Oktober 2,2014
• ትክክለኛውን የቀጠሮ ቀን ለማወቅ አልተቻለም
(ኮማንደር ተክላይ ጥቅምት 20 ነው ሲሉ፤ ፖሊስ ጥቅምት 22 ነው ብሏል)
ዘሬ መስከረም 22/2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ኃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ የሸዋስ አሰፋ፣ የአረና ም/ የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ችሎት ያለ ጠበቃ ተካሄደ፡፡ ችሎቱ በዝግ የተካሄደ በመሆኑ መቼ እንደተቀጠረ ያልታወቀ ሲሆን ችሎቱ ግቢ ሆኖ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ የችሎቱን ውሳኔ ከመዝገብ ቤት ጠይቆ እንዳይረዳ በፖሊስ ተከልክሏል፡፡ የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ቀጠሮውን ለማጣራት ባደረገው ጥረት ፖሊስ ቀጠሮው ጥቅምት 22 ነው ሲል ኮማንደር ተክላይ ቀጠሮው ለጥቅምት 20 እንደሆነ ገልጸውለታል፡፡
ችሎቱ 8 ሰዓት ላይ ይደረጋል ተብሎ የነበር ቢሆንም የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀብታሙ አያሌውና የአንድነት ም/ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዳንኤል ሺበሽ 10 ሰዓት እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ሸዋስ አሰፋና የአረና ም/የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ 10፡30 አካባቢ ላይ ወደ ችሎት ገብተዋል፡፡
የዛሬው ችሎት ከእስከ ዛሬው በተለየ በርካታ ትዕይንቶች የታዩበት እንደሆነም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ከእነዚህም መካከል እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች የበለጠ ህዝብ የተገኘበት ሲሆን ህዝቡም ለመጀመሪያ ጊዜ እየተፈተሸ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስካሁን ከተደረጉት ችሎቶች በተለየ ከፍተኛ ጥበቃ ሲደረግ ታይቷል፡፡ በችሎቱ የሰማያዊና የአንድነት ሊቀመናብርት፣ ዶክተር ያቆብ ኃይለማሪያምን የመሳሰሉ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የተለያዩ አገራትና ተቋማት ተወካዮች፣ የተለያዩ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም ዜጎች በችሎቱ ግቢ በመገኘት ለታሳሪዎቹ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ጋዜጠኞች ገብተው ችሎቱን መከታተል እንደሚችሉ ተገልጾ የነበር ቢሆንም በኋላ ግን እንዳይገቡ ተከልክለዋል፡፡
በተመሳሳይ የአራቱ የፖለቲካ አመራሮች ጠበቆች የተለያየ ምክንያት እየተፈጠረ ደንበኞቻቸውን እንዳያገኙ መደረጋቸው፣ ማስፈራሪያ የሚደርስባቸው በመሆኑና ህጉ የማይከበር በመሆኑ በጊዜ ቀጠሮ ለደንበቻቸው መቆም ስለማይችሉ ለጊዜው ለአመራሮቹ የሚያደርጉትን ጥብቅና በማቆማቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ጠበቃ ቀርበዋል፡፡
ችሎቱ 11፡30 አካባቢ ያበቃ ሲሆን አጋርነቱን ለማሳየት ወደ አራዳ ምድብ ችሎት ያቀናው ህዝብ ታሳሪዎቹ ከችሎቱ ግቢ ከወጡ በኋላ እስኪርቁ በር ተቆልፎበት ችሎቱ ግቢ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ

No comments:
Post a Comment