Wednesday, July 16, 2014

ፍርድ ቤቱ በእነ ሐብታሙ ጉዳይ ጠንከር ያለ ትዕዛዝ አስተላለፈ

July15/2014
ከዳዊት ሰለሞን
የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገ መንግስቱና የጸረ ሸብር አዋጁ በሚያዙት መሰረት እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ እንደሚገባቸውና በቤተሰቦቻችውና በጠበቃቸው መጉብኘት መብታቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ጠበቆቻቸው ያልተሟሉላቸው መብቶች በፍርድ ቤት ጣልቃ ገብነት ይከበሩ ዘንድ በዛሬው ዕለት ክስ መስርተው የማዕከላዊ አመራሮች ለቀረበባቸው ክስ በአካል በመገኘት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሃላፊዎቹ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ምላሽ ሰዎቹን ፍርድ ቤት በ2/11/2006 ዓ.ም ማቅረባቸውን ጠቅሰዋል፡፡የታሳሪዎቹ ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉና አቶ ገበየሁ ደምበኞቻቸውን ማግኘት አለመቻላቸውን ፍርድ ቤት ሲቀርቡም እንዲያውቁ አለመደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ጠበቆቹ ደምበኞቻቸውን ማየት እንዲፈቀድላቸውና በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ እንዲደረግ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አቤት ብለዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካደመጠ በኋላ ታሳሪዎቹ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ እንዲደረግና ከጠበቆቻቸው እንዲመካከሩ ይደረግ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ፍርድ ቤቱ ከዚሀ በተጨማሪም በማዕከላዊ እንደሚገኙ የተነገረላቸውን ታሳሪዎች የፊታችን አረብ 4፡00 እንዲቀርቡ ሲል አዟል፡፡የማዕከላዊ ኃላፊም በፍር ቤቱ የተሰጠውን ትዕዛዝ መፈጸሙን እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡10557351_10202411521670248_5400861717310665444_n


No comments: