Thursday, December 5, 2013

የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ=በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

December 5, 2013 
የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ፍቅርና አንድነት ትምህርት ሰጥቶ ይሆን? በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ልዩ የሆነ ትኩረት እንዲሰጡትና ለወገኖቻቸው የማያቋርጥ ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡

ባለፉት በርካታ ሳምንታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ባለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስል መታየት መጀመሩን ተከትሎከአውስትራሊያ እስከ አሜሪካ ባሉ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ እና የልብ ስብራት በማስከተሉ ምክንያት በየአካባቢያቸው ባሉ የሳውዲ አረቢያ ቆንስላዎችና የዲፕሎማሲ ማዕከላት በሮች ላይ ፊት ለፊት በመሰለፍ በግንባር በመግጠም ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጵያዊ የተቃውሞ ወኔ የመብት ረጋጮችን የሳውዲ አረቢያ ገዥ ባለስልጣኖች በማሸማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ6 – 7 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን/ት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የሳውዲ አረቢያ ገዥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸመ ያለውን ህገወጥ እርምጃና የሰብአዊ መብት እረገጣ በአስቸኳይ እንዲያቆም በመጠየቅ በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ወገኖቻቸው ጋር የማያቋርጥ ትብብርና ወገናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአደባባይ በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከአትላንታ እስከ ሲያትል ከተሞች በመሰለፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች በመውጣት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

 የሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በየደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ባነሮችን በመያዝ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ!” በማለት ተቃዎሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ በአስተማማኝ መረጃ ላይ ተደግፎ የቀረበ በመሆኑ ሊካድ የሚችል ጉዳይ አይሆንም፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ ዴሴምበር 1/2013 ባወጣው ዘገባ መሰረት “የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ሠራተኞች ላይ የኃይል እርምጃን በመውሰድ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞችን የአካል ጉዳት ሰለባ እንዲሆኑ አደርጓል፣አንዳንዶችንም ገድሏል፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ኢትዮጵያውያን/ት ደግሞ ያለበቂ ምግብና መጠለያ አቅርቦት በጊዚያዊ የእስር ቤት ማዕከሎች አጉሮ ይገኛል“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ በወገኖቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በመመልከት በተግባር እያሳየ ያለውን ንዴትና ቁጣ ሶስት ዋና ዋና ነገሮች በትክክል ይገልጹታል፡፡ 1ኛ) የሳውዲ አረቢያ የመንገድ ላይ ዘራፊዎች እና የፖሊስ ሌቦች እንዲሁም ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኛ ዜጎችን ከየቤታቸው በማስወጣት በየመንገዱ በመጎተት በቃላት ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ ጭካኔና አረመኔነት በተመላበት ሁኔታ ሲደበድቡ፣ ሲዘርፉና ሲያስሩ በመታየታቸው፣ 2ኛ) የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል የእራሱ ፖሊሶችና ሁከት ፈጣሪዎች በእብሪት ተነሳስተው በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ ያለምንም ማቋረጥ ጥቃት ሲሰነዝሩ እያየ ምንም ነገር ሳያደርግ በማንአለብኝነት መመልከቱ፣ 3ኛ) በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከመሰሉ ገዥ የሳወዲ አረቢያ አካል ጋር በመሞዳሞድ የገንዘብ እርዳታ ስለሚያገኝ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ደካማነትና የእግር ላሽነት ባህሪ በግልጽና በዓለም የአደባባይ መድረክ ላይ በማሳየት ላይ በመገኘቱ የሚሉት ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና በአትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል እየደረሰ ባለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ ሁለት የማይገናኙና ተጻራሪ የሆኑ ምላሾን ሲያንጸባርቁ ይታያሉ፡፡ በአንድ በኩል በውጭ አገር ያለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ስደተኛ ሠራተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየደረሰ ባለው መከራ እና ስቃይ ከወገኖቹ ጎን በጽናት ሲቆም በተጻራሪው ገዥው በአዲስ አበባ የሚገኘው አካል ደግሞ ጠንከር ያለ መግለጫ ከማውጣት ወደኋላ ያፈገፍጋል፣ እንደ አሉሚኒየም ብረት ወደኋላ ይለመጣል፣ የሳውዲን ገዥ አካልን ጫማ ለመላስ ወደ ተረከዙ ያጎነብሳል፣ እንዲሁም አምባገነኑን አረብ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ በአጭሩ ሎሌነቱን በይፋ አሳይቷል!፡፡ ከወባ ትንኝ ተመራማሪነት በፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሸሙትና እ.ኤ.አ ከ2015 አገራዊ “ምርጫ” በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይጠቀልላሉ ተብለው የሚጠበቁት ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖችን ውሳኔ እና ህገወጥ ስደተኞችን የማባረር ፖሊሲያቸውን ኢትዮጵያ እንደምታከብር በድፍረት ለብዙሃን መገናኛ ይፋ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በተደረገው የዜጎች ህገወጥ አያያዝ ስሜታቸው የተጎዳ መሆኑን ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር በቀልድ መልክ ገልጸው ይደልዎ ብለዋል፡፡ በዲፕሎማሲያዊ በእራስ መተማመን መልክ አድሃኖም “ይህ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡

እርሳቸውና ገዥው አካል ነገሮችን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዳደረጉ በሚመስል መልኩ አድሃኖም “ዜጎቻችንን ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“ በማለት የምጸት ጩኸት አሰምተዋል፡፡ ማዘናቸውን የገለጹበት ሁኔታ ከልብ ያልሆነ፣ ለታይታ እና ለይስሙላ የተደረገ፣ የባለስልጣንነት ሞገስ የሌለውና እርባናየለሽ ነበር፡፡ እንዴት አንድ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጠ ባለስልጣን የእራሱን ዜጎች ለሚያዋርድ የሌላ አገር ፖሊሲ “ክብር” ይሰጣል? እንዴት አንድ ሰው የአንድን በባዕድ አገር የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች አስገድዶ የሚድፍር፣ የሚገድል፣ ሰውነትን የሚበጣጥስ፣ የሚያሰቃይና ተጠርጣሪ ነው በማለት ያለፍርድ የሚገድል ኃይል በእራሱ አስተሳሰብ በመመራት “ተቀባይነት የለውም” የሚለውን ትርጉምየለሽ የዲፖሎማሲ ቃል ይመርጣል? እንዴት አንድ ሰው በትክክለኛው የዲፕሎማሲያዊ ንዴትና ቁጣ ኖሮት በህጋዊ መንገድ ጉዳዩን ለመከታተል ሳይሞክር “ስሜቴ ተጎድቷል” እንዲሁም “አዝኛለሁ” ሊል ይችላል? ስዕል የአንድ ሺ ቃላትን ያህል የመናገር ኃይል ያለው መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያዎች የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስሎች የዲያስፖራውን ቁጣ የመቀስቀስ ኃይል ነበራቸው፡፡

 በቀላሉ ሊታይ የማይገባው እውነታ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመው አሳንሶ የማየት፣ የማዋረድ፣ ማሰቃየትና ሰብአዊ መብትን መርገጥ በተመሳሳይ መልኩ በተራው ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኢትዮጵያው ገዥ አካል ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካል ነጻውን ፕሬስ በማሽመድመድ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የሰብአዊ መብት እረገጣ ከህዝብ ዕይታ ለመደበቅ ያደረገው ጥረት በአብዛኛው ስኬታማ ቢሆንም ሁሉንም ደብቆ ለማስቀረት ግን አልተቻለውም፡፡ ብዙ አስደንጋጭ የፎቶግራፍ ምስሎች በማስረጃነት ቀርበዋል፣ እነዚህም የፎቶግራፍ ምስሎች የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ከፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ የበለጠ የኢትዮጵያ ገዥ አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የፈጸመው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ ፎቶግራፍ የበለጠ አስደንጋጭ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በኖቬምበር 2013 የተፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ በኢትዮጵያ ገዥው አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኦክቶበር 2013፣ በኖቬምበር 2012፣ በዴሴምበር 2011፣ ወዘተ በተመሳሳይ መልኩ ተፈጽሟል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ገዥው አካል እስረኞችን ከህግ አግባብ ውጭ አስገድዶ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ያደረገውን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዘገባው “በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት እስረኞች በማያቋርጥ ሁኔታ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይደበደባሉ፣ በቦክስ ይነረታሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ ጥቂቶቹ በሚያሰቃይ ሁኔታ እጆቻቸውን ከኩማዎቻቸው ላይ በማንጠልጠል፣ ወይም ደግሞ እጆቻቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ አድርገው በማቆም ማሰርና ለብዙ ጊዜ እየተደበደቡ እንዲቆዩ ማድረግ“ አካቶ አቅርቦታል፡፡ ዋናው ከክስተቱ የተማርኩበት አጋጣሚ፣ የነቃና የተበሳጨ ህዝብን መመልከት፣ እውነት ለመናገር ለእኔ አሁን ባለው የሳውዲ አረቢያ ሁኔታ ዋናው “የተማርኩበት አጋጣሚ” ብዬ የምወስደው አብዛኛው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰባስቦ ተቃውሞውን በመግለጽ እረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህ አይነት ቀልጣፋ በሆነ መልክ፣ ኃይልና አስደናቂ ፍላጎት ስልታዊ በሆነ መልክ ዓለም አቀፍ የቁጣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አይችልም የሚለውን የቀድሞ እምነቴን እንድሰርዝ አድርጎኛል፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር ይህ ድርጊት ለእኔ “ይበል” የሚያሰኝ ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አይቻለሁ፣ ከተለመዱት የመብት ተሟጋቾች በስተቀር አብዛኛው ለእኔ ዝምተኛ ብቻ ሳይሆን የተኛም ጭምር መስሎ ይታየኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሚያስደንቅ ሁኔታ ግዙፉን የኢትዮጵያን ዲያስፖራ በንቃት ሲሳተፍ ተመልክቻለሁ፡፡ ወንዶች ሴቶች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች በሳውዲ አረቢያ በወንድሞቻቸውና በእህቶቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ስቃይና የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በመቶዎችና በሺዎች በመሆን እየወጡ ከጎናቸው ተሰልፈዋል፡፡ ይህን ግዙፍ ዲያስፖራ እንዲነቃ ያደረገው ምንድን ነው? እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ትልቁ ስጋቴ በሳውዲ ያለው ቀውስ ካበቃ በኋላ ይህ ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ተመልሶ ይተኛ ይሆን የሚለው ነው፡፡ የሁላችንም ትምህርታዊ አጋጣሚዎች፣ የኢትዮጵያ ስደተኛ ሰራተኛ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በደርሰባቸው የሰብአዊ መብት እረገጣና ማሰቃየት የኢትዮጵያ ገዥው አካል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ልዩ የሆኑ ትምህርታዊ አጋጣሚዎችን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “ትምህርታዊ አጋጣሚ” የሚለውን ሀረግ ለብዙሀን ትምህርት፣ ለህዝቦች መነሳሳትና ለግለሰቦች በንቃት መሳተፍን ሊያመጣ የሚያስችል በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ልዩ ድርጊት በማለት ተርጉሜዋለሁ፡፡ ከዚህ በመቀጠል የሚቀርቡትን ጥቂት የማስተማሪያ እና የመማሪያ ትምህርቶች የትርጉም ቅርጽ ከግንዛቤ በማስገባት ማስተላለፍ የምፈልገው ዋናው መልዕክት ቀውስ በደረሰ ጊዜ ብቻ የሚወረወር ምላሽ ነጻነትን፣ ዴሞክራሲን ለመጎናፀፍ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር ስኬታማ እና ለድል የሚያበቃ ስሌት አይደለም፡፡ በሳውዲ አረቢያ እንደደረሰው ቀውስ ሁሉ በሌሎችም ትክክል ናቸው ብለን በምናምንባቸው ጉዳዮች ሁሉ ልዩ የሆነ ዓለምአቃፋዊ ትብብር፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና መነሳሳትን በተረጋጋ ሁኔታ ማንጸባረቅ ይጠበቅብናል፡፡ በሳወዲ አረቢያ ቀውስ ምክንያት የታየውን የመነሳሳት “አዚም” ደግመንና ደጋግመን ማሳየት ይኖርብናል፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት በቋሚነት ለሰብአዊ መብት መከበር መሟገትና መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ በኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ መነጽር መመልከት፣ ተራ ንግግር እራሳችንን ከስሜታዊነት፣ ግንፍልተኝነት እና ከቀውስ ለመውጣትና የእራሳችንን እጣ ፈንታ እራሳችን ወሳኝ እንድንሆን ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” ምናባዊ ቅርጽ የሚል ላስተዋውቅ፡፡ የነቃውን ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለዘለቄታው እንደነቃ ለዘላለሙ ጠንቃቃ ተመልካች ሆኖ አንዲቀጥል ልዩ ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ያሉ ችግሮችና ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ እናውቃለን፣ ጥቂቶች በጣም ቀላል ነገሮች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መፍትሄ ለማግኘት የበለጠ አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ በግልጽ በመተማመን እና በመወያየት ችግሮችን ካልፈታናቸው በስተቀር ታላቁን የነቃ የዲያስፖራ እንቅስቃሴ ወደኋላ በመመለስ እንዲተኛ ማድረግ ያስችላሉ፡፡ ከአንድ ቀውስ ወደሌላ ቀውስ መሸጋገር እኔ በበኩሌ ያመኛል፣ ይደክመኛልም፡፡ የዲያስፖራው ማህበረሰብ እርስ በእርስ እንዲዋደድ፣እንዲደራጅ፣ እንዲታደስ እና ለውጤት እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አለብን፡፡ ከእራሳችን እና ከእያንዳንዳችን ጋር ንግግሮች ያስፈልጉናል፡፡ “በኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እመለከታለሁ፡፡ ንግግር ለማድረግ መስታወቱን ከግድግዳው ጋር እሰቅለዋለሁ፡፡ እኔን ወደኋል ይመለከተኝ እና እንዲህ ይላል፣ ሁላችሁም ማድረግ ትጀምራላችሁ ነገር ግን አትጨርሱትም፡፡ መስታወቱ እንዲህ በማለት ያስታውሰናል፣ “በቅርቡ በህይወት የተለዩት የኢትዮጵያ ገዥ አካል መሪ እንዲህ ብለው ነበር ’የአትዮጵያ ዲያስፖራዎች ብዙ ነገሮችን ይጀምራሉ፣ የጀመሩትን ግን በፍጹም አይጨርሱትም፣ ታዲያ ስህተት ተናግረዋልን?’” ጥያቄውን ላለመመለስ ቃላትን ለመፈለግ እሞክራለሁ፡፡ “እውነት ለመናገር ብዙ ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን፣ ነገር ግን በጣም ጥቂቶችን ብቻ ለውጤት እናበቃለን፣ ከእኔ የግል ተሞክሮ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ፣ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ትግል በንቃት ስቀላቀል ያየኋቸው፣ የሰማኋቸው፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተሳተፍኩባቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ወይም የአድቮኬሲ ቡድኖች፣ ግብረ ኃይሎች፣ ኮንፈረንሶች፣ ፎረሞች፣ የምክክርና የውይይት ቡድኖች፣ ቴሌኮንፈረንሶችና የግል ስብሰባዎች፣ ወርክሾፖች፣ ስምምነቶች፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና ሲምፖዜሞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ አንዱም ፍሬ አፍርቷል ብየ ለመናገር አልደፍርም“:: ወዲያዉኑ እራሴን በፍጥነት አርማለሁ፡፡ “አንድን ነገር በግማሽ አሳክተናል፣ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ኤችአር/HR 23ን ማን ይረሳዋል (ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ተጠያቂነት ድንጋጌ)፣ አዎ! ያ ታላቅ ትምህርታዊ አጋጣሚ ነበር፡፡ ያ የህግ ሰነድ በቅርቡ በህይወት ለተለዩት ጠቅላይ ሚኒስትር የእራስ ምታት፣ የልብ ስብራት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጀርባ ውጋት፣ የጥርስ ቁርጥማት እና የጆሮ ህመም ሆኖባቸው ነበር! ኤችአር 2003 የተለያየ አመለካከት የነበራቸውን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ወደ አንድ እንዲመጡና ተቀራርበው ዓላማቸውን በጋራ እንዲያሳኩ ለማድረግ አስችሎ ነበር:: መስታወቱ አቁአረጠኝ፡ “እንዲህ ነው እንጂ! ሁላችሁም አንድ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጠንካራ መሰረት ያለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የዲያስፖራ ማህበረሰብ ድርጅት ማቋቋም ትችላላችሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ለማሰቃየት፣ ከህግ ውጭ ለሚፈጸም ግድያ፣ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ማዋል እና እስራቶች፣ ድብደባዎች እና ለምርጫ ድምጽ ስርቆት የተለየ ትኩረት በመስጠት የማያምን ማን አለ?” ግልጽ የሆነውን መልስ ላለመስጠት ወሰንኩ፡፡ አንድ ነገር ስንጀምር ወደ ስኬታማነት ልናመጣው ይገባል ወይም ደግሞ የፈለገውን ጊዜ ቢውስድም እየሞከርነው መቀጠል ይኖርብናል፡፡ ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም አንድን ነገር ለመቃወም በንዴት በስሜታዊነት ትነሳላችሁ፡፡መስታወቱ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፣ “በኢትየጵያ ያለው ታማኝነት የጎደለው ገዥው አካል አንድ ነገር ሲያደርግ ወይም ሳያደርግ ሲቀር ሁላችሁም ሁልጊዜ በንዴትና በስሜታዊነት ምላሽ ለመስጠት የምትሞክሩት ለምንድን ነው?“ በፍጥነት የሳውዲ አረቢያን ሁኔታ ሃሳብ መጣብኝ፡፡ “ስሜታዊነት መሆን ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ሰው መሆንና ስሜታዊ አለመሆን ማለት ሮቦት መሆን ማለት ነው፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሳውዲ አረቢያ ከሰው በወረደ መልክ ግፍ ሲፈጸምባቸው እያየን እና እየሰማን ለምንድን ነው የማንናደደውና ከቁጥጥር ውጭ የማንሆነው?“ መስታወቱ በጥንቃቄ መጠየቁን ይቀጥላል፣ “ከተነፈስክ በሁላ ንዴት ሲበርድልህ የሚተርፍህ ምንድን ነው? ተስፋ መቁረጥ፣ በጣም ስሜታዊ መሆን፣ ማዘን? ኃይል የለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ ምንም ነገር ያለማድረግ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህን? ወይም ደግሞ እንደገና ለመደራጀትና ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ያለ የሌለ የፈጠራ ኃይልህን ትጠቀማለህ? እራሴን በመነቅነቅ ሀሳቤን አንጸባርቃለሁ፡፡ “ምንጊዜም ቢሆን ንዴት በመጨረሻው ተፈጻሚነት እንዳይኖርና ሽባ ሆኖ ያስቀራል፡፡ በምንናደድበት ጊዜ የምናባክነው ኃይል ወደ ረዥሙና ቀጣይነት ስላለው የአድቮኬሲ እና ድርጊት በአወንታዊነት ማዋል አለብን::” ንዴታችን ለምክንያታዊነት፣ በስሌትና በጥቅል ታስቦበት ለሚሰራ ተግባር መንገድ መስጠት አለበት፡፡ ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ቀውሶችን የመቃወም ዝንባሌ ታሳያላችሁ፣ ነገር ግን ከእነዚህ ያላነሰ ጠቀሜታ ላላቸው ሆኖም ግን ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን ችላ ትላላችሁ:: መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “ባለፈው ዓመት በርካታ አስደንጋጭ ቀውሶች በግልጽ ለመውጣታቸው ምስክር ናችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ገዥ አካል በሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሰብአዊ መብት መርገጥና ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ ጥንታዊውንና የተከበረውን የኢትዮጵያን የኃይማኖት መሬት የዋልድባን ገዳም ዓይን ባወጣ መልኩ ገዥው አካል ለውጭ የሸንኮራ አገዳ አልሚዎች ማስረከቡ ይታወሳል:: በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል በማፈናቀል የዘር ማጽዳት ዘመቻ መፈጸሙ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው::” መስታወቱ ቀጥሏል፣ “በርካታ ዝቅተኛ ገጽታ ያላቸው ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የአውዳሚነት ባህሪ ያላቸው እየተከናወኑ ያሉ ቀውሶች አሉ፣ የገዥው አካል “የሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት” ማስመዝገብ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም በአሁኑ ጊዜ ወደ አስር ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን/ት በረሀብና ቸነፈር የህይወት አጣብቂኝ መካከል ወድቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹና በመጀመሪያዎቹ 1980ዎቹ እንደነበሩት ዓመታት ዓይነት ረሀብ የማይታየው በዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ምክንያት ነው፡፡ በጎረቤት አገሮች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮያውያን/ት ቁጥር በየዓመቱ በመቶዎችና በሺዎች እየጨመር በመሄድ ላይ ይገኛል፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ቀውሶች ይታያሉ፡፡ የሙስና ቀውስ እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራት ደካማ መሆን እና የአገልግሎቱ እጥረትም ይታያል፣ ይህም በወጣቶች ስብዕና ላይ ትልቅ የሰብአዊ መብት እረገጣ ተብሎ ሊመደብ ይችላል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በተሳሳተ አስተዳደር እየተመሩ ነው፣ የፖለቲካ ተቋማት እየሆኑና የገዥው ፓርቲ ታማኞች የሙስና ስልጠና አካባቢዎች እየተደረጉ ነው::

” በገፍ መቃወም ያለብን ትልቅ ገጽታ ያላቸውን ቀውሶች ብቻ ሳይሆን ትንሽ ገጽታ ያላቸውን ጭምርም መሆን አለበት፡፡ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ሁላችሁም በሚባል መልኩ ሁልጊዜ ደካማ የመከላከል ጨዋታ ታደርጋላችሁ::መስታወቱ እንዲህ ይገልጻል፣ “በዲያስፖራው ያላችሁ ሁላችሁም መንግስት የሚሰራውን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ፣ የማይሰራውን ግን በጣም ጥቂት ብቻ ትይዛላችሁ:: በቅርቡ በህይወት የተለዩት የገዥው አካል መሪ ይህንን ደካማ ጎን እንደ በሰይፍነት የመጠቀም ጉብዝና ነበራቸው:: እና እናንተ በሙሉ ለአገራችሁ እርባና ያለው ነገር ስትሰሩ አትታዩም፣ እሳቸው የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሉ አንድ አስደንጋጭ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ እናንተ ለዚያ ምላሽ ለመስጠት ስትሽከረከሩ ትወጡ ትወርዱ ነበር፣ ይህንም አይተው በዚያ ጭራቃዊ ፈገግታቸው ይመለከቱ ነበር::” ለመስታወቱ እንዲህ በማለት ለመግለጽ እሞክራለሁ፣ “እኒያ ሰው ጨካኝ በመሆናቸው ጎበዝ ነበሩ፣ እሳቸው ዋና የነገር አጧዥ፣ የተንኮል ንድፍ አውጭ፣ ታማኝነት የሚጎድላቸው እና የብልጥነት ሴራ የሚሰሩ ነበሩ፡፡ ምርጫ አልነበረንም::” መስታወቱ ይሄን አስተያየት ችላ አለው:: “አሁንም የእርሳቸው ጋሻጃግሬዎች በእርሳቸው ፈለግ እንደዚያው እንደተለመደው የማይረባ ድርጊታቸውን እንዲቀጥሉ ትፈቅዳለህ?“ እኔ መልስ የለኝም፣ ጥያቄው እንዳልሰማ ለማስመሰል እሞክራለሁ፣ ለእራሴ ቀስ ብየ እናገራለሁ፣ “ምንም ዓይነት ቡድን ጠንካራ የመከላከያ መስመር ሳይኖረው ለድል አይበቃም“:: ጠንካራ የዲያስፖራ ቡድኖችን መፍጠርና ጠንካራ የመከላከል ጨዋዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁላችሁም ትኩረት ይጎድላችኋል፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣”ሁላችሁም ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላ ዝውውር ለማድረግ ትኩረትና ተስፋ ይጎድላችኋል፣ የቀውስ ሁኔታዎችን በንዴት ምላሽ ለመስጠት ስትሞክሩ ይህ ሁኔታ ደግሞ በጣም ረዥም በሆነ ምንም ነገር ያለመስራት ወሰንተኛ የሆነ ቸልተኝነት ያስከተላል::” እራሴን እጠይቃለሁ፣ “ያ የሚሆነው ለምንድን ነው?“ ድርጅትና አመራር ሳይኖር አንድ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላልን? ለምንድን ነው ግልጽና ጠንካራ የአድቮኬሲና የድርጊት አጀንዳ የማይኖረን?” ለመስታወቱ እነግረዋለሁ፣ “ትኩረት ያጥረናል ምክንያቱም ግልጽ ራዕይ የለንም፣ ራዕይ ያጥረናል ምክንያቱም ቁርጠኝነት ያጥረናል፣ ቁርጠኝነት ያጥረናል ምክንያቱም በእራሳችን በራስ መተማመን እና በክርክር ጭብጦቻችን ላይ እምነት ያጥረናል፡፡“ እዚህ ላይ የአፍሪካን የጥንት አባባል በመዋስ፣ “ወደየት እንደምትሄድ ካላወቅህ ማንኛውም መንገድ እዚያ ያደርስሀል፡፡“ አብዛኞቻችሁ ቆሞ ተመልካች ናችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “አብዛኞቻችሁ ከጎዳና ዳር ቆሞ ማየትን ትመርጣላችሁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከጎን ሆነው ትችት መሰንዘርን ይመርጣሉ፡፡“ አቋረጥኩ፡፡ “ዋናው ዘዴ የተመልካቾችን ምዕናብ ለማጎልበት፣ ለእነሱ ተስፋ ለመስጠትና ለማጠናከር፣ እውቀት እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ በእራስ የመተማመን ጠቀሜታ ለማጎልበት ነው፣ በዚህም መሰረት ከተመልካችነት ወደ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ይቀየራሉ፡፡“

 መስታወቱ ስሜትን እንዲህ በማለት ያነሳሳል፣ “ሰብአዊ መብት የተመልካች እስፖርት አይደለም፣ ሰብአዊ መብት የቡድን ስራ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሜዳው ውስጥ ነው፣ እያንዳንዱ ሰው የሚጫወተው ድርሻ ይኖረዋል እና ትልቅ ግብ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡“ ከታች ጀምረን ማነሳሳትና ማንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡ እናንተ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ የሲቪክ ማህበረሰብ የድርጊት ዘመቻ መመስረት አለባችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ በአንክሮ ያስጠነቅቃል፣ “እናንተ ሁላችሁም ለድል የሚያበቃችሁን መንገድ በመከተል በተለየ ሁኔታ ለመስራት፣ ቅድሚያ ዝግጅት በማድረግ ለመስራት፣ ከስሜታዊነት ነጻ ሆኖ ለመስራት መብቃት አለባችሁ፡፡“ እናንተ ሁላችሁንም ማስተማር፣ ማንቀሳቀስ፣ ማደራጀትና ማጠናከር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ለጋራ ጥረት ማብቃት አለባችሁ፡፡ እናንተ ሁላችሁም የሰቪክ ማህበረሰቡ ጋር በመሆን ዘመቻውን በቀልጣፋነት ማካሄድ አለባችሁ፣ ለሲቪክ ማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ህበረተሰቡን በኮሚቴ፣ በጎ ፈቃደኞችን በመመልመል፣ ለወርክሾፖች አመራር በመስጠት፣ ከታች ጀምሮ ያለውን እያንዳንዱን ዜጋ ለማጠናከር እና በንቃት ለማሳተፍ በቴሌቪዥንና ሬዲ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት በመስጠት መስራት ያስፈልጋል፡፡ የሲቪክ ማህበረሰቡ ከታች ጀምሮ በሙሉ እንዲሳተፍ! እናንተ ሁላችሁም በሌሎች ላይ ስድቦችን በመወርወር ጊዜ ማባከን፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እናንተ ሁላችሁም ገዥውን አካል በማውገዝ እና ዘለፋዎችን በመወርወር ብዙውን ጊዚያችሁን በከንቱ ታባክናላችሁ፣ ሁላችሁም አታገኙትም፣ የዱሮ አባባል በመዋስ፣ ’ከአሳማ ጋር (ወይም ከሌባ) ከጭቃ ውስጥ ትግል አትግጠም‘ አሳማው (ወይም ሌባው) ሲደሰት አንተ ቆሻሻ ትሆናለህ:: ወሮ በላን በጭቃ ጅራፍ በዝልፍያ መስተካከል አይቻልም::” ምላሽ ለመስጠት ፈጠንኩ፡፡ “አንድ ሰው አካፋን አካፋ ማለት አለበት፡፡

“ መስታወቱ እንዲህ በማለት ምክር ይለግሳል፣ “ስለዚህ አንዴ ጥራው እና ተንቀሳቀሱ፣ አስታውስ! ወደ ዴሞክራሲ ወይም ወደ ነጻነት በስድብ አትደርስም፡፡”” መስማማቴን ለመገልጽ እራሴን ነቀነቅሁ፡፡ “የእውነት ወንጭፎችን እና ቀስቶችን ታጥቀን መዋጋት አለብን፣ በእውነት ጋሻዎች መመከት አለብን፣ ከመብት እረጋጭ ኃይሎች ነጻ ሆነን በነጻነት ለመናገር፣ ለመዘመር፣ ትልቁን ጉዞ መጓዝ አለብን፡፡“ እውነትን ተናገር እንጅ የሰብአዊ መብት እረጋጭ ኃይሎችን አትሳደብ፡፡ እናንተ ሁላችሁም በክፍል ውስጥ ላለው ዝሆን ትኩረት ስጡ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እነሱን ለመረዳት ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ጫማዎች ለመጓዝ ሞክር (ምክንያቱም“እነሱን ለመረዳት መሞከር ጊዜ ማጥፋት ነው) ነገር ግን የእነርሱን ፍርሃት ለመረዳት እና የድብቅ እንባ ማፍሰስ ለመገንዘብ ሞክር፣ እነሱ አደጋዎች ጭካኔ የተሞላባቸው እና ህሊና የሌላቸው ናቸው፣ ነገር ግን ፍርሃት አልባዎች አይደሉም፡፡ በፍርሃት ይኖራሉ፣ ነገር ግን መሰረተቢስ ፍርሃቶች አይደሉም፣ የእነርሱ ፍርሃት በጫካው ውስጥ በማታ አያነደደ እንደሚያበራው ነብር ሁሉ ተመሳሳይ ናቸው፡፡” ይላል ዊሊያም ብሌክ፡፡ “የቸርቺል ኬኔዲ የፍርሃት ተቃርኖ’ በሚሉት ወጥመድ ተይዘዋል፣ አምባገነኖች ደፍረው ወጥተውው በማይጋልቧቸው ነብሮች ከወዲያ ወዲህ ይላሉ፣ እና ነብሮቹ ተርበዋል”፣ ቸርችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ ለማስታወስ “በጥንት ጊዜ በሞኝነት በነብሮች ጀርባ ላይ በመቀመጥ ኃይልን ለማግኘት ይፈልጉ የነበሩ አምባገነኖች በነብሮቹ ሆድ ውስጥ ገብተዋል፣ በሌላ አባባል “በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ የሚከለክሉ እነሱ በአመጽ መወገዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱ ቀጠለ፣ “አምባገነኖች እርግጠኛ እና እብሪተኛ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ይህ ሁሉን አቀፍ የሆነ ፍርሃታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የሚያደርጉትና ከዕለታት በአንዱ ቀን እነርሱ ከታች ለወደቁ ጭቁኖች እነርሱ በፈጠሩት ገሀነም አነርሱ ስልጣናቸውን በኃይል ተነጥቀው ወደ መቀመቅ መውረዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱን እጠይቀዋለሁ፣ “አምባገነኖች ቀን በቀን ይኖራሉ ብለህ መናገር ትችላለህ? ነገ ድረስ ለመቆየት አምባገነኖች ዛሬ ሁሉን ነገር ያደርጋሉ፣ ነገ ከነገ ወዲያም እና ከዚያ ወዲያም ቀን በቀን ነው የሚኖሩት?“ መስታወቱ እንዲህ ያስተካክለዋል፣ “በፍጹም፡፡ አምባገነኖች ሰዓት በሰዓት፣ ደቂቃ በደቂቃ፣ ሰከንድ በሰከንድ በፍርሃት ተውጠው ነው የሚኖሩት፣“ የተራቡ ነብሮች? የነቁ ግዙፎች ነብሮች! እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ ከመሄድህ በፊት የመጨረሻዋን ቃል መስታወቱ እንዲህ ይናገራል፣ “እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ እናንተ ሁላችሁም ጓደኞች መፈለግና ከእነርሱ ጋር ተባብራችሁ በጋራ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡” ማሰብ ጀመርኩ፣ “ስንቶቻችን ነን ለእኛ ምርጥ ጓደኞች ጓደኞች የሆን? ስንቶቻችን ነን የሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዘላለማዊ መጠበቂያ አባል የሆንነው? ስንቶቻችን ነን የሲ ፒ ጄ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ድርጅት መብራቱን በቃሊቲ እስር ቤት ላይ በማነጣጠር እነ አስክንድር ነጋ፣ ውብእሸት ታየ እና ሌሎች በህገወጥ መንገድ ታስረው ለሚገኙት አባል የሆንነው? ብቻችንን ልንሰራው የምንችለው ጉዳይ አይደለም፡፡

ስንቶቻችን ነን ባህላዊውን የህብረተሰብ ቡድኖች እና የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥፋት ለመከላከል ብለው ልዩ ስራዎችን ዓለም አቀፍ ወንዞች በፍትሀዊነት እንዲያገለግሉ የሚታገሉትን ዜጎች የምናደንቅ? በዓለም አቀፍ እና በአገር ውስጥ ከሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ጓደኛ አለን? በድንገት በአምሮዬ ጥያቄ መጣ፡፡ ለምንድን ነው እነ ሲኤን ኤን፣ቢቢሲ፣ ኤቢሲ፣ ሲቢኤስ፣ አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኤልኤ ታይምስ፣… የእኛን ሰላማዊ ተቃውሞዎች ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉት?“ ከእነርሱ ጋር ጓደኝነት ስላልመሰረትን ነው? ብቻችንን ልንሰራው የምንችለው ጉዳይ አይደለም፡፡ አብረን ለምንሰራው ሁሉ ሰማይ ወሰናችን ሊሆን አይችልም! መስታወት፣ መስታወት በ…. “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እውነቱን ወይም ደግሞ ውሸቱን ሊነግረን ይችላል፡፡ ምናልባት በመስታወቱ ውስጥ ማየት የምፈልገውን አይቼ ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱም እኔ በመስታወቱ ላይ እንዲታይ ያስቀመጥኩትን አንጸባርቆ ይሆናል፣ ምናልባት መስታወቱ ሁሉም መልሶች ያሉት ወይም የሌሉት ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱ የእኔ ህሊና ይሆናል፣ በእርግጥ በበየእለቱ በመስታወቱ ስመለከት የምጠይቀው፣ “በግድግዳው ላይ ያለህው መስታወት የነቃው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርበታል? ወደፊት ይቀጥላ … ለአንባቢዎች ማስታወሻ፣ “ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት ንግግሮች“ ልዩ በተከታታይነት የሚወጡ ትችቶች ናቸው፣ወደፊት በየጊዜው በሚስቡ ክስተቶችና ድርጊቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደምጽፍ እገምታለሁ፡፡ ማስተማሪያና መማሪያ በሚሆኑ ድርጊቶችለመምህር ፈልጎ ማውጣት መቻሉ በአጣቃላይ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡ 12/4/2013

‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የመሸጋገሪያ ድልድይ ፈረሰ

December 5/2013
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጆሊ ባር...
፣ ኮጆሊ ባር ወደ አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ለመሸጋገርያ የሚያገለግል የብረት መሰላል መሥራቱ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ ይህንን መሸጋገሪያ መሰላል የሠራው፣ በአካባቢው የሚተላለፈው የሕዝብ ብዛት ከሌሎች አካባቢዎች የበዛ ስለሆነ፣ የትራፊክ መጨናነቅና በየቀኑ በተሽከርካሪ አደጋ እየተቀጠፈ ያለውን የሰው ሕይወት (ምንም በተባሉት ቦታዎች እስካሁን የከፋ አደጋ ባይደርስም) ለመታደግ በሚል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ሦስተኛ መሸጋገሪያ ድልድይ የሠራው ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ወደ ራስ መኰንን፣ ወደ አዲሱ ገበያና ወደ አፍንጮ በር (ውቤ በረሃ) በሚወስደው አደባባይ ላይ ነው፡፡
ይህ መሰላል አቀማመጡ ወይም የተሠራበት አቅጣጫ ለተጠቃሚው አመች ባለመሆኑ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሲጠቀሙበት የሚስተዋሉት የጐዳና ተዳዳሪዎች ናቸው፡፡ በአካባቢው የሚኖሩት የጐዳና ተዳዳሪዎችም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጥር ሥር የሚያድሩና በልመና ላይ የተሰማሩ ሲሆኑ፣ መሰላሉን መፀዳጃ በማድረጋቸው፣ መተላለፊያነቱ ቀርቶ የበሽታ ማስተላለፊያ እስከመሆን ደርሶ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያሠራው የፒያሳው የመተላለፊያ መሰላል በአካባቢው በሚገነባው የቀላል ባቡር ተርሚናል ምክንያት ሰሞኑን እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ የተሠራበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን የሚያስታውሱ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ‹‹አስተዳደሩ የሚመራው በዕቅድና በፕሮግራም ከሆነ፣ ቀላል የባቡር መስመር በቅርብ እንደሚሠራ እያወቀ በዚህን ያህል ወጪ ለምን አሠራው?›› በማለት በትዝብት እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡   ‹‹ጥቅም›› ላይ ሳይውል የፈረሰው መሸጋገሪያ

Ginbot 7’s Response to EPRDF’s Request for “Negotiation”

December 5, 2013
The authoritarian system that has been built by the Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) is in apparent crisis. It is now evident that panic and nervousness within EPRDF is increasing with the passing of each day, and there is ample evidence that indicates towards this major behavioural shift within the ruling EPRDF party. For example, the sudden death of its leader, the ever increasing popular resistance inside and outside the country, and the customary uneasiness of the regime as national elections approach are some of the main indicators. The long-standing political behaviour the EPRDF regime demonstrates that whenever EPRDF is cornered or finds itself in a crisis situation, it uses negotiation as a quick way out or crisis management tool. We believe EPRDF’s most recent call for “negotiation” is not different from its established political behaviour.
Ginbot 7: Movement for Justice, Freedom and Democracy has repeatedly affirmed its strong allegiance towards a democratic change in Ethiopia in a peaceful way through dialogs, discussions, and negotiations. It is EPRDF’s stubbornness and arrogance that pushed Ginbot 7 to look for alternative means and strategies of fighting for justice, freedom and democracy.
The Executive Committee of Ginbot 7 has thoroughly deliberated on EPRDF’s call for “negotiation”. The committee has concluded that this issue concerns the Ethiopian people as a whole, not just Ginbot 7 as a movement. Ginbot 7 strongly believes that the negotiation and its outcome has direct impact on the struggle for freedom and democracy that the Ethiopian people have already waged, and the sacrifices that they are paying. Therefore, Ginbot 7 has decided to exploit the convenience of this opportunity to reiterate its position on negotiation in general, and EPRDF’s current call for negotiation in particular.
1. On negotiated change
As we have repeatedly made it very clear to the Ethiopian people, our primary choice or the most preferred way of struggling for democratic change in Ethiopia is through peaceful dialogs and constructive round table discussions. It is the arrogance of the EPRDF, and particularly its use of force to settle political differences that forced us to look for alternative strategies. G7 has made it clear, time and again, that if the choice presented to us is between living in tyranny and fighting for our liberty, our choice always is dying in dignity while fighting for liberty. We deeply believe in these sacred values, and it is this fundamental principle that attracts our members in Ethiopia and all over the world.
Our principal standpoint on negotiations has two aspects. The first has to do with the process itself. We are always open for a meaningful negotiation to settle political problems. The second has to do with the expected outcome of such an exercise. The outcome of the negotiations should lead to the establishment of a genuine democracy at the minimum possible cost. Ginbot 7 is not interested in negotiations that will jeopardise the aspiration of the Ethiopian people for justice and democracy. We welcome negotiations that can insure sovereignty of the Ethiopian people to decide and shape their destiny through free and democratic process. We cannot negotiate against our principles and the will of the Ethiopian people.
Therefore:
  1. Full recognition of the sovereign power of the Ethiopian people and laying the foundation for a democratic political dispensation should be the ultimate outcome of any and all negotiations. This being the primary goal, there might be several other valuable goals that come in the process, such as the immediate release of all political prisoners. However, other goals, valuable as they may be, cannot substitute the primary goal of establishing a genuine democratic dispensation. The primacy of the will of the Ethiopian people is not negotiable. Ginbot 7 shall not negotiate with EPRDF, or any other force for that matter, unless it accepts this primary objective.
  2. Such negotiations should be conducted not only between EPRDF and Ginbot 7; but with all other stakeholders – political and civic organisations—. EPRDF’s preference to negotiate with individual organisation emanates from a short sighted tactical calculation; it does not show that it seeks long term sustainable solution to the multifaceted challenges facing the country. There is no democracy that is good for one organisation only. All efforts to establish a democratic order should include other political and civic organisations in Ethiopia. Deciding who should run the country, or who should get how much power are not the principal objectives of such a negotiation. The negotiation should be how to empower people to elect their own leaders in a free and fair election and ensure the basic rights of citizens. The issue should not be power grab but starting a genuine process that will establish an acceptable, just and democratic system of governance in Ethiopia.
  3. As explained above, this is a national issue and cannot be conducted behind closed doors. There is no reason why it should be kept secret from the Ethiopian people.
2. Confidence building measures to ensure that past mistakes are not repeated
Based on our past experience in negotiating with EPRDF, which emanate from lack of sincerity on the part of the EPRDF, negotiations should take the opponent’s behaviours into account. Negotiating with an untrustworthy entity requires a different approach to that conducted with a credible negotiating partner. The later requires a set of precautions to ensure that there is a good faith effort to negotiate as well as a rigorous mechanism of verification and implementation to avoid backsliding. In the absence of such precautionary measures, the negotiation cannot be expected to be fruitful.
This is not the first time that EPRDF sought negotiation. So far, we do not know a single instance when EPRDF faithfully implemented agreements reached at negotiations. Rather, we have observed time and again that it in fact cherishes violating negotiations as bravery and cleverness. Nothing is more important to EPRDF than clinging on to power. It hasn’t shown any willingness in the past to sacrifice even a fraction of its power for the long-term benefits of the country.
We, in Ginbot 7, do have first-hand experience with EPRDF’s bogus negotiations. We cannot allow this to repeat itself.
Therefore, we need to make sure that the following actions are taken by the EPRDF government as a confidence building measure and as an indicator of its genuine interest in finding a negotiated solution to the country’s multifaceted political problems:
  1. All political prisoners, journalists, human right activists should be released. This should include those who are detained in secrete prisons;
  2. Intimidating people, especially members of the opposition political parties should stop immediately. The rights of every Ethiopian should be respected and protected;
  3. All politically motivated verdicts of the Kangaroo courts should be nullified. Files that are currently active should be dropped;
  4. All repressive laws that are aimed at terrorising and silencing people should be annulled;
  5. Negotiations should be conducted in the presence of third party mediators. All the process should be filed and kept in hands of the independent mediators. The negotiation place itself should be negotiated. The whole process should be open to the Ethiopian people.
If EPRDF is not willing to take these actions, we would not believe that it has any genuine interests in any negotiated settlement. Until then, Ginbot 7 and other democratic forces will continue their struggle in line with their respective strategies. Ginbot 7 will not be distracted by a negotiation proposal and process that lack substance towards tackling and resolving the longstanding challenges facing Ethiopia and in line with the aspiration of the Ethiopian people for a genuine and democratic change.
December 2, 2013
The Executive Committee
Ginbot7: Movement for Justice, Freedom and Democracy.

ኢትዮጵያን በሙስና ከሚታወቁ የዓለም አገሮች ተርታ ያሰለፈው ሪፖርት ይፋ ሆነ

December 5, 2013 

corruption index



ትናንት ኅዳር 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በመላው ዓለም ይፋ የሆነው የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ተቋም የሙስና አመላካች ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ከሙስና ጽዱነት ተርታ ውጭ ከሆኑና በሙስና ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈረጁ አገሮች አንዷ ሆና መገኘቷን ይፋ አደረገ፡፡
ሪፖርቱ በሚከተለው የሙስና መለኪያ ሚዛን መሠረት፣ ከሙስና ጽዱ የሚባሉ አገሮች ከዘጠና እስከ መቶ ነጠብ የሚያገኙት ናቸው፡፡ በአንፃሩ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል፣ የሙስና ጎሬ ሆነዋል ተብለው የሚታሰቡ አገሮች ደግሞ ከመለኪያው ከ50 በመቶ በታች የሚያስመዘግቡት ናቸው፡፡ በመንግሥት ተቋሞች ውስጥ ከፍተኛ ሙስና ተንሰራፍቶባቸዋል ተብለው ከተለዩት ውስጥ ኢትዮጵያ 33 ከመቶ የመለኪያውን ነጥብ በማስመዝገብ ከከፍተኛ ሙስኞች ተርታ እንደምትሰለፍ የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ከ177 አገሮች ውስጥ 111ኛውን ደረጃ መያዟም በሪፖርቱ ይፋ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ መላው አገሮች ለሙስና ተጋላጭነት ከሚለኩባቸው መመዘኛዎች መካከል፣ የፕሬስ ነፃነት፣ የተጠያቂነትና የሰዎች የመደመጥ መብት፣ የፍትሕ አካላት ከተፅዕኖ ነፃ መሆን፣ የሕግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ ልማት መለኪያና ሌሎችም ጠቋሚዎች እንደሚካተቱ ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በድረ ገጹ ይፋ አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በፕሬስ ነፃነት ከ179 አገሮች 127 ደረጃን በመያዝ የፕሬስ ነፃነት ከሌሉባቸው አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ በፍትሕ አካላት ነፃነትና ከተፅዕኖ ውጭ ካልሆኑ አገሮች መካከል አንዷ ስትሆን ከ142 አገሮች ውስጥም 93ኛ መሆኗ ይፋ የተደረገው ዓምና ነበር፡፡
ተቋሙ 177 አገሮችን በሙስና እንደሚጠረጠሩበት ደረጃቸው በመመዘን ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሐራ በታች ከሚገኙ አገሮች 90 ከመቶው ለሙስና በሚያስጠረጥራቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሆነው አግኝቷቸዋል፡፡ ቦትስዋና ከሰሐራ በታች አገሮች ዝቅተኛ የሙስና ወንጀል የሚፈጸምባት ስትሆን፣ ሶማሊያ ከሁሉም አገሮች በታች በመሆን ሙስና የተንሰራፋባት ተብላለች፡፡ በዓለም ላይ ከ177ቱ ውስጥ 69 ከመቶ አገሮች ከፍተኛ የሙስና መናኸሪዎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያረጋግጣል፡፡
ከሰሐራ በታች የሚገኙትን አገሮች በሙሰኝነት ተፈርጀው የሚመሩት የምሥራቅ አውሮፓና እስያ አገሮች ሲሆኑ፣ 95 ከመቶ በላይ አገሮች ከፍተኛ ሙሰኞች ሆነው ተመዝግበዋል፡፡
በዓለም ላይ ከፍተኛ ሙስና ከተንሰራፋባቸው አሥር አገሮች ስድስቱ ከሰሐራ በታች አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ (ሪፖርተር)

Wednesday, December 4, 2013

ሳውድ አረቢያ የውጭ ዜጎችን ማስወጣቱዋን እንደምትቀጥል አስታወቀች

december 4/2013

ህዳር (ሃያ አምስ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ካለፈው ወር ጀምሮ ህጋዊ ወረቀት የላቸውም በሚል የውጭ ዜጎችን ማባረር የቀጠለችው ሳውድ አረቢያ፣ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ትችት ቢደርስባትም፣ ዜጎችን ማስወጣት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። አረብ ኒውስ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 126 ሺ ሰዎች ከአገሪቱ መውጣታቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ 90 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል።

አረብ ኒውስ አንድ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ውጭ ዜጎችን የማስወጣት እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል። ኢትዮጵያውያን በአለማቀፍ መድረኮች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ቢቀንሱም፣ አሁንም ግን ከ40 ሺ ያላነሱ እስረኞች በእየሰር ቤቶች ወንጀለኞች ተብለው ታስረው እንደሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በአረብኛ የሚታተሙ ጋዜጦችን በመጥቀስ ተናግረዋል። አረብ ኒውስ ዛሬ ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያውያን ከአገሪቱ ከወጡ በሁዋላ ወንጅል በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ብሎአል።
ሂማውን ራይትስ ወች ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት ያቀደው የሳውዲ መንግስት፣ እርምጃ ከመውሰዱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ” ኢትዮጵያውያንን የሚያጥላላ ዘገባዎችን ያሰራጭ እንደነበር መጥቀሱ ይታወቃል። የሳውዲ ጋዜጦች ኢትዮጵያውያንን ማጥላላት መቀጠላቸው የሳውዲ መንግስት በሂደት ለሚወስደው እርምጃ ጋዜጦቹ ከአሁኑ መከላከያ እያዘጋጁለት ነው በማለት በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወረቀት የላቸውም በሚል እንደሚባረሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የሳውዲ መንግስት የምህረት አዋጁን ሊያራዝም ይችላል በሚል ወደ አገር ለመመለስ እአመነቱ እንደሆን ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ በተለይም በጅዳ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ተመሳሳይ ከአገር የማስወጣት ዘመቻ ሊካሄድ እንደሚችል የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በጂዳ ሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ሳይዘናጉ አጋጣሚውን በመጠቀም ቶሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያነጋገርናቸው ሰዎች መክረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።  መንግስት ይህን ያክል ህዝብ በአንድ ጊዜ ለመቀበል አቅም እንደሌላው እየገለጠ ይገኛል።

ማምሻውን በሹክሹክታ የደረሰኝ ብርቱ መረጃ !

December 4/2013

ነቢዩ ሲራክ ke Saudi Arabia
መልዕክቱን አስቀድሜ ዝርዝሩን ላስቀጥል ልቤ ፈቀደ ! ሹክሹክታው የመልዕክቱ አደራረስ እንጅ መልዕክቱ የተጨበጠ እውነት ነው እናም ስሙኝ ... !
ይድረስ ለወገኖቸ ... ህጋዊ መኖርያ ሰንድ ስሌላችሁ ወደ መጠለያ ለመግባት ፈልጋችሁ እስካሁን እድሉን ያላገኛችሁ ወገኖቸ ሆይ! እነሆ ተራችሁ ደርሷል ! በተለምዶ ፖሊስ ለማያዝ ሰው በሚሰባሰብበት በሸረፍያ ድልድይ ስር በመሄድ እዚያው ብትሰባሰቡ በሁለት ቀናት ውስጥ አውቶቡስ እየመጣ ወደ ሽሜሲ መጠለያ እንደሚወስዳችሁ ከአንድ ብርቱ ውስጥ አዋቂ ወዳጀ በሹክሹክታ መረጃ ደርሶኛል! ሽሜሲ እንደደረሳችሁ ወደ መጠለያው ሳትገቡ አሻራ በማድረግ በአንድ ቀን ልዩነት ወደ ሃገር ቤት የምትገቡበት መንገድ መዘርጋቱንና ይህንንም ለማሳለጥ የመጠለያው ሃላፊዎች ፣ የፖስፖርት ክፍል (የጀዋዛት) ሃላፊዎችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ከጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መክረው ዘክረው ውሳኔ መተላለፉ ብርቱ መረጃ ከብርቱው ውስጥ አዋቂ ወዳጀ መረጃው ማምሻውን በስልክ አቀብሎኛል !
መረጃውን ያቀበለኝን አረብ ወዳጀ ለተጠቀሱት መረጃዎች ቅርብ ነው ። እናም መረጃውን አቀብሎኝ ሲጨርስ በራሴ ላይ የሚጉላላውን ጥያቄ አነሳሁና ... ለምን ነዋሪው በጅዳ ቆንስል ተሰብስቦ እንዲሄድ አይደረግም? ስል ጠየቅኩት " እሱን እርሳው! በአካባቢው የኢትዮጵያ ቆንስልን ጨምሮ የተለያዩ ዲፕሎማሲ መስሪያ ቤቶችን በአካባቢው ይገኘኛሉ ። ትልቁ የንጉስ ፉሃድ ሆስፒታል ትምህርት ቤቶችና በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በቆንስላችሁ አካባቢ ምንም እንቅስቃሴ ሊኖር አይፈቀድም! አሁን መውጣት ለሚፈልጉ ብቸኛው አማራጭ ሸረፍያ ብቻ ነው ። እዚያ በመሔድ የአካባቢውን ጸጥታ ሳይረብሹ በረጋ መንፈስ መሰባሰብ ከቻሉ ቢበዛ በ24 ሰአት ውስጥ መሰባሰባቸው ሲታወቅ አውቶቡሶች መጥተው ይወስዷችኋል! አውቶቡስ ላይ እንዳሉ የመጓጓዣ ሰነድና አሻራ እንዲሰጡ ይደረጋል ! በመጡበት አውቶቡስ በመጠለያው ሳይውሉ ሳይድሩ በተዘጋጀው አውሮፕላን ወደ ሃገራቸው ይላካሉ ! ሌላው
የመጠለያ እንግልቱን ፈርተው በራሳቸው ቲኬት መሄድ ለሚፈልጉትም አሁን የሚፈሩት ችግር የለም ። ለቲኬት ገንዘብ አይክሰሩ ፣ ቲኬት በራሳችሁ ከሚቆርጡ ገንዘባቸውን ቆጥበው ሸረፍያ አውቶቡስ ሲመጣ ጠብቀው ተዘጋጅተው ከሄዱ በአንድ ቀን ሰንድ ተሰርቶላቸውና ቲኬት ተቆርጦላቸው ወደ ሃገር ቤት መግባት ይችላሉ ። ይህ ማለት ደግሞ ገንዘብ ቆጠቡ ማለት ነው! ግን በአየር መንገድ በቤተሰብ መሸኘት ከፈለጉ የራሳቸው ምርጫ ነው ። " ሲል የማይዋሸው ብርቱ ወዳጀ የሰጠኝ መረጃ ውሃ የሚያነሳ ምክር ጭምር ነው!
ጥያቄየን ቀጠልኩ ...ከሁለት ቀናት በፊት በአልጋ ወራሹ ልዑል ሰልማን በመሩት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ " ህገወጦችን በማስወጣቱ ረገድ እርምጃውነሰ አጠናክረን ፣ እንቀጥላለን " የሚለውን ጠንከር ያለ መግለጫ አነሳስቸ ፣ ብዙ ነዋሪዎች " ህጉ ይሻሻላል ፣ የምህረት አዋጁ ለአመት ተራዝሟል ! " በሚል ወደ ሃገር ቤት መግባትን አለመፈለግ እንደተጋጨብኝ አጫወትኩት ... ቀጠልኩና በዚህ ዙሪያስ ምን ትላለህ? ስል ወዳጀን የብዙዎቻችሁን ጥቃቄ ጠየቅኩት! ያማይዋሽ የማይቀጥፈው ፣ ብርቱው የመረጃ ምንጨ ፈገግ እንደማት ብሎ መለሰልኝ " ልብ ያለው ልብ ቢል ይሻላል ፣ ዘንድሮ አምናና ካች አምና አይደለም ፣ ሰአቱ ሳይልቅ በተከፈተው መንገድ የወጡ የታደሉ ነው የሚሆኑት! የምክር ቤቱን መግለጫ ሰምተሃል ፣ እኔም ውስጥ ውስጡን እየሆነ ያለውን ገላልጨ አልነግርህም ፣ ህገ ወጥ ሆኖ ፣ ያልተሟላ ሰነድ ይዞ እንደ ቀድሞው " ህግ ይሻሻላል፣ ምህረት አለ !" የሚለውን ተወው! አመነኝ! ያ ጊዜ አሁን አይደገምም!
ልብ ያለው ልብ ይበል ፣ ጓዙን ሸካክፎ ዛሬ በመጣው እድል ተጠቅሞ ወደ ሃገሩ በሰላም ቢገባ ይሻለዋል። ይህ ላልሆነና ተደብቄ ጊዜውን አለወፋለሁ ለሚል ፍርድ ነው! መቀጮውን ከፍሎ በእስር ማቅቆ እንደሚሄድ አትጠራጠር ! ይህ ብርቱ ህግ ነው ፣ ህጉን ለማስፈጸም መንግሰት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣ ነው ፣ ሁሉመ ሆኖ ያለወጣ ሰውዋጋውን ከፋይራሱ ነው የሚሆነው! " ሲል ቀርጥ አድርጎ የሚያውቀውን መረጃ አካፍሎኛል!
በሽሜሲ መካ መጠለያ እና በመዲና ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የጠየቁት በአብዛኛው በያዝነው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት መሸኘታቸውን ተጨባጭ መረጃ ደረስኝ መባቻ ወዳጀ ውስጥ አዋቂው ያለኝን ሰምታችኋል። የጅዳ ከተማ ያሉ ወገኖች ተራውየእናንተ ነው ፣ ተዘጋጁ ፣ አማራጫችሁን እናንተው ታውቃላችሁ! ወገኖቸ ሆይ ! ጆሮ ያለው ይህን ሹክሹክታ ይስማ !
መረጃው እንደደረሰኝ ከአደጋ ጊዜ ከተቋቋመው ኮሚቴ አንዳንድ አባላት ጋር በሸረፍያ የሚሰበሰበው ነዋሪ ሊረዳ የሚችልበትን መንገድ ተወያይቻለሁ! ዝርዝሩን እና የምክክሩን መድረሻ እናዎጋለን! እስከዚያው ምከሩ ! አትውጡ እንዳልኳችሁ ውጡ ያልኩት ተጨበጭ መረጃን ይዠ እንደሁ ግን እመኑኝ !
የግርጌ ማስታዎሻ :
ወዳጆች ከላይ ሹክ ያልኳችሁን መረጃ የሚያጠናክሩ መረጃዎች ማምሻውን ለእኛ መንግስት ሃላፊዎች እና ለወገን ወገን ደራሽ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ባልደረቦች መድረሱን ሰምቻለሁ! እናም መረጃውን በሰፊው በማሰራጨት ግንዛቤ እንሰጥ ዘንድ እማጸናችኋለሁ ! እባካችሁ share "ሸር" በማድረግ እንደጋገፍ !
እስኪ እሱ ያቅናው !

በመርካቶ ከፍተኛ ቃጠሎ ተከሰተ::

December 4/2013
በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎን ይህ ዜና ለዘ-ሐበሻ እከደረሰበት ሰዓት ድረስ የከተማዋ የ እሳት አደጋ ሊቆጣጠረው አለመቻሉን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታወቁ። ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት መሃል መርካቶ ከከምዕራብ ሆቴል ወደ በርበሬ በረንዳ በሚወስደው መንገድ ወይም በተለምዶው ቦምብ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተነሳ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ንብረት እየወደመ ነው። በዛው አካባቢ በሚገኙት ሜትሮ ሆቴል. ሐረር ዳቦ ቤት፣ ዓለም ሽንሽንና ጌጣጌጥ መሸጫ መደብሮች በዚህ ቃጠሎ የተጠቁ ሲሆን ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀው የእሳት ማጥፋት ሥራ ቃጠሎውን ሊቆጣጠሩት አለመቻላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት ማክሰኞ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት 70 ዎርክሾፖች በ06 ቀበሌ (ኢንዱስትሪ ዞን) በእሳት ቃጠሎ መውደማቸውን አብረሃ ደስታ ከመቀሌ መዘገቡን ዘ-ሐበሻ ላይ አስነብበን ነበር። ዛሬም አብርሃ ከመቀሌ እንደጻፈው “ዛሬ ሮብ ሌሊት ደግሞ በዓዲ ሐቂ ገበያ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶ ብዙ ንግድ ቤቶች ወድመዋል። በተመሳሳይ አጋጣሚ ዛሬ ሮብ ጠዋት በዓዲሹምድሑን ሰፈር በእሳት ቃጠሎ አደጋ ንብረት ወድመዋል።” ብሏል።
አብርሃ ‘መቐሌ በሁለት ቀናት ዉስጥ በሦስት አቅጣጫዎች (ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ) የእሳት አደጋ ሰለባ ሆናለች። የማክሰኞው አደጋ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት ሲሆን የዛሬው የዓዲ ሐቂና የዓዲሹምድሑን ቃጠሎ መንስ ኤ ግን እስካሁን በትክክል አልታወቀም።” የደረሰበትን መረጃ በፌስቡክ ገጹ አካፍሏል።
አብርሃ የመቀሌውን ዜና ከዘገበ በኋላ በአንዳንድ ሰዎች የተሰጠውን አስተያየት ሲተች “መቐለ በ18 ሰዓታት ዉስጥ ሦስት የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አስተናግዳለች (06፣ ዓዲሐቂና ዓዲሹምድሑን)። ህዝብ ተጨንቀዋል፣ አዝነዋል፣ ተገርመዋል። ባለስልጣናቱ ግን ምንም ዓይነት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ እንኳን ዝግጁ አይመስሉም። ካድሬዎቹም አደጋው ከመከላከል ይልቅ ‘ንብረት ወደመ’ ስንል ‘ቃላት ተሳሳቱ’ እያሉ ያሸፉብናል። በመቐለ ከተማ በወደመው ንብረት ለማዘን ስለ እሳት አደጋው መስማት በቂ ነው። ስለ ቃላት አመራረጥ ማተኮር ግን ጥሩ አይመስለኝም። ምክንያቱም ጥረታችን ፅሑፍ መፃፍ ሳይሆን ስለ ደረሰው አደጋ መረጃ መስጠት ነው።” ብሏል።
(ዘ-ሐበሻ)


 

የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት መታሰብያ በዓል እንዳይከበር ፍቃድ ከለከለ

December 4, 2013
የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ 100ኛ አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ ልኳል።

የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡
እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?
ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!
Semayawi party, Addis Ababa

“መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” Ethiopian government did not request to negotiate with Ginbot 7

December 4/2013

(በሰንደቅ ጋዜጣ) “መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” Ethiopian government did not request to negotiate with Ginbot 7
በኢትዮጵያ ፓርላማ በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፤ ኢህአዴግ ለደርድር ጥያቄ አቅርቦልኛል በሚል እያናፈሰ ያለው መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ መሆኑን አቶ ሽመልስ ከማል የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ።
ግንቦት 7፤ ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም በኢሳት ቴሌቪዥን በኩል ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በሁለት ወር ጊዜያት ውስጥ ለሶስት ጊዜያት ያህል የእንደራደር ጥያቄ አቅርቦልኛል ብሏል። ንቅናቄው ለእንደራደር ጥያቄው ምላሽ በሚል ባሰፈረው ሐተታ የኢህአዴግ የእስካሁኑ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ ይገዛል ካለ በኋላ ስማቸው ባልተገለጸ መልዕክተኞች በኩል ደርሶኛል ያለውን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄው በዋናነት ያየው ኢህአዴግ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ ነው በማለት ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል።
አቶ ሽመልስ ከማል ግን በመንግስት በኩልም ሆነ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በኩል ለግንቦት 7 የቀረበ እንደራደር ጥያቄ እንደሌለ አረጋግጠው መንግስት ቢፈልግ ጌታው እያለ ከተላላኪው ጋር ምን ያደራድረዋል ሲሉ ጠይቀዋል። ይህ የእነዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቅጥፈት መሆኑን ጠቅሰው “በዚህ መንገድ እያሞኙ ገንዘብ መሰብሰብ ለምደዋል፤ ይህም ውሽት ለዚሁ ተግባር የተፈበረከ ነው” ብለዋል። ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ሁኔታ ድጎማና ድጋፍ ለሚሰጧቸው አካላት ሒሳብ ለማወራረድ ድል አድርገን ልንገባ ነው በማለት ሲቀጥፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በባዶ ሜዳ ራስን አግዝፎ ለማየት ከመመኘት የሚመነጭ ቅዥት ነው ብለውታል።

ዝምታችን በቃ!! የምናውቀው ብቻችን እጣ ፈንታችን ሰንጎነጫት ነው፡፡ በጣም እጅግ በጣም ከመሸ! ዝም ስንል እናልቃለን! ……

December 4/2013

‹‹መጀመሪያ በ‹‹አማራው›› ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ‹‹አማራ›› አልነበርኩም፡፡ ቀጥለው ‹‹በኦሮሞ›› ላይ መጡ ምንም አላልኩም ምክንያቱም ‹‹ኦሮሞ›› አልነበርኩም፡፡ በመቀጠል ‹‹በሶማሊው፣ በጋምቤላው፣በትግሬው….ላይ መጡበት ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ከአንዳቸውም አልነበርኩም ከዚህ በመቀጠል በሙስሊሙ ላይ መጡ አሁንም ምንም አላልኩም ምክንያቱም ሙስሊም አልነበርኩም በመቀጠል በክርስቲያኖቹ ላይ መጡ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም ክርስቲያን አልነበርኩም በስተመጨረሻ በእኔ ላይ መጡብኝ አሁን ለእኔ የሚቆምልኝ ማንም አልቀረም፡፡ ብቻዬን ነኝ!››
ይህ በናዚዎች ስር የነበረው ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ በአምባገነኖች ስር ያለና የነበረ ህዝብ ታሪክ ነው፡፡ የእኛው የኢትዮጵያውያን የወቅቱ ችግር ነው፡፡ኒይሞለር በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፈና የናዚ ቀንደኛ ደጋፊ የነበር የፕሮቴስታንት ፓስተር ነበር፡፡ ጨፍጫፊው ናዚ ለጀርመናውያን እቆማለሁ ቢልም በሀሳብ የተለዩትን ጀርመናዊያን ላይ ግን ጠንካራ ብትሩን አሳርፎባቸዋል፡፡ እናም ኮሚኒስት፣ ሶሻሊስት፣ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የሰራተኛ ማህበራት….ሌላም ሌላም ከናዚ አስተሳሰብ የሚቃረኑት በሙሉ በየተራ እርምጃ ተወሰደባቸው፡፡ በዛ ዘመን አንዱ ላይ እርምጃ ሲወሰድ ሌላው ዝም በማለቱ ናዚዎች የሚፈልጉትን ሁሉ በግፍ ጨፍጭፈዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የፕሮቴስታንቱ ፓስተር ማርቲን ኒይሞለር የሂትለርና የናዚ ደጋፊ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኮሚኒስት፣ ሶሻሊስት፣ ቤተ እስራኤላዊያን፣ የሰራተኛ ማህበራት… የሚባሉት መካከል ብዙዎቹ ከፕሮቴስታንት ጋር የሚቃረኑ በመሆናቸው እንደ ጠላት አይቷቸዋል፡፡ ፓስተሩ ሂትለር ኮሚኒስቶቹን ሲያዝር፣ ሲገድል፣ ሲያግዝ ‹‹እግዚያብሄር አይወደውም፣ እነሱም ጀርመናውያን ናቸው፣ ይቅር ተባባሉ፣ ተቀራረቡ›› ከማለት ይልቅ እግዚያብሄር የማይወደውን እግፍ በአይኑ እያየ ዝምታን መረጠ፡፡
ናዚ ያልዳሰሰው የህብረተሰብ ክፍል፣ ካድሬ ለማድረግ ያልጣረው ጀርመናዊ፣ ከጎኑ ለማሰለፍ ያልሞከረው መሪ አልነበረምና በስተመጨረሻ ወደ እምነት ተቋማት ማምራቱ የግድ ነበር፡፡ እናም ፕሮቴትታንትም ቤተ ክርስቲያንም ከመጽሃፍ ቅዱስ ይልቅ የናዚን ‹‹ዶክትሪን›› እንድትቀበል ተገደደች፡፡ ልክ እንደኛው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ማለት ነው፡፡ ናዚን አድንቆ የገባውን ካድሬ ‹‹የእምነት አባት›› እነ ሂትለር እጃቸውን ዘርግተው ተቀበሉት፡፡ በእምነታችን ጣልቃ ሊገባብን አይገባም ያሉት ግን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተዋል፡፡
ማርቲን ኒይሞለር የናዚን ‹‹ዶክትሪን‹‹ አልቀበልም ካሉት ‹‹አባቶች‹‹ መካከል አንዱ ነበር፡፡ ናዚ ሲያሰቃያቸው ዝም ብሎ ያያቸው ቤተ እስራኤላዊያን፣ ኮሚኒስቶች፣ ሶሻሊስቶች፣ የንግዱ ማህበራት…..የደረሰባቸው እጣ ፈንታ አሁን እሱ ጋ ደርሳለች፡፡ ከሌሎቹ ጋር ባለመተባበሩ ብቻውን ቀረ፡፡ ናዚዎች አስረው ሲያሰቃዩት ኖረው የተፈታው ጥምር ጦሩ ከአሸነፈ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም ይህ ፓስተር ከስቃዩ በኋላ በእጅጉ ተጸጽቷል፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1984 ድረስ ስለ ሰላም ሰብኳል፡፡ ይህ ሰው ከሚታወቅባቸው መካከል ዝምታ አንድ በአንድ እንደሚያስጨርስ በእስር ዘመኑ የተናገረውና መግቢያየ ላይ ወደ እኛው ሁኔታ አጠጋግቼ የጠቀስኩት ወርቃማ አባባል ነው፡፡ እሱ ቃል በቃል ያለው እንዲህ ነበር፡፡
‹‹First they came for the communists, and I didn't speak out because I wasn't a communist. Then they came for the socialists, and I didn't speak out because I wasn't a socialist. Then they came for the trade unionists, and I didn't speak out because I wasn't a trade unionist. Then they came for me and there was no one left to speak for me.››
ይህ አባባል ከሌላ ብሄር፣ እምነት ወይንም ሌላ ማንነት ውስጥ ነኝ ብሎ በሌሎች ላይ የሚደረጉትን ጥቃቶች በቸልታ ለሚያልፍ አሊያም ከላይ የተጠቀሱት ‹‹ማንነቶች›› ውስጥም ሆኖ ግድ ለማይሰጠው ሰው ሁሉ የሚያገለግል ነው፡፡ በሌሎች ላይ የሚደረግን በዝምታ ሲያልፍ ኖሮ በስተመጨረሻ አብሮት የሚቆም አጥቶ በብቸኝነት ለሚጨቆን ሁሉ የተነገረ ነው፡፡
በእኛ አገር በአንዱ ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ችግር ሲደርስ ሌላኛው ዝምታን ይመርጣል፡፡በእምነትም ቢሆን ተመሳሳይ ነው፡፡ ሙስሊሙ ሲነካ፣ ኦርቶዶክሱ ስለ መርህ፣ ስለመብት አብሮ አይጮህም፡፡ ሙስሊሙ፣ ፕሮቴስታንቱምና ካቶሊኩም የሚያደርገው ተመሳሳይ ነው፡፡ በተቃዋሚዎቻችን ሰፈር ደግሞ ይብሳል፡፡
በአገራችን ከሚነገሩት አሉታዊ አባባሎች መካከል ዝምታን የሚያበረታቱት በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሌሎች በሚደርስባቸው ችግር ይቅርና በራሳችን ጉዳይ ዝምታን በመምረጥ ኢትዮጵያውያን ባህላችን አድርገነዋል፡፡ ዝምታ ወርቅ ነው፣ ዝም አይነቅዝም፣ ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም፣ ዝምን ማን ወሰደው፣ ብንናገር እናልቃለን…. እና በርካቶች ዝምታን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ ከመናገር ይልቅ ዝምታን የሚመርጠው ይህ ባህላችን ‹‹መቻል!›› የሚባል ቃልንም በምሳሌነት፣ በስምነትና በሌላም መልኩ በስፋት ይጠቀምበታል፡፡ ገዳይ ባህል!
የጀርመኑ ፓስተር የናዚ ቀንደኛ ደጋፊ ነበር፡፡ መጨረሻ ግን የሂትለር ዱላ ያመራው ወደሱው ነው፡፡ እንዲያውም ስቃዩን በወጉ የሚያይለት፣ ለዚህ ስቃዩ የሚቆረቆርለት አላገኘም፡፡ ደጋፊ፣ ካድሬ…..ም ቢሆን ስለ አንድ ብሄር፣ እምነት፣ ቋንቋ፣ ሙያ፣ አሊያም ስለ ራሱ ከዚህም ወረድ ሲል ፈርቶ ዝም ቢል የመጨረሻው መዓት እሱ ላይ ማረፉ የማይቀር ነው፡፡ የአሁኑን ጨምሮ ከገዥው ጋር የተሰለፉ ፖለቲከኞች፣ ካድሬዎች፣ ደጋፊዎችና ሌሎች አካላትም በስተመጨረሻ በትሩ ያረፈው እራሳቸው ላይ ነው፡፡
በቃ! የዝምታችን አባዜ ይህ ነው ትርፉ፡፡ ልክ እንደዚያ ቄስ፣ ልክ እንደኛ ፖለቲከኞች፣ ልክ እንደአገራችን የእምነት ተቋማት፣ እንደ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ልክ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተለመደ ተግባር ዝምታ፣ ‹‹ምን አገባኝ!››፣ የፖለቲካ እሳትነት ብቻችን ያስበላናል፡፡ አስበልቶናልም፡፡ ማንም ስቃያችን ሳያይልን፣ ማንም ሳይጮህልን፣ ማንም ሳይቆምልን ያስፈጀናል፡፡ ያስጨርሰናል፡፡ ዝምታ ከወርቅ ይልቅ እንደሚያበሰብስ፣ እንደሚነቅዝና እንደሚያነቅዝ የምናውቀው ብቻችን እጣ ፈንታችን ሰንጎነጫት ነው፡፡ በጣም እጅግ በጣም ከመሸ!
ሚኒልክ ሳልሳዊ

Tuesday, December 3, 2013

በጅጅጋ የሚታየው ስረአት አልባነት ተባብሷል

December 3/2013


ህዳር (ሃያ አራ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ በማንኛውም ሰአት ዜጎች ቤታቸው በጸጥታ ሀይሎች ይፈታሻል። የጸጥታ ሀይሎችም ከሞባይል ስልክ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ እንዲሁም ገንዘብ ይወስዳሉ። የቀበሌ መታወቂያዎችን ሳይዙ ከሄዱ ደግሞ ተጠርጥረው ይያዛሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅጅጋ ለኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ በላይ የስቃይ መሬት ሆናለች ።

አንድንድ ምንጮች እንደሚሉት ችግሩን የተወሳሰበ ያደረገው አልሸባብ  በጅጅጋው ፕሬዝዳንት የግል ሞባይል ላይ የብሄር ብሄረሰቦች በአል በከተማዋ የሚከበር ከሆነ  እርምጃ እንደሚወስድ መሀላ ያለበት የዛቻ ኤስ ኤም ኤስ መላኩን ተከትሎ
ከፍተኛ ፍተሻ በየጎዳናው እየተደረገ ሲሆን ከነሱ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል አንድ የጅጅጋ ነዋሪ ጫካ ተወስዶ  ሲደበድቡት በድንገት በመሞቱ ለቤተሰቡ 50 ሺ ብር ካሳ ተሰጥቶ ሬሳው ከከተማ ውጭ እንዲቀበር ተደርጓል፡፡  ከአልሸባብ ጋር በተያያዘም አንዲት ወጣት ሴት ከአካባቢው ተወስዳ ማእከላዊ ታስራ መደፈሩዋም ታውቋል፡፡

ህዳር 29 የሚከበረውን  የብሄር ብሄረሰቦች ቀን  እንዲሳተፉ የተጋበዙ አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የካቢኔ አባላት በጸጥታና ደህንነት ምክንያት ለመሄድ አለመፈለጋቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።  ይህንን ተከትሎም ከፍተኛ ባለስልጣኖች ለካቢኔ አባላት ጠንካራ ደብዳቤ በመጻፍ በስፍራው እንዲገኙ እያዘዙ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ  በኢ.ፌ.ዳ.ሪ. የፌዳሬሽን ምክር ቤት እና በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልላዊ መንግሥት ትብብር 8ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ለውይይት የቀረበ በሚል ርእስ የተዘጋጀው ጽሁፍ ለኢሳት አስቀድሞ የደረሰው ሲሆን  በጽሁፉ ውስጥ ስለክልሉ ታሪክ አነጋጋሪ የሆኑ ጉዳዮች መካተታቸውን ተመልክቷል።

በጽሁፉ ውስጥ “የአቢሲንያ መኳንንት ወደ በረሃው የሚወርዱት ሊያጋጥም የሚችለውን የወባ በሽታ በሚክስ ደረጃ ፈጣንና ትርፋማ የከብት ዘረፋ ለማድረግ ብቻ ነው፡፡” ለምሳሌ ሽፍቶችን በማጥፋት ስም የአፄ ምኒሌክ ጦር አባላት በ1902 እ.ኤ.አ. ከ50ሺ በላይ የእንስሳት ሀብት ከማኅበረሰቡ ተዘርፎ በጅጅጋ በኩል ወደ ሀረር እንዲላክ ተደርጓል፡፡ ” ይላል።

በኀይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥትም የክልሉ ሕዝቦች እንደ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሀገሪቷ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተገለው የቆዩበት ጊዛ ነበር ካለ በሁዋላ፣ የጭቆና ቀንበራቸውን በመጫንና ሕዝቡን ለመቆጣጠር ጥቂት ለሆዲቸው ለኖሩ የጎሳ መሪዎች የተወሰነ ጊዚያዊ ጥቅም በመስጠትና በማታለል ይንቀሳቀሱ ነበር ብለዋል፡፡ የኢጣሊያ ወራሪ ኀይል ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በሚያደርገው ዝግጅት የተደናገጡት አፄ ኀይለስላሴ በመጀመርያ ጊዜ የክልሉን ታዋቂ ግለሰቦችና የጎሳ መሪዎች ሀረር ላይና በመቀጠል በቀብሪደሀር ከተማ በመሰብሰብ የክልሉ ሕዝብ ሀገሪቷን ከወራሪው ኀይሌ እንዲከላከል ጠይቀው ነበር ጽሁፉ ያመለክታል፡፡ጽሁፉ በኢህአዴግ ዘመን ለክልሉ የተሻለ እድል መምጣቱንም ያትታል።

Woyane – bringing the war to America

December 3, 2013
by Yilma Bekele 
Things come apart so easily when they have been held together with lies.’ Is what comes to mind when we see the behavior of the Ethiopian government and its response to the Ethiopian tragedy taking place in the Kingdom of Saudi Arabia.
Lies have been told to cover up previous lies that it has become a Public Relations War instead of unfolding human catastrophe. Catastrophe is a very loaded word but it explains what we know to have happened to our people in that closed kingdom. Thanks to todays technology of Internet and Mobile communications we are witnessing what could happen when cowards take charge. They could strip you of your humanity and throw you into a no man’s land between Saudi and Yemen like a piece of garbage.
Ethiopians working in the Kingdom of Saudi Arabia
We Ethiopians are beyond shock. All those that witnessed YouTube videos, digital photographs and interviews with the frightened and lost cannot but feel the agony of these young people. There are plenty of outsiders that are willing to stand with us against injustice. We need all the help we can get. A little part of the deal is that we have to start to do the job ourselves and then they would help us. It always works better that way.
Ethiopians in their hundreds of thousands travel out of the country to work. In the tens of thousands more leave thru the porous boarders and travel all over the world without papers. The last week we have been focusing on those in Saudi Arabia that found themselves stranded with no place to go. Refer to the link to read morehttp://www.tikuranbesa.com/the-kingdom-from-hell-and-ethiopians/
The Saudi Kingdom gave a seven month amnesty period for foreigners to get their paper in order or leave. November 3rd was the deadline. It is estimated that ‘nearly a million Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis and Yemenis left before the end of amnesty period.
The Ethiopian Government knew of the Saudi decision to deport undocumented people and it is fully aware of the thousands of its citizens that migrate to the Middle East without paper. It chose to ignore the problem for seven months. The Ministry of Pimping that sends thousands of citizens like any export Item and the Ministry of Foreign Affairs under Dr. Tedros Adhanom and all his Embassy and Conciliates decided to be quiet about it wishing it would go away.
The Saudi regime started rounding up undocumented workers November 4th and they had their first Ethiopian victim on November 5th. It became open season on hunting illegals’ by Saudi Security forces and vigilantes. (http://www.ethiopianreview.net/index/ )
The Diaspora that always keep one eye on Ethiopia started their protest movement right around this time. No Saudi Embassy was safe from our outrage. The Ethiopian people heard the bad news due to the relentless coverage by ESAT and our independent web sites. Initially the Ethiopian government tried to blame alarmist Diaspora for the bad news. But nothing could stay hidden in this day and age.
First they tried to ignore the impending disaster. Then they tried to find a scapegoat. Unable to deflect the news of the horrible situation they decided to use the good old trick of lying, disinformation and empty bravado to cover their impotence. Here in entirety is a speech given by the foreign Minister in front of some African meeting in Addis Abeba on November 18th three weeks into the tragedy.
“As you know from Saudi Arabia you know although it is not just deporting Ethiopians only but are deporting other citizens they call illegal and from Ethiopian side three were killed during the crackdown and not only that thousands are in camps we are trying to make it as smooth as possible because if Saudi Arabia says they are illegal we don’t mind they have homes to come to (applause) and we have already started the operation. Our command post is working and well and we have already received hundreds we are expecting tens of thousands and I would like to reassure you that we are ready to receive our fellow citizens home (applause) I had the last ten days because in family planning as we had been saying be careful girls and women I had heard straight from camps from women who are crying for help there is nothing moving than that. I am so saddened I am really depressed that is why I was not going to actually come here asking Dr. keste if he could excuse me because it is almost round the clock crisis management since this issue started but in the name of global solidarity even if we have to deport illegal we can do it smoothly because this is not a war situation it may be accepted when nations are at war to deport like this in a rapid fashion people could understand but not in peaceful situation we could have arranged it together to make the smooth transfer because as I said earlier we are ready to have our citizens so I am sorry to start with this it is something that has been bugging me for some time now ….. “
It is easy to see why things keep going wrong in our country. There is something missing in the picture. We are lacking some major ingredient that our country is made from. How did we survive as a nation state for hundreds of years? How exactly did our country stayed free while all around us were colonized by powerful European powers? It is not that we had a formidable military force or a well-developed economy. What we had was ‘that free leave me alone spirit’ and wise leaders surrounded by skilled diplomats. That is what we are missing today.
Emperor Tewodros committed suicide rather than be taken prisoner by the British force thereby denying them the reason to stay.  Emperor Minilik played the English, French, Russians even Italians like a Masinko and won at Adwa. Emperor Haile Selassie spoke at the league of nations where he said those fateful words ‘’it is us today, it will be you tomorrow.’ Accompanied by PM Aklilu Haptewold and Foreign Minister Ketema Yifru His Majesty played a central role in establishing the Organization of Africa Unity and getting Addis Abeba to be the Headquarter. Those are our accomplishments of the last one hundred fifty years.
Who is filling those shoes today? It is obvious Dr. Tedros is not a diplomat or has not been given the training and skill set to be an effective diplomat. Those dis jointed statements cannot be made by a seasoned diplomat or by someone speaking on behalf of eighty million people.
The puppet Prime Minster was not allowed to acknowledge the crisis and was seen standing for a photo opportunity with Gulf Arabs while stretching his hands for alms in the middle of this affront to people and country. Some say the TPLF party was displaying the leadership potential of the Foreign Minister preparing him for promotion. Based on his performance it looks like they picked a good time to show his short comings. He got his position not due to his ability but solely due his ethnicity.
The Ethiopian government is used to telling all kinds of tall tales to its citizens due to its monopoly of the mass Media including Print, Television, Radio, Phone, Internet and a spy in every neighborhood. But when the crisis attracts international attention this kind of ‘deception’ or ‘evading the truth’ does not work. Dr. Tedros was sent out to put lipstick on a pig. He failed miserably.
How is the Diaspora handling this cowardly attack by the Arabs against a people that have not done them any harm except do their most menial and dangerous jobs? We went out in every city that has any number of Ethiopian exiles to protest this atrocity. It was headlined by our relentless media and discussed in every coffee shop.How is the Diaspora handling this cowardly attack by the Arabs
It is definitely a good thing that thousands of miles from home that we still feel a strong affinity to people and country. The anger was genuine and the pain was deeply felt by all. We are a unique people that the love for our homeland seems to have been engrained in our DNA if that at all is possible. I went out on a protest in San Francisco with about five hundred of my people and felt genuinely invigorated.
I also noticed something unique during this protest which I have not come across before. The protest call was scheduled to happen on Monday and I received a text message with the pic of the post card on Saturday. I have heard that there was a tele conference called to organize a protest and I was surprised by the speed they were working. It was not that group. The Post card does not have a contact number or a web address. ‘Ethiopian Community and Cultural center in Oakland’ is mentioned as a sponsor but no one seems to know who they are. Some people were confused by the proximity of the name to the real ‘Ethiopian Center’ they know and are familiar with. I was also surprised by the sameness of all the post cards printed in North America. It is obvious it was designed by the same person or group. The use of shocking images, the color combination and the title are a giveaway.
What was most surprising was the sheer number of post cards and the speed they spread in the community. Every Ethiopian and Eritrean center including Orthodox Churches, Mosques and Evangelical Churches were covered. There is nothing like having frightened and blackmailed cadres to do your menial job.
Someone called for a protest and there was nothing to do but go out and give a hand. I was very curious. Slowly people started to show up. It is as if we were all told to bring the real Ethiopian flag with us. A few ladies were wearing it as a head scarf while some had it around their neck. The men were wearing it on their hats, as a T shirt while a few were carrying the mother of all Ethiopian Flags about twenty feet long. One hour into the event no one that claims responsibility has shown up but our number was increasing by the minute. Around 12 PM a few young people showed up with megaphone and we started congregating around the loud device.
The speech being given by the still unknown organizers was laying the ground for our slogans. The target was to be Saudi Arabia and our beef with them was regarding the treatment of our people. What was said repeatedly was since this is strictly about ‘human rights’ thus no ‘politics’ should be allowed to contaminate the atmosphere. Mentioning the role of the Ethiopian government was a cause to boo. At long last things were beginning to make sense. The haste in organizing this fake protest was becoming clearer by the minute.
Why would anyone want to circumvent this noble cause most of us went out to show solidarity with our people is a valid question? The majority that showed up were genuinely concerned about the condition of their people and with good Ethiopian heart they came out to express their deeply felt sadness. Unfortunately it is sad to see a very small number that were used to squander this golden opportunity that could have been used for greater good. Why? What would they benefit?
The answer is intertwined with the nature of the government in power and how they have managed to use greed as a weapon. Up until now Woyane has used its sympathizers to silently infiltrate and create chaos from within. The two favorite recipients of this were the Political Party support groups and our Church. It is sad to see our community being taken over or made a subsidiary of TPLF. This occasion was the crowning moment of all that work. Our people at home are faced with an overwhelming and cruel force that terrorizes their daily life and today some in the Diaspora are economic prisoners to be called upon to serve their master in times like this.
I was in complete awe watching the protest march from the side by the actions of the masterful operators at work. The way they played the crowed reminded me of Jimmy Hendricks on Guitar, Mulatu Astatke on keyboard, Shambel on Masinko, Tilahune, Teddy with Gigi as vocalists – they were that good.
What was achieved is a good question. As a diaspora activist I learnt never to discount the ingenuity of Woyane as an enemy. This fifth column (http://en.wikipedia.org/wiki/Fifth_column ) they unveiled took a long time to build. All the registration for land, the requirement of personal documents including finger print was part of the process. Today every city and town has its own kebele rep just like in mother Ethiopia. For us it was a wake up moment and for Woyane it was a champagne time.
One thing for certain is that their action was a betrayal of our people and country. Our protests are not random noises but a thought of calculated acts to achieve a certain gain. Regarding our current problem in the Middle East our aim was:
  • Stop the abuse immediately while we search for lasting solution.
  • Organize some kind of entity to research and offer options.
  • Work with the UN, Red Cross and other organizations to look for safe locations for the political refugees and resettle those who want to return to Ethiopia.
  • Put pressure on the Ethiopian government to allow political freedom.
The interference by the Woyane regime and the Banda like work by our own friends, family and neighbors sabotaged all this important work. The problem is still with us. Despite the lie by the Ethiopian government there are still tens of thousands stranded in Saudi Arabia and dumped in Yemen. Those that called for this quick response are nowhere to be seen today. Their job is done, after all it was never about stopping the atrocity but it was all about shielding the regime. Check out the protest in your city and notice that there is no follow up work or any attempt to continue the work till the problem is solved. What the regime wanted was for us to go out and vent our displeasure on the Arabs and go home and that was the end of the matter.
Our work is still not done. We should go back and start from scratch and re organizes our response. We have learnt a lesson. Woyane has arrived in America in full force. The sleeper agents, the morally deficient characters they have recruited, the economically challenged cheap Hodams they have bought are not going to be a push over. Afraid to be unmasked they would try any means to saw dissent amongst us. It is time to recognize the shifting situation in our movement and act accordingly.
Our people still are not comfortable asking questions, digging deep and researching before making a decision. Our culture does not encourage curiosity and we abhor reading, learning and referring to experts. The last weak we saw all our weaknesses when we saw people following like cattle and afraid to even ask who is in charge here and who elected you to that position. We should never follow without asking by whom and for what. Like we shouldn’t sign a paper without reading it first we should never follow someone without knowing what the game plan is all about. It is time to fight back intelligently not emotionally.
“Things come apart so easily when they have been held together with lies.”
― Dorothy AllisonBastard Out of Carolina