Friday, December 27, 2013

ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ !

December 27/2013

"የሳውዲ መንግስት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ሳውዲን ለቀው አንዲዎጡ ያስተላለፈውን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስለወ መስሪያ ቤቶች ዜጎች ሀጉን አክብረው ወደ ሃገራቸው እንዲወጡ
ያስተላለፉትን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች በመረዳት ወደ ሃገር ለመግባት ወደ ሽሜሲ መጠለያ በመሄድ እጃችን የሰጠን ዜጎች እየተንገላታን ነው! " በማለት ሮሮና ቅሬታቸውን ያቀረቡ ወገኖች መጠለያ እንደገቡ በኢትዮጵያ መንግስት የመጓጓዣ ሰነድ የተሰጣቸው ቢሆንም የሳውዲ ፖስፖር ሃላፊዎች የቀረበላቸውን ሰነድ በማጣራት የመውጫ ሰነድ ለመስጠት አንግልት አያደረሱባቸው መሆኑን ገልጸውልኛል። ጉዳያቸውን ለማስፈጸም በአውቶቡስ ላይ እና በመጠለያው ግቢ ውስጥ ተበትነው በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ የገለጹልኝ እኒህ ወገኖች የአቅመ ደላማ ሴቶችና ህጻናትን እንግልት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው የሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ትብብር ያደርጉላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

እኒሁ ሮሯችን ለሚመለከታቸው እንዳሰማ የተማጸኑኝ ወገኖች ወደ ጅዳ ቆንሰል ሃላፊዎች ስልክ ደውለው ስልክ ስለማያነሱ ወደ እኔ መደወላቸውን የገለጹልኝ ሲሆን ወደ ሃገር ግቡ ተብለን ወደ ሃገር እንግባ ባልን እንግልት ሊደርስብን አይገባም ሲሉ " አሁን በደል እያደረሰብን ያለው ሳውዲ ኢሚግሬሽን መፍትሄ እንዲሰጠን ዲፕሎማቶች የተቻላቸውን ያድርጉልን! " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። በሌላ በኩል ወደ መጠለያው ገብተው አስፈላጊውን ሰነድ ያሟሉ አንዳንድ ነዋሪዎች መካከል ሻንጣችን ጠፋብን የሚሉና ከአንድ ሻንጣ በላይ እንዳይዙ የተከለከሉ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
ጉዳዪን ለማሳወቅና ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ አቶ ዘነበ ከበደ እና ወደ ምክትላቸው አቶ ሸሪፍ ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ ዛሬም አልተሳካም!
ሰላም
ነቢዩ ሲራክ

No comments: