) መለስ ዜናዊ (የቀድሞው የትግሬ-ወያኔ መሪ፣ በ፪ሺህ፭ ዓ.ም. በሞት የተለየ)፣
(3) አረጋዊ በርሄ (ዶክተር፣ በስደት ሆላንድ የሚኖር)፣
(4) ዐባይ ፀሐዬ፣
(5) ሥዩም መሥፍን፣
(6) ግደይ ዘርዓጽዮን (በስደት ኖርዌይ የሚኖር) ናቸው።
መመሪያውን በማስፈጸም ጥቃቱን በአካል ያስፈጸሙት ደግሞ ሥዬ አብርሃ (በአሜሪካን አገር ይኖራል)፣ አርከበ ዕቁባይ፣ ፃድቃን ገብረተንሣይ፣ ዘርዓይ አስገዶም እና አውአሎም ወልዱ መሆናቸውን የድርጊቱን ሂደት በተጨባጭ የሚያውቁት አቶ ገብረመድኅን አርአያ ያረጋግጣሉ። ሁሉንም የሰሜን ጎንደር ዐማራዎች የጭፍጨፋ ዘመቻ በበላይነት ይመራው እና ያስተባብረው የነበረው ስብሐት ነጋ እንደነበር የዐይን እማኞች የነበሩ በተለያየ ጊዜ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በአርማጨሆ የዐማራ ተወላጆች ላይ የጥቃት ዒላማውን ሲያነጣጥር፣ መንገድ መሪ እና መረጃ አቀባይ በመሆን የጥፋቱን ከፍተኛ ድርሻ የሚወስደው በአባቱ የወልቃይት-ጠገዴ፣ በእናቱ ደግሞ የሽሬ ተወላጅ የሆነው የ«ሪጅን አንድ» የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው በዓለም ስሙ «ዮሴፍ ዘለለው» (በበረሃ ስሙ ደግሞ «መኮንን ዘለለው») በመባል የሚታወቀው ግለሰብ ነው። መኮንን ዘለለው በአሁኑ ሰዓት በስደት በአሜሪካን አገር ይኖራል። ለመኮንን ዘለለው ከሕወሓት የተሰጠው ተልዕኮ፦ በሕዝቡ መሃል እየተዘዋወረ ሠቲት፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት እና አጎራባች ወረዳዎች የትግሬ ግዛት አካል መሆናቸውን፣ ሕዝቡም ትግሬ መሆኑን በመስበክ ማሣመን፣ የሚያምኑትን መመልመል፤ «ትግሬ አይደለንም» ያሉትን እና አጥብቀው የተከራከሩትን እየመዘገበ ለፈዳያን (ገዳይ ቡድኖች) ስማቸውን በማስረከብ ማስገደል ነበር። በዚህም መሠረት መኮንን ዘለለው ከላይ በተጠቀሱት ወረዳዎች እየተዘዋወረ፦ «ይህ መሬት የትግራይ መሬት ነው። እናንተም ከእንግዲህ ወዲያ የሰሜን ጎንደር ዐማራ ተወላጆች አይደላችሁም። በመሬቱ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ። እኛ ትግሬ አይደለንም፣ መሬቱም የትግራይ አይደለም የምትሉ ካላችሁ ደግሞ፣ የሕወሓትን ውሳኔ ጠብቁ።» የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጥ ነበር። ሆኖም ሕዝቡ ያላዳች ማመንታት የሰጠው መልስ «እኛ ዐማራዎች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም። የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት፣ እና የሠቲት ወረዳዎችም የትግራይ አካል ሆነው አያውቁም።» የሚል ነበር። «የሁለቱ ክፍለ ሀገሮች ማለትም፦ የትግራይ እና የጎንደር (ቤጌምድርና ሰሜን) የተፈጥሮ ወሰናቸው ተከዜ ነው። የትግራይ ግዛት ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም።» በማለት ታሪክ እያጣቀሱ ሞገቱት።
መኮንን ዘለለው ከሕዝቡ ያገኘውን ምላሽ ለአለቆቹ ሪፖርት አቀረበ። ሪፖርቱ ተልዕኮው ያልሰመረለት መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ፣ በወቅቱ የሕዋሓት ሊቀመንበር የነበረው ስብሐት ነጋ በብስጭት በመኮንን ላይ የስድብ ናዳውን በማውረድ ከሪጅን አንድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊነቱ እንዲነሳ አደረገው። ሕወሓቶች መኮንን ዘለለውን ባያስሩትም የተለያዩ ሥቃዮችን እንዲቀበል አደረጉት። ሕወሓትም በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ቂም ቋጠረ። ዕውነትን ጋሻ፣ ታሪክን ማጣቀሻ አድርገው የሞገቱትን ሰዎች እየለቀሙ አድነው ጨፈጨፏቸው። በዚህም መሠረት የትግሬ-ወያኔ ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ ተከዜን ተሻግሮ በቅድሚያ ከጨፈጨፋቸው የአገር ዘብ የነበሩ የወልቃይት-ጠገዴ የዐማራ ተወላጆች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1) ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
2) ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
3) ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
4) ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
5) አቶ ማሞ ዘውዴ፣
6) አቶ እንደሻው ታፈረ፣
7) አቶ አያሌው ሰሙ፣
8) አቶ በርሄ ጎይቶም፣
9) አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
10) አቶ  ልጃለም ታዬ፣
11) ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
12) ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
13) ወጣት ደረጀ አንጋው፣
14) ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
15) ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
16) ወጣት ታደለ አዛናው፣ እና
17) ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።
ከዚያን ወቅት ወዲህ የትግሬ-ወያኔ በአካባቢው ይኖሩ በነበሩ የዐማራ ተወላጆች ላይ በተከታታይ ከፈፀማቸው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፦
1) በ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን እና ከ፭፻ (አምሥት መቶ) በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው የትግሬ ተወላጆችን አሠፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ይገኙበታል።
2) ከ፲፱፻፹፰ እስከ በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ከ፫ (ሦሥት) ሺህ በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለው እና አሰድደው የትግሬን ገበሬ አስፍረውበታል።
3) ከ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. ጀምሮ በማይ ኅርገጽ፣ በቤት ሞሎ፣ በማይ ጋባ፣ በማይ ደሌ፣ በአንድ አይቀዳሽ፣ በእምባ ጋላይ፣ በትርካን፣ በቃሌማ፣ በእጣኖ፣ በመጉዕ፣ ወዘተርፈ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባርረው የትግሬ ተወላጆችን አስፍረዋል። በአጠቃላይ የትግሬ-ወያኔዎች ሰሜን ጎንደርን ከወረሩበት ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩት ፴፬ (ሠላሣ አራት) ዓመቶች በአካባቢው ለም መሬቶች ከ፫፻(ሦሥት መቶ) ሺህ በላይ የሚሆኑ የትግሬ ተወላጆችን አስፍረዋል።
ኃብት እና ንብረቶቻቸውን የተነጠቁ፣ እንዲሁም እንዲወድምባቸው የተደረጉ የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የሠቲት፣ እና የአካባቢው የዐማራ ተወላጆች መካከል ለመጥቀስ ያህል፦
1) የአቶ ዘነበ ሐጎስን ፬፻፶(አራት መቶ ሃምሣ) ያህል የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
2) የአቶ አባየው ቢያድግልኝን ከ፮፻(ስድስት መቶ) የማያንሱ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ሰውዬውን  ገድለዋቸዋል፤
3) የአቶ ገብረሕይዎት ኃይሌን ከ፹(ሰማንያ) በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
4) በ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. የአቶ አለባ ሕደጎን ከ፭፻ (አምሥት መቶ) በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ዘርፈዋል፤
5) የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀልን ፳፬(ሃያ አራት) በሬዎቹ አርደው ከ፱፻ (ዘጠኝ መቶ) መቶ በላይ ማድጋ እህል ወርሰዋል።
ከዚህ በታች የቀረበው ሠንጠረዥ ደግሞ ከሰሜን ጎንደር የዐማራ ተወላጆች መካከል በትግሬ-ወያኔ አማካይነት ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ የተገደሉ፣ የታፈኑ እና የደረሱበት ያልታወቁ ዜጎችን ዝርዝር በጥቂቱ መለክታል።
ተራ ቁጥር
ስም ከነአባት
ተራ ቁጥር
ስም ከነአባት
ተራ ቁጥር
ስም ከነአባት
1)
አበበ ይርጋ
2)
አበራ ኃይሌ
3)
አበራ ዓለማየሁ
4)
አበራ ገብረመስቀል
5)
አበራ  አስረስ
6)
አበራ ሐጎስ
7)
አበጀ ክፍሌ
8)
አባተ እሸቴ
9)
አባው ጠጅነህ
10)
አብርሃ አዳነ
11)
አብርሃ አርጉ
12)
አብርሃ ነጋ
13)
አብርሃ በላይ
14)
አቻምየለህ ሽታዬ
15)
አቸናፊ ጽጌ
16)
አደበ ዓለም
17)
አደራጀው ገብሬ
18)
አዲሱ አበበ
19)
አዲስ አብተው
20)
አዲሰይ ልጃለም
21)
አዳነ ደረሰ
22)
አዳነው ርስቴ
23)
አለባቸው ደፈርሻ
24)
አለበል ይርጋ
25)
አለኸኝ መሥፍን
26)
አለማው ታረቀ
27)
አለማይ ካሣ
28)
ዓለሙ ጌታቸው
29)
ዓለሙ ለገሠ
30)
ዓለሙ ፈንታይ
31)
ዓለማየሁ  አበጠለው
32)
አለነ ክንዲሽ
33)
አላቸው ልጃለም
34)
አላቸው ገብረመድኅን
35)
አማረ ፈንቴ
36)
አንገረብ ተሰማ
37)
አንዶም ካሣ
38)
አረጋ ወልዴ
39)
አረጋው አየነው
40)
አረፈዓይኔ መኮንን
41)
አረፈ በለጠ
42)
አረፈ ግደይ
43)
አስገዶም ጥሩነህ
44)
አስመላሽ ይገዙ
45)
አስማረው ግደይ
46)
አስመራው ወልዴ
47)
አስማረው አስረሴ
48)
አስማረው መለሰ
49)
አስረስ ታከለ
50)
አስፋው መንግሥቴ
51)
አስፋው ወርቁ
52)
አሸናፊ ወንዱ
53)
አታላይ አበራ
54)
አታላይ አማረ
55)
አታላይ ዘነበ
56)
አጥናፈይ ዓለማየሁ
57)
ዐወቀ ዘውዱ
58)
አየነው ሙሉ
59)
አየነው ርስቴ
60)
አየነው በየነ
61)
አያሁነኝ ወንዶሻል
62)
አያሌው ሰሙ
63)
አያና ገብሬ
64)
አዘነህ ልጃለም
65)
አዛናው ቸሬ
66)
አዛናው ይደግ
67)
አዛናው ጽጌ
68)
እንዳልካቸው ጠጆ
69)
እንደሻው ታፈረ
70)
እንግተይ አየልኝ
71)
እሪበይ ገብሩ
72)
እሸቴ አያልነህ
73)
እሸቱ መስፍን
74)
በየነ ፍሬይ
75)
በየነ አየልኝ
76)
በሪሁን ደስታ
77)
በዕዱ ወንድም አገኝ
78)
በላይ ሙሉ
79)
በላይ ታደሰ
80)
በላይ መኮንን
81)
በለጠ ዓለም መብራት
82)
በለጠው ተስፋዬ
83)
በልጤ ወንድም-አገኝ
84)
በራ የማነ
85)
በራ ወልደሥላሴ
86)
በርሄ ሐጎስ
87)
በሪሁን ይግዛው
88)
ቢያድግልኝ ዘውዴ
89)
ባሕታ ፈንታይ
90)
ባሕታ መኩሪያ
91)
ባሕታ ወንድምአገኝ
92)
ባሕታ ረዳ
93)
ባሕታ እርትብ
94)
ባሕታ መንግሥቱ
95)
ባየው ባሕታ
96)
ባየው ቢያረግልኝ
97)
ባየው ልጃለም
98)
ብሪሁን ይርጋ
99)
ብላታ አብርሃ
100)
ብርሃኔ ማሞ
101)
ብርሃኑ ዳኛቸው
102)
ብርሃኑ ሽታዬ
103)
ገብረሕይዎት ኃይሌ
104)
ገብረመድኅን የኋላ
105)
ገብረመድኅን ዘርፉ
106)
ገብረመስቀል ጥርፊነህ
107)
ገብረሥላሴ ረዳ
108)
ገብረሕይዎት ባሕታ
109)
ገብረሕይዎት ገዛኸኝ
110)
ገብረማርያም አረፈዓይኔ
111)
ገብሬ ሐጎስ
112)
ገረመው ዳኜው
113)
ገሪማ ተኽላይ
114)
ጉበን ፊያሃጸን
115)
ጉዎይ መብርሃቱ
116)
ጉዎይ አዳነ
117)
ጊፍታቸው ዳኘው
118)
ጌቱ ጠለለው
119)
ጌታቸው አብርሃ
120)
ጌታቸው ብዙነህ
121)
ጌታቸው ተገኜ
122)
ጌቴው ታምሬ
123)
ግደይ ካሣ
124)
ግደይ ማሙ
125)
ግንባይ ጌታሁን
126)
ግርማ ይደግ
127)
ግርማይ ትኩስ
128)
ግርማይ ጥቄ
129)
ጎይቶም ምኅረት
130)
ጎይቶም ሐድጎ
131)
ጎርፉ ገብሩ
132)
ጎሹ አሰፋ
133)
ጎሹ ትርፍነህ
134)
ደቢል ዘነበ
135)
ደቢል ተክለሃይማኖት
136)
ደገፋ ጎይቶም
137)
ደሣለኝ ዋርካው
138)
ደስታ ሰርጸ
139)
ዳኜው ሢሣይ
140)
ድራር ገሠሠው
141)
ሀብቱ ይርጋ
142)
ሀፍቴ ዘነበ
143)
ወግሃታይ መንበሩ
144)
ወረታ ገብሩ
145)
ወልዴ ኢዮብ
146)
ወልዴ የኔሁን
147)
ወንድም ፍስሃ
148)
ወንድም ጠለለ
149)
ወንድም ጠጋ
150)
ወንድምአገኘሁ ታረቀ
151)
ወርቅዬ ገብረመድኅን
152)
ወርቅነህ አታላይ
153)
ዋኘው መንበሩ
154)
ዘውዱ ሽባባው
155)
ዘውዴ ሢሣይ
156)
ዘለቀ ግርማይ
157)
ዘራይ መርሻ
158)
ዘሩ በላይ
159)
ሐጎስ ገብራይ
160)
ሐጎስ መንግሥቱ
161)
ሐጎስ ይስፋ
162)
ጣሌ ገብሬ
163)
ጣሰው አሰፋ
164)
ጤላ ኃይሌ
165)
ጥጋቡ መኳንንት
166)
ጥላሁን ተወልደ
167)
ጥላሁን ታደሰ
168)
ጥሩነህ መብራቱ
169)
ጫኔ ይርጋ
170)
ጫቅሌ ገበየሁ
171)
ጫሉ ይዘዘው
172)
የኋላሸት ዘለቀ
173)
የሻለም በሪሁን
174)
የሽዓለም ጽጌ
175)
ይበይን ገብረእግዚአብሔር
176)
ይደግ አየነው
177)
ይደግ አያሌው
178)
ይዘዘው  ገብረመስቀል
179)
ይላቅ ተዘራ
180)
ይርጋ ደምሰው
181)
ይስፋ ፋንታይ
182)
ከሰተ ይርጋ
183)
ካሱ ንጉሤ
184)
ካሂሱ ንጉሡ
185)
ካሣሁን ሲሣይ
186)
ካሣ መብራት
187)
ካህሱ ጌታው
188)
ክንፈ ከበደ
189)
ክንፈ ናሁ
190)
ለማ ታደሰ
191)
ሉሌ መሥፍን
192)
ሊላይ ሐድጉ
193)
ልዑል ገብረመስቀል
194)
ልዕልቲ ወንድምአገኝ
195)
ልጃለም በላይ
196)
ልጃለም ታዬ
197)
መብርሃቱ ይግዛው
198)
መብርሃቱ ገብረእግዚአብሔር
199)
መሓሪ አዱኛ
200)
መኮንን ለውጤ
201)
መኮንን አበራ
202)
መኳንንት ዋርካው
203)
መኩሪያ ገብረማርያም
204)
መንገሻ ሙሉጌታ
205)
መርዕድ ገብረሚካኤል
206)
መሣፍንት ዳኜው
207)
ሙኮጠይ ታደሰ
208)
ሙሉዓለም ዋርካው
209)
ሙላው ዞፌ
210)
ሙሉ አታላይ
211)
ሙሉ አማረ
212)
ሙሉ በርሄ
213)
ሙሉ ገብረኪዳን
214)
ሙሉነህ ደሞዜ
215)
ማለፊያ ጉዎይ
216)
ማሌ ዘነበ
217)
ማሙ  ዋርካው
218)
ማሙ ቸሬ
219)
ማሙ ታደሰ
220)
ማሙነህ ይደግ
221)
ማማይ አብርሃ
222)
ማማይ አየልኝ
223)
ማማይ አለዩ
224)
ማማይ በላይ
225)
ማማይ ሙሉ
226)
ማማይ ረዳቴ
227)
ማማይ ፈረደ
228)
ማማይ በላይነህ
229)
ማሞ ደስታ
230)
ማሞ ዘውዴ
231)
ምራጭ ተሰማ
232)
ሞላ ጠለለ
233)
ነጋ አስረስ
234)
ነጋ አለበል
235)
ነጋ ጌታሁን
236)
ነጋ ሐጎስ
237)
ነጋ ምትኩ
238)
ነጋ ተበጀ
239)
ንጉሡ አብርሃ
240)
ንጉሤ ቀለመወርቅ
241)
ንግሸት ሐድጉ
242)
ሰጠኝ እንዳለው
243)
ሰጠኝ ሽታዬ
244)
ሰረበ ረዳ
245)
ሲሣይ አበራ
246)
ሲሣይ ተስፋሁነኝ
247)
ስማቸው ማሙ
248)
ስማቸው ዓለሙ
249)
ሺሙዬ ደምሰው
250)
ሺሙዬ ማሙ
251)
ሺሙዬ አለሜይ
252)
ሻንቆ በለጠ
253)
ሽፈራው ውብነህ
254)
ሽፈራው ንጉሤ
255)
ሽፈራው ተስፋይ
256)
ሽሁን ኪዳኔ
257)
ፈለቀ ግርማይ
258)
ፈረደ ዘርዓይ
259)
ፈረደ ፍሉይ
260)
ፈንቴ ገብራይ
261)
ፈንቴ ዘነበ
262)
ፋንቱ ሲሣይ
263)
ፋንታዬ አየልኝ
264)
ፍሬይ ተወልደ
265)
ፍታለው ታፈረ
266)
ጽይተይ አብርሃ
267)
ቁዊ ተዘራ
268)
ረዳኢ ለማ
269)
ርስከይ መለሰ
270)
ርስከይ ምንተስኖት
271)
ርስከይ ይልማ
272)
ርስከይ ኃይሌ
273)
ሮስኬ ማንጆስ
274)
ተበጀ መለሰ
275)
ተበጀ በቀለ
276)
ተገኘ ነጋ
277)
ተገኘ ደምሴ
278)
ተካልኝ አበበ
279)
ተካልኝ መንግሥቱ
280)
ተሰማ አብቅህለው
281)
ተሰማ ፍሬይ
282)
ተስፋ ፀጋዬ
283)
ተስፋይ አብርሃ
284)
ተስፋይ አጽብሃ
285)
ተስፋይ መኮንን
286)
ተስፋይ ኃይሉ
287)
ተሻገር ገብረመድኅን
288)
ተሾመ ፈረደ
289)
ተሾመ ጠለለ
290)
ታደለ አባተ
291)
ታደሰ ከሺ
292)
ታፈረ ሊላይ
293)
ታገል ተድላ
294)
ቶጋ ተገኘ
295)
ቻላቸው አበረ
296)
ቻላቸው ታደለ
297)
ቻላቸው ታደሰ
298)
ኃየሎም ይርጋ
299)
ኃይሉ ልዩነህ
300)
ፀጉ ዘነበ
301)
ፀጋዬ አበበ
302)
ፀጋዬ የኔሁን
303)
ፓስተር በለጠ ተስፋይ
ይህ እንግዲህ በግልጽ መረጃ የተገኘላቸው ናቸው። በአጠቃላይ ከ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. ጀምሮ በሰሜን ጎንደር የትግሬ-ወያኔ በጅምላ የጨፈጨፋቸው ዐማራዎች ቁጥር ከ፳(ሃያ) ሺህ የማያንስ እንደሆነ የአካባቢው ተወላጆች ይመሠክራሉ። ከዚህ በተጨማሪም በሰሜን ጎንደር አካልነት ከሚታወቁት የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የሠቲት እና አጎራባች ወረዳዎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማራዎች ከአፅመ-ርስታቸው ተፈናቅለው በገዛ አገራቸው ስደተኞች ሆነዋል፣ አካባቢውም በሠፋሪ ትግሬዎች ተወርሯል።
በአሁኑ ወቅት የእነዚህ በግፍ በትግሬ-ወያኔዎች ደማቸው የፈሰሰው ወገኖቻችን ደም ይጣራል፣ በገዛ አገራቸው ሥደተኛ የሆኑት ወገኖቻችንም የድረሱልን ጥሪያቸውን ያሰማሉ። ዐማራው ዘሩ እየጠፋ ነው። ይህ ሁሉ ሲፈፀም እጅን አጣምሮ በመቀመጥ የሚመጣ መፍትሔም የለም። ስለሆነም ችግሩ መኖሩን አምኖ ተቀብሎ ወገብን ጠበቅ አድርጎ ለኅልውና መታገል ይገባል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የዐማራው ደም የውሻ ደም ሆኖ አይቀርም!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

Thursday, July 31, 2014

የተደራጁ ወንበዴዎች ለመፍጠር እየፈለጉ ያሉትን ብዥታ ለማጥራት -ከዳንኤል ተፈራ

July31/2014
10150630_609195442498727_1046966781_nባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በጣም ወሳኝ የሆነ ስራ ሲሰራ ነበር፡፡ እሱም ውህደት ነው፡፡ የአንድነት/መኢአድ ውህደት ወሳኝና መሰረታዊ ድርድሮችን አልፎ የቅድመ ውህደት ፊርማው ከተቀመጠም ከወር በላይ ሆነው፡፡ከፊርማው በኋላ ውህደት አመቻች ኮሚቴ ተዋቅሮ በአጭር ጊዜ ነገሮችን መልክ ለማስያስ የቻለ ሲሆን ውህደቱም የሁለቱ መስራች የጉባዔ አባላት በተገኙበት ነሐሴ 3 እና 4 ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ታዲያ ከመስራች ጉባዔው አስቀድሞ ሁለቱ ፓርቲዎች በተናጠል ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የውህዱን ፓርቲ ደንብና ፕሮግራም፤ ለውድድር የሚቀርብ እጩ ፕሬዘዳንት መምረጥ፣ አዲስ ስያሜ በመጠቆም እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት ይጠናቀቃል፡፡ በነገራችን ላይ የተናጠሉ ጉባዔ ስራውን የሚጀምረው አዲሱን የጋራ ደንብ በማፅደቅ ይሆናል፡፡ አጠቃላይ ውህደቱን ተቀበለው የሚባለው ደንብና ፕሮግራሙን ሲያፀድቅ ይሆናል፡፡
በአንድነት ፓርቲ በኩል በምክር ቤት ደረጃና በተለያዩ መዋቅሮቹ የሀሳብ ክርክር ማድረግ የተለመደ እንጅ ብርቅ አይደለም፡፡ የሃሳብ ክርክር ሲደረግ ‹‹ተባሉ፣ ምናምን›› እያሉ የሚጮሁት ከክርክሩ ትርፍ ለመሸመት የተሰለፉ ባእድ ሃይሎች እንጅ አንድነቶች አይደሉም፡፡ ነገዳቸው የሃሳብ ክርክር ከማውቀው ጎራ ስለሆነ የአንድነት አባላት የሃሳብ ፍጭት ሲያደርጉ ይደነግጣሉ፡፡ በአንድነት በኩል እጩ ፕሬዘዳንቶችን አስመልክቶም የተለመደው ክርክር ተደርጎ፤ እጩ ፕሬዘዳንቶቹ ወደ ጠቅላላ ጉባዔ ሄደው ከሦስቱ አንዱ እንዲመረጥ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድምፅ ተወሰነ፡፡ የቀረቡት እጩ ፕሬዘዳንቶች ከታወቁ በኋላም ደጋፊዎቻቸው እከሌ ቢመረጥ ይሻላል የሚል ሀሳብ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ እኔም እከሌ ቢመረጥ ፖለቲካውን የተሻለ ያንቀሳቅሰዋል የሚል መብት አለኝ፡፡ ይህንን መብት የሰጠኝ ማንም ሳይሆን አንድነት ነው፡፡
ሀቁ ይሄ ቢሆንም የአንድነት ወገን ያልሆኑ ስማቸውን የደበቁ ወሮበላ ተላላኪዎች ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም የአለቆቻቸውን ትዕዛዝ ለማስፈፀም መንፈራገጣቸው አልቀረም፡፡ ዘመቻ ከተከፈተባቸው መካከል ደግሞ አንዱ እኔ መሆኔ ፈገግ ያሰኘኛል፡፡ ብዥታውን ማጥራት ያስፈለገኝም ለምን ስሜ ተጠቀሰ ብየ ሳይሆን የሀሰት ዘመቻውን አንድምታና ከየት አቅጣጫ እንደተሰነዘረ ለመጠቆም ነው፡፡ ዘመቻው የውሸት ስሞችን በመጠቀምና ማስጃ አልባ የተቀነባበሩ ስድቦችን በማዥጎድጎድ ብዥታ መፍጠር ነው፡፡ በተለይም ስርዓቱ ምንደኛ የሆኑ ተላላኪ ግለሰቦች ‹‹አሉላ እንደገና፣ ሰለሞን ሳልሳዊ፣ የፍቅር ቃልና አፄ ልብነድንግል›› የሚሉ የተልኮ ስሞችን በመጠቀም ውህደቱ ከመደረጉ በፊት ክፍፍል ለመፍጠር ኢህአዴጋዊ ተልዕኮ ተሰጥቷዋቸው እየባዘኑ ይገኛሉ፡፡ አንድነት አበቃለት እያሉ ስማቸውን ደብቀው እንደተራበ ቁራ ያንቋርራሉ፡፡ እነዚህን ከሙታን የሚለያቸው በድን ተንቀሳቃሽ መሆናቸው ነው፡፡ ህሊናቸውን የሸጡ ርካሽ ፍጡራን ናቸው፡፡
ዋናው ቁምነገር ዘመቻው ለምን ተከፈተ የሚለው ነው፡፡ የሚጠበቅም ነበር፡፡ ዘመቻው በተለይም በእኔና ጓዶቼ ላይ የተከፈተው ስለለውጥ፤ የተቃዋሚ ጎራውን የማይናድ መሰረት ስለማስያዝና የተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ስለተናገርን ብቻ ነው፡፡ ስለሰራን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መስራትን ደግሞ የአንድነት ልጆች ይደግፉታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ የሚቃወመው ሃይል ‹‹ተቃዋሚው ማንሰራራት የለበትም፤ እግር ማውጣት የለበትም›› ብሎ የሚያምነው ኢህአዴግ ብቻ ነው፡፡ የስም ማጥፋት ዘመቻው በቀጣይ አመት የሚካሄደው ምርጫ ላይ የሚኖረንን ተሳትፎና ትግል አጋጣሚውን ተጠቅሞ የመምታት ነው፡፡ እነዚህ ከላይ የተቀስኳቸው የሀሰት ስም ተጠቃሚ ባንዳዎች ሀብታሙ አያሌው ላይ ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍተው ነበር፡፡ ስም በማጥፋት እንደማይበገር ሲያውቁ አሰሩት፡፡
አንድነት ካቀረባቸው ሦስት ጠንካራ እጩዎች መካከል የጠቅላላ ጉባዔ ተሳታፊው አንዱን ይመርጣል፡፡ ዋናው የሂደቱ ዴሞክራሲያዊ መሆን ነው፡፡ ኢንጅነር ግዛቸውና አቶ ትዕግስቱ ለአንድነት እዚህ መድረስ ያደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦና የከፈሉት ዋጋ ሳይዘነጋ ነገር ግን አሁንም የእኔ እምነትና ፍላጎት ሀቅን መካድ ስለማይቻል ለአንድነት ፓርቲ አሁን ያለበት ከፍታ ላይ መድረስ በላይ ፈቃዱ ዋናው ስለሆነ፤ ትግሉን ወደ ህዝቡ ለማውረድና ከቢሮ ለማውጣት በነበረው ትንቅንቅ ላይ እውቀቱን፣ ገንዘቡንና ጊዜውን ያለ ምንም ስስት ሲሰጥ ስላስተዋልኩ፤ በላይ ፍቃዱ የሚታወቀው ሀሳብ በማመንጨትና ያ ሀሳብም ተግባራዊ እንዲሆን ሳይደክም በመስራት ስለሆነ፤ ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት›› የሚለው ወሳኝ ህዝባዊ ንቅናቄ ስያሜ በበላይ በኩል የቀረበ እንደነበር ስለማውቅ እንዲሁም በላይ ፈቃዱ ፓርቲያችን የማተሚያ ማሽን ሊኖረው ይገባል የሚል ሃሳብ በማቅረብና በመተግበር ውጤት ያሳየም በመሆኑና በአጠቃላይ የጀርባ ሞተር ሆኖ የቆየ ውድ የአንድነት ልጅ ነው ብየ ስለማምን ለበላይ ድጋፌን እሰጣለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ግልፅ እምነቴ በድብቅ ስሞች ስም ለማጉደፍ በሚሯሯጡ በገዥው ፓርቲ ምልምሎች በኩል የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፈትብኝ አድርጓል፡፡ ልብ በሉ ‹‹ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው›› ነውና በወሬኞች ላለመፈታት እንጠንቀቅ፡፡ ስም አጥፊዎቹ የአንድነት ልጆች ቢሆኑ ኖሮ እንደዘረዘሩት የሀሰት ውንጀላ አንድ ቀን አናድርም ነበር፡፡ የውሸት ስም መጠቀም ሳያስፈልጋቸው ቢፈልጉ ፕሬዘዳንቱ ጋ አሊያም የምክር ቤት ሰብሳቢው ጋ በማምጣት ባቀረቡ ነበር፡፡ አድናቆቴ ከፍ ይል የነበረውም ይህንን ማድረግ ቢችሉ ነበር፡፡ አሁንም እስከነፃነት ትግሉን እንቀጥላለን፡፡

የአዲስጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ተጨማሪ የ5 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባት

July31/2014
• መኖሪያ ቤቷ በፖሊስ ተበርብሯል

ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአንዋር መስጂድ በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የታሰረችው የአዲስጉዳይ መጽሔት ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድ ሐሙስ ሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም ሜክሲኮ በሚገኘው በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምድብ ችሎት ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ቀርባለች።

ምርመራውን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ባለፈው ሳምንት የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት ወደአዚዛ መኖሪያ ቤት ተጉዞ ብርበራ ማድረጉ ታውቋል። በዚህ ብርበራ ፖሊስ አዚዛን በጥርጣሬ ከያዘበት ጉዳይ ጋር ተያያዠነት ያለው ማስረጃ እንዳላገኘ ነው ፎቶ ጋዜጠኛዋ የተናገረችው።

ጉዳዩን በማጣራት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ክፍል አዚዛን ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ያቀረባት ሲሆን ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችለው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን አምስት ቀን ብቻ በመፍቀድ ለማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አዚዛና ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች እንዲቀርቡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዕለቱ የተጠርጣሪዎቹን የፍርድ ሂደት ለመከታተል በርካታ ግለሰቦችና ቤተሰቦቻቸው የተገኙ ቢሆንም ችሎቱ ግን በዝግ ተካሂዷል።
ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሰየማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ችሎት አርፍዶ ነበር የተሰየመው።ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሲጠይቅ በፍርድ ቤቱ ከመፈቀዱ በቀር አዚዛ በችሎቱ የተጠየቀችው ነገር እንዳልነበር ነው የተናገረችው።

በስፍራው ለስራ ከመገኘቴ በቀር በፖሊስ ሊያሳስረኝ የሚያስችል ምንም የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም የምትለው ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሃመድ ምንም አይነት ጥፋት ለመፈጸሟ ማስረጃ ባይቀርብባትም ፖሊስ ለቀጣይ 5 ቀናት በእስር ላይ እንድትቆይ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።

አዚዛ እስካሁን በፖሊስ የቀረበባት እና የተጠረጠረችበትን ጥፋት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመኖሩ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው የጊዜ ቀጠሮ በነጻ ሊያሰናብታት አለያም በዋስ ሊፈታት እንደሚችል ያላትን ተስፋ ለባልደረቦቿ ተናግራለች።

አዚዛ በሚቀጥለው ቀጠሮ ፍርድ ቤት ስትቀርብ የእስር ቆይታዋ 18 ቀናት ይሆናል ማለት ነው።