Thursday, November 24, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በወያኔ ጦር ላይ በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን በመቀጠል ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ፡፡

November 24,2016
November 24, 2016
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበልባል የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለሊት ጎንደር ዳንሻ ከተማ ልዩ ስሙ አዲስ አለም በተባለ ቦታ ሰፍሮ ከሚገኝ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ድንገተኛ ማጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ አጥቅቶ ተሰውሯል፡፡ በወሰደው ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃም 15 የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን በመግደል ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ ማቁሰሉን አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ከስፍራው ባደረሰን ዘገባ አስታውቋል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጥቃቱን በመቀጠል ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም በአብደራፊ ከተማ ዙሪያ በህወሓት መከላከያ ሰራዊት ላይ ተመሳሳይ የደፈጣ ጥቃት የሰነዘረ ሲሆን ባደረገው ሰፊ የማጥቃት እርምጃም 25 በመግደልና 17 በማቁሰል በቅጥረኛው የህወሓት ጦር ላይ ጠንካራ ክንዱን በማሳረፍ የበላይነትን ተጎናፅፎ የህወሓት ቅጥረኛ ወታደሮችን እንቅስቃሴ በመግታት መበታተን እንደቻለ ሪፖረተራችን አክሎ ገልጿል፡፡
ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እየፈፀመ ያለውን ቆራጥ ተጋድሎ ጥቃቱ በሚፈፀምበት ቦታ ሁሉ ሙሉ በሙሉ የህዝብን ድጋፍ እያገኘ ሲሆን የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ትልቅ ጉልበት እንደሆነው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ትንሳኤ እስኪሆን ድረስም ጀግኖች የአርበኞች ግንቦት 7 ነበልባል ሰራዊት ወደፊት በመግፋት በተግባር የኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ፡፡
ag7-nov-2016-1
ag7-nov-2016-2
ag7-nov-2016-3
ag7-nov-2016-4

Sunday, November 20, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ከመቀሌ ከተላከ ኮማንድ ፖስት ግብረኃይል ጋር ተዋግቶ ድል ተጎናጸፈ

November 20,2016
arebegnoch


















ህ ቀጥሎ እንደወረደ የሚነበበው ዜና አርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ ከፎቶግራፍ ጋር አስደግፎ የዘገበው ዘገባ ነው::

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለው ቦታ ከመቀሌ የተላከ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይል ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ድል ተጐናፅፏል።
ይህ ከመቀሌ የተንቀሳቀሰው የወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሃይል ዋና ተልዕኮ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊትን እንቅስቃሴ ለመግታት ታስቦ ሲሆን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በ56 መኪኖች አጓጉዞ በቃፍቲያ ሁመራ ልዩ ስሙ ማይነብሪ በተባለ ቦታ ቢያሰፍርም ለሀገራቸውና ህዝባቸው ሲሉ ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል የማይሰስቱት የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በከፈቱት ድንገተኛ ማጥቃት 92 በመግደልና 65 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማስመዝገባቸውን ከስፍራው የሚገኘው አርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን ባደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እንቅስቃሴን ለመግታት የተንቀሳቀሰውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስትን ይመሩ ከነበሩ መካከል 5 አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል መቶ አለቃ ጣዕመ የሚባል እንደሚገኝበትም ታውቋል።
በተያያዘ ዜና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት ህዳር 8 ቀን 2009 ዓ.ም በቃፍቲያ ሁመራ ሩዋሳ አካባቢ ማይጐነጥ ልዩ ስሙ ማይቆማ በተባለው ቦታ ሰፍሮ ከሚገኘው የ24ኛ ክፍለ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ አንድ ብርጌድ ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከማውደሙም በተጨማሪ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ አካባቢ በተደረገው ውጊያ የወያኔው የ24ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጀግኖች የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም ተስኖት እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
በእለቱ በተደረገው ውጊያ 120 የወያኔ መከላከያ ሰራዊትን በመግደልና 80 በማቁሰል በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ከባድና ቀላል ተተኳሽ መሳሪያዎችን ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረካቸውንም ሪፖርተራችን ገልጿል።
በውጊያው እለት የቆሰሉ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ብዛት ቁጥር ስፍር የሌለው ከመሆኑ የተነሳ ሁመራ የሚገኘው ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁንና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸውን ደግሞ ወደ ጐንደር ሆስፒታል በመላክ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ሰራዊት ባደረገው ተከታታይ የማጥቃት ርምጃ የአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ እጅጉን ከመደሰቱም በተጨማሪ ከትግሉ ጐን ለመሰለፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት እየገለፁ እንደሚገኙም ታውቋል።
arebegnoch2
የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣናትም በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎችን አገዛዙን ለመፋለም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ አካባቢውን በመውረር ህብረተሰቡ ከቤቱ ወጥቶ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ሲሆን፤የሞቱ የሰራዊቱ አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳያይባቸው የራሳቸውን ሰዎች በመመልመል እንዲቀበሩ እያደረጉ መሆናቸውን ሪፖርተራችን አክሎ ገልጿል።
በደረሰባቸው የሰው ህይወትና የንብረት ኪሳራ እጅጉን የተደናገጡት የህወሀት አገዛዝ ባለስልጣናትም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ግብረ ሀይልና በ24ኛ ክፍለ ጦር ላይ ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሚሰነዘረው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉና ፋታ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በአካባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮችን በማሰማራት አሰሳና ቅኝት ሲያደርጉ እንደነበረ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት እስከአሁን ባደረጋቸው ውጊያዎችና ባስመዘገባቸው ድሎች በመደሰት በአካባቢው የሚገኙ የሚሊሸያ ታጣቂ ሀይሎች ከወንድሞቻችን ጋር ውጊያ አናደርግም በማለት በአገዛዙ ላይ እንዳመጹና ብዛት ያላቸው የሚሊሸያ አባላትም ከአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጋር መሰለፋቸውን ከስፍራው የደረሰን የአርበኛ ታጋይ ሪፖርተራችን መረጃ ያስረዳል።