September21,2014
(አምዶም ገብረስላሴ – ከመቐለ)
በመቐለ ከተማ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በመሬት የነባር ይዞታ ለማረጋገጥ ተብሎ በተጠራ ስብሰባ በተፈጠረ ኣለመግባባት ተከትሎ 4 ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።
ሓሙስ 08 / 01 / 2007 ዓ ም የሓውልቲ ክፍለ ከተማ ከ 1 ሺ በላይ የኣካባቢው ኑዋሪዎች “….የነባር ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጣቹሃል…” ብለው ከሰበሰቡ በሁዋላ 200 ሰዎች ማረጋገጫ ሰጥተው የተቀረው “..ኣይመለከታቹም..” ብለው ሲመሉሷቸው በርካታ እናቶች በማልቀሳቸው ምክንያት ኣስተዳዳሪዎቹ ፖሊስ በመጥራት ድብደባ በማድረሳቸው ያካባቢው ወጣቶችም ድብደባው ለመከላከል መኩረዋል።
በዚህ መሰረት 20 ሰዎቹ በክፍለ ከተማዋ ኣስተዳዳሪ ኣቶ በርሀ ፀጋይ የእስር ትእዛዝ በማውረድ እንዲታሰሩ ኣድርገዋል።
የክፍለከተማዋ ኣስተዳደር ሆን ብሎ ያዘጋጀው ድራማ እንደነበርና ድብደባው ለመከላከል የመኮሩት ወጣቶች የቪድዮ ካሜራ ባለሞያ ኣዘጋጅተው ጠብቀው ቀረፃ በማካሄድ የውንጀላ ሴራ ሊጠቀሙበት ኣስበዋል።
የመቐለ ከተማ ኣስተዳደር በመሬት ኣስተዳደር ጉዳይ ዜጎች መደብደብ፣ ማሰር፣ ኣስለቃሽ ጋዝ በመርጨት፣ ንብረታቸው በ ኣፍራሽ ሃይል ማውደም የተለመደ ተግባሩ መሆኑ የሚታውቅ ነው።
No comments:
Post a Comment