Friday, September 26, 2014

የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ተሰወሩ

September 26,2014
የአንድነት ፓርቲ የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳግም ተሰማ ከትላንት መስከረም 15 ቀን ጀመሮ መሰወራቸዉን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። « ዳግም፣ ድህንነቶች መኖሪያ ቤቱድረስ (ኦሎምፒያ) ሰሞኑን በዲኤክስ መኪና መጥተው ያነጋሩትንና ያስፈራሩትን አውግቶን ነበር፡፡ ይህንን ሲያወጋን ግን በራስ መታማመኑ እና ድፍረቱ ከራሱ ጋር ሆኖ ነው፡፡ ለዛሬጥዋት ፖሊስ ጋር ተጠርቶ ቀጠሮ ቢኖርበትም እሱ ግን ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ ሃሳብ ያካፍለን የነበረው በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች ነበር፡፡ ዳግም ጎበዝ፣ ረጋ ያለ፣ አስተዋይና ራሱንበዕውቀት ለማበልጸግ የሚጥር ወጣት መሆኑን አውቃለሁ» ትላንት ከአዲስ አበባ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እንደጦመረው ፖሊሲ በአቶ ዳግም ላይ ከፍተኛ ማስፈራራትና ክትትል ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያደርግ ነበር።
አቶ ዳግም ታስረው እንደሆነ ለማጣራት በተደረገው ሙከራ፣ አቶ ዳግም ቢያንስ አዲስ አበባ ባሉ እሥር ቤቶች መታሰራቸውን የሚያረጋገጥ ምን መረጃ አልተገኝም።
አቶ ዳግም መሰወራቸው እንጂ መታሰራቸው ገና ባይታወቅም፣ በፖሊስ መጠራታቸዉና ወከባ በርሳቸው ላይ መፈጸሙ ፣ አገዛዙ በአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ ጥንካሬ መደናገጡን  ፣ ይደረጋልተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የተመታና የተሰባባረ፣ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የማይችል፣ የአንድነት ፓርቲ እንዲኖር ለማድረግ ፣ የአመራር አባላቱን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ፣  ከወዲሁ ሆን ብሎእየስራ መሆኑን አመላካች ነው።
አቶ ዳግም ተሰማ የሚመሩት የኦዲት ኮሚቴ፣  በቅርቡ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ ሪፖርት አቅርቦ የነበረ ሲሆን ፣ ኮሚቴው ያቀረበዉን ሪፖርት ምክር ቤቱ እንዳጸደቀው፣ በስፋራውየነበሩ የአንድነት አመራሮች ይናገራሉ።
ከዚህ በፊት በነበራቸው  ሃላፊነት ተገምግመው  “ኤፍ” ያገኙትን ኢንጂነር ዘለቀ ረዲን፣ የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሌሎች በርካታ ብቃት ያላቸው ወጣት አመራሮች እያሉ፣  ለምንምክትል ሊቀመንበር አድርገው እንደሾሙ በመጠየቅ፣  የኦዲት ኮሚቴው ከፍተኛ  ትችት በሊቀመንበሩ ላይ አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩም በኦዲት ሪፖርቱ ደስታኛ እንዳልነበሩም የደረሰን ዜናያመለክታል።
በአቶ ዳግም ላይ ፖሊስ ክትትል ማድረግ የጀመረዉም፣ የሚሰበስቡት ኮሚቴ የኦዲት ሪፖርት ካቀረበ በኋላ እንደሆነ ፣ ከዚያ በፊት ብዙ በፖሊስ ራዳር ያለነበሩ የአንድነት አመራር አባል እንደሆኑም ለማወቅ ችለናል።
ከሶስት ወራት በፊት የታሰሩት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ንቅናቀ ሰብሳቢ፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  በአንድነት ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ዉስጥ ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ የዉጭግንኙነት ስራቸውን መስራት እንዳልቻሉና መቀየር እንዳለባቸው ሐሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ፣ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ከስህተቶቻቸው ተምረው ሥራ  ላይ እንዲያተኩሩከማድረግ ይልቅ፣ ጭራሹን  አቶ ሃብታሙ አያሌውን ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊያባርሩ እንደነበረም ለመረዳት ችለናል። ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት «የሚሰራና የሚንቀሳቀስ አመራር እንዴትእናስወጣለን ? » በሚል የኢንጂነር ግዛቸው ዉሳኔ እንዲቀለበስ አደረጉት እንጂ፣ አቶ ሃብታሙ ከአንድነት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊባረሩ ይችሉ ለማወቅ ችለናል።
እንደዚያም ሆኖ ብዙም አልቆየም ፣ ከኢንጂነር ዘለቀና ኢንጂነር ግዛቸው ጋር ክርክር የገጠሙት አቶ ሃብታሙ አያሌው በሕወሃት/ኢሕዴጎች ለመታሰር መብቃታቸውም የሚታወቅ ነው።
በአንድነት የምክር ቤት ስብሰባ ኢንጂነር ግዛቸውና ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ያልተደሰቱበትን  ሪፖርት ፣ አቶ ዳግም ተሰማ የሚመሩት የኦዲት ኮሚቴ ባቀረበ በጥቂት ሳምንታት ዉስጥ፣ አቶ ዳግም ተሰማመታሰራቸው፣  ብዙዎች በኢንጂነር ዘለቀና በኢንጂነር ግዛቸው ላይ ጥያቄ እንዲጠይቁ እያደረጋቸው ነው።
በተያያዘ ዜና የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ፣ ትግሉን ወደ ኋላ እየጎተቱት በመሆናቸው፣ ለአገርና ለትግሉ ሲሉ፣ ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው እንዲለቁ፣  በፓርቲዉ ዉስጥ ባሉ አባላትእንዲሆም ከፓርቲው ዉጭ ባሉ ለፓርቲው ቅርበት ባላቸው የተከበሩ ምሁራን ተማጽኖ እየቀረበላቸው እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።
ኢንጂነሩ በተለያዩ ሜዲያዎች «ለወጣቶች ሃላፊነቴን ነገ ለማስረከብ ዝግጁ ነኝ። የስልጣን ጥማት የለኝም»  በአንድ በኩል እያሉ፣ በሌላ በኩል ግን አብረዋቸው በታገሉ፣ አብረዋቸው ቃሊት ታስረውበነበሩ አንጋፋ ምሁራን ሲለመኑም «ከስልጣኔ  ፍንክች አልልም» የሚል አቋም እንደያዙም ለማረጋገጥ ችለናል።
ኢንጂነር ግዛቸው ሃሳባቸውን ካልቀየሩ በፍቃዳቸው በክብር የማይለቁ ከሆነ፣ በድርጅቱ ሕግና ደንብ መሰረት፣ በምክር ቤቱ ዉሳኔ ከሃላፊነታቸው ሊነሱ የሚችሉበት ሁኔታም እንዳለም የሚገልጹአንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ነው።

No comments: