December 11/2913
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥፋት ተከትሎ በፌስቡክ እና በትዊተር አማካኝነት ለሕዝብ መረጃ መስጠታቸው በኢሕአዴግ ባለስልጣናት ዘንድ እንዳልተወደደና እንደተተቹበት ለመንግስት ቅርብ እንደሆነ የሚነገርለይ ድሬ ቲዩብ የተባለው ድረ ገጽ ዘገበ። “የዶ/ር ቴዎድሮስ ግልጽና ተወዳጅ የዲፕሎማሲ ስልት በፖለቲካ ጓዶቻቸው ዘንድ እንዳስወቀሳቸው ተነገረ” ሲል ዘገባውን ያሰፈረው ድሬ ቲዩብ ዶ/ሩን በማሞካሸት ባቀረበው ዘገባው “አብዛኛው ፖለቲከኛጋ የማይታይ ቀለል ብሎ የሚያሸንፍ ስብዕና (Disarming Personality) የተላበሰና እንደሌሎቹ የተጠና ፖለቲካዊ ዲስኩር የማይደረድር፤ ካለበት የስልጣን ከፍታ አንጻር እሱን ማግኘት አይከብድም…በለውጥ ሀይል የተሞላና አብረውት ቢያወጉ የማይሰለች ተወዳጅ ነው የሚሉት ብዙዎች ናቸው የሚለው ዘገባ…አሁን አሁን ግን ይህ ባህሪ በፖለቲካ ጓዶቻቸው እንዳልተወደደላቸው ነው የሚነገረው፡፡” ሲል ገልጾታል።
ድረ ገጹ ጨምሮም “በሶሺያል ሚዲያው ንቁ ተሳታፊ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ በሳዑዲ ተመላሾች ዙሪያ በዋናው ሚዲያና በሶሺያል ሚዲያው ላይ በተደጋገሚ መታየታቸውና የነበራቸው ንቁ ተሳትፎ ከሁለት ሳምንታት በፊት በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ “ክስተቱን ለግል ዝና ማግኛነት አውለኸዋል” በሚል በፖለቲካ ጓዶቻቸው አስወቅሷቸዋል፡፡” ካለ በኋላ በተጨማሪም “በስብሰባው ወቅት ካስወቀሷቸው ጉዳዮች ሌላኛው፣ ለሳዑዲ ተመላሾች ማቋቋሚያ ባለሀብቶች የ7 ሚሊየን ብር እርዳታና ከተመላሾቹ የተወሰኑትንም በመቅጠር የስራ ዕድል ለመስጠት የተስማሙበት ጉዳይ ሲሆን፤ ይህ የዶ/ር ቴዎድሮስ አካሄድ ግን በመንግስት ለተመላሾቹ የተያዘውን በአነስተኛና ጥቃቅን የማደራጀት እርምጃ ይቃረናል በሚል ነበር በፖለቲካ ጓዶቻቸው ያስወቀሳቸው፡፡” በማለት የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩንና በድርጅታቸው ውስጥ የተፈጠረባቸውን ወቀሳ ዘግቦታል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቀጣዩ ምርጫ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለዚህም ነው በግል ዝና ግንባታ ላይ የተሰማሩት የሚሉ አስተያየቶች በተደጋጋሚ ሲደመጡ መቆየታቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment