August 9/2014
“መኢአድ ጠንካራ ድርጅት ነው።” በድንገት መኢአድ ቢሮ የደረሱ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከኢሕአፓ ሕዋስ (ሴል) በመቀጠል በብቸኝነት ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጥበቅ ታላቅ ስራዎችን የሰራው እና እየሰራ ያለው እንዲሁም በ97 ምርጫ የቅንጅት ማሸነፍ ታላቅ አስታውጾ የነበረው የፕሮፌሰር አስራት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በትላንትና እለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባስተላለፈው የትግል ጥሪ የተደናገጡት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶችም እንደሆኑ ከኤምባሲው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በትላንትናው እለት የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በጋር በሰጡት መግለጫ መኢአድ ድርጅታዊ መዋቅሩን ተጠቅሞ የጎዳና ላይ አመጽ እንደሚጠራ እና ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ ለምርጫ ቦርድ እና ለወያኔም ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወቃል። ይህ ያሰጋው ወያኔ እንደለመደው ሲራወጥ ሁኔታው እና የመኢአድ ጥንካሬ ያሰጋቸው የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በዛሬው እለት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆነችዋ የኤምባሲው ዲፕሎማት በመኢአድ ጽ/ቤት በመገኘት አመራሮቹን ማነጋገሯ ታውቋል።
ከጠዋቱ በአምስት ሰአት በአስቸኳይ የፖለቲካ ጉዳይ በመግለጫው ዙሪያ ማብራሪያ ለመጠየቅ መኢአድ ቢሮ የመጡት እና በአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ሴት የተመሩት ዲፕሎማቶች የመኢአድን ጠንካራ ፓርቲነት መስክረዋል። በወቅቱ በውይይቱ ላይ እንዲገኙ የተጋበዙት አንድነቶች ኢንጂነር ግዛቸው ብቻቸውን በመምጣት ያልተጠየቁትን ሲቀባጥሩ መስተዋላቸውን ከዲፕሎማቶቹ ጋር በቦታው የነበሩ የኤምባሲው ምንጮች ገልጸዋል።
የመኢአድ አመራር በውይይቱ ወቅት በሃገሪቱ ያሉትን ችግሮች እንዲሁም ምርጫ ቦርድ መኢአድን ለማፍረስ እየሰራ ያለውን ደባ እና መንግስታዊውን በፓርቲዎች ላይ የሚደረገውን ሽብር በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። አንዳንድ ለመኢአድ እና ለአንድነት የሚቀርቡ ምንጮች ወያኒ አንድነት ውስጥ ባሉ ሰርጎገቦቹ ን ተጠቅሞ ከውህደቱ በኋላ የመኢአድን ድርጅታዊ መዋቅር ለማፈራረስ ደባ እንደወጠነ ሲጠቁሙ ውህደቱን እንደማይፈልገው ተደርጎ የሚወራው ለይምሰል መሆኑን አክለው ይገልጻሉ። ወያኔ የመኢአድ ድርጅታዊ መዋቅር ክፈረሰለት እፎይ እንደሚል ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይናገራሉ።#ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment