ደመቀ የኔአየህ
July 23, 2014
የዛሬ ሦስት ወር አካባቢ የ ወያኔ መንግስት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊከፍት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ከውስጥ የተላከልኝን መረጃ ማስነበቤ ይታወሳል።
የጦርነቱም ዋና አላማ በኤርትራ ውስጥ ያሉትን የነፃነት ታጋዮችን እንቅስቃሥሤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማምከን የሚል ነው። የዚህ ጦርነት ዋና አላማ በስልጣን ላይ ያለውን የሻብያ መንግስት በመጣል በኢትዮጵያ ውስጥ ሲያዘጋጁቸው የኖሩትን የ ኤርትራ ተቃዋሚወች ወደ ስልጣን በማምጣት በኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን ማንኛውም አይነት የትጥቅ ትግል ቦታ ማሳጣት ነው። ለዚህም ይረዳሉ ተብለው በ10 ሺወች የሚሆኑ ኤርትራውያንን በኢትዮጵያ ዪኒቨርስቲወች ውሥጥ ሲያሥተምር ቆይቱል። እነዚህ ተማሪወች ከአካዳሚክ ትምህርት ባሻገር በአመት ሶሦት ጊዜ የ መንግስት አስተዳደር፣ የፓለቲካ እና የደህንነት ትምህርቶችን ሲማሩ ቆይተዋል።
ይህ ጦርነት ግቡን ይምታላቸውም አይምታላቸውም እንደተጠበቀ ሆኖ በቅርብ ጊዜ ጦርነቱ ሊጀመር መሆኑን መረጃወች ይጠቁማሉ።
ይህን የታሪክ አጋጣሚ የኢትጵያ ህዝብ እንዴት ሊጠቀምበት እንደሚችል አይታወቅም። በወያኔ ግምት የኢህዴግ ሰራዊት በድል ያጠናቅቃል የሚል እምነት እንዳለው ያመለክታል። ህዝቡ ድጋፍ አደረገም አላደረገም ሰራዊቱ አሁን ባለው አቁም ይህን አደራ በአሸናፊነት እንደሚያጠናቅቅ እምነት እንደተጣለበት ያመለክታል።
የኢህዴግ ሰራዊት ከተቁዋሚ ጎራ ይሠልፍ ይሆን የሚለውንም ሃሳብ አውጥተው አውርደው አስበውበታል። በእነሱ እምነት ይህ ሃሳብ ውሃ የሚቁጥር ሆኖ አላገኙትም።
አይቀሬው ጦርነት ሊጀመር ጫፍ ላይ መሆኑን በ ያዝነው ወር በቀን 18 የአሜሪካ የ አቬሽን ባለስልጣን ያወጣውን የ ሰላማዊ አውሮፕላን በረራ እገዳ አንድ ትልቅ ፍንጭ ነው።
በተጨማሪም በየወረዳው የተጀመረው የውትድርና ምልመላ አንድ ሌላ ተጨማሪ ፍንጭ ነው።
No comments:
Post a Comment