August16/2014
አርአያ ተስፋማሪያም
የሻዕቢያ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ጄ/ል ስብሃት ኤፍሬም ባለቤት ታጋይ ሩት ሃይሌ ትባላለች። ሩት ሃይሌ እና የሕወሓቱ ሽማግሌ ስብሃት ነጋ የቅርብ ስጋ ዝምድና እንዳላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።
ሌላው ዶ/ር ሰለሞን እንቑይ ይጠቀሳሉ፤ ፓርቲውን የተቀላቀሉት በ1983ዓ.ም ሲሆን ቀደም ሲል በለንደን ይኖሩ ነበር።በወቅቱ የ «ማ.ረ.ት» ሃላፊነት ቦታ ተቆናጠጡ። በ1993ዓ.ም የትግራይ አፈ-ጉባኤ ተደርገው ተሾሙ፤ የድርጅቱ ማ/ኰሚቴ አባልነትን ጨምሮ 5 ቁልፍ ሃላፊነቶችን እንዲጨብጡ ተደረገ። በ1994ዓ.ም መጋቢት ወር ከፓርቲው ልሳን ጋር በትግርኛ ቁዋንቑ ባደረጉት ቃለምልልስ አስመራ ተወልደው እንዳደጉ የገለጹት ዶ/ር ሰለሞን የሻዕብያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ የአጎት ልጅ መሆናቸው ምንጮች አረጋግጠዋል።
በ1995ዓ.ም በመቀሌ በተነሳ ተቃውሞ፡ አምስት ሰላማዊ ነዋሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ፦ በሺህ የሚቆጠር ህዝብ የዶ/ር ሰለሞንን መኖሪያ ቤት ከማውደሙም በተጨማሪ « የሻዕብያ ወኪል እኛን አይመራንም» በሚል የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል። ( በነገራችን ላይ ይህ ጉዳይ « በኢትኦጵ» ጋዜጣ በወቅቱ በዝርዝር መረጃው ቀርቦ ነበር።)
ሌላው የሻዕቢያ አባል የነበረው ኤርትራዊው ሳሙኤል ገ/ማሪያም ሲጠቀስ፤ የ ጠ/ሚ/ሩ አማካሪ ሆኖ የተመደበው በ1993ዓ.ም ነበር። ከሁለት አመት ቆይታ በሁዋላ የአድዋ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ ተደርጎ ተዛወረ። በ1996ዓ.ም ወደ ኢሮብ ወረዳ ያቀናው ሳሙኤል የአካባቢውን ሕዝብ ሰብስቦ … በአቶ መለስ በወቅቱ የረቀቀውን ባለ 5 ነጥብ አጀንዳ ተብዬ ለነዋሪው ለማስረዳት ይሞክራል።
በፅኑ ኢትዮጲያዊነቱና በጀግንነቱ የሚታወቀው የኢሮብና አካባቢዋ ነዋሪ የሳሙኤልን ማንነት አብጠርጥሮ በመናገርና አጀንዳውን በማብጠልጠል ተቃውሞ ያሰማል። ሳሙኤል ገ/ማሪያም ስብሰባውን በማቑዋረጥ በመጣበት ኮብራ መኪና ተሳፍሮ ጥቂት እንደተጉዋዘ.. በአካባቢው ነዋሪ በ12 ጥይት ተደብድቦ ተገደለ።
በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው የሚመሩት ወ/ሮ ሒሩት ናቸው። ኤርትራዊ የሆኑት ሒሩት የአባዲ ዘሞ ባለቤት ሲሆኑ፤ የሂሩት ወንድም እያብ (የቀድሞ መጠሪያ ስሙ ሱራፌል) ከአራት አመት በፊት ም/ሚንስትርና የጠ/ሚ/ሩ አማካሪ ተደርጎ በመለስ መሾሙን ምንጮች ጠቁመዋል። ኤርትራዊው እያብ ትምህርት የሌለው፤ ምንም አይነት ችሎታና ብቃት እንደሌለው እየታወቀ ሃላፊነት በሚጠይቅ ትልቅ ቦታ መመደቡ አስገራሚ ነው ያሉት ምንጮች አሁንም በጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም ካቢኔ መቀጠሉን አክለው ገልጸዋል።
በማስከተል በሕወሓት ማ/ኰሚቴ ያለውን ቤተሰባዊ ግሩፕ ምንጮቹ እንደሚከተለው አስቀምጠዋል፤
ቅዱሳን ነጋ፡ ፀጋዬ በርሄ፡ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር ከማ/ኰሚቴ አባላት ቅድሚያ ይጠቀሳሉ። ቅዱሳን የሽማግሌው ስብሃት ነጋ እህት ስትሆን የጸጋዬ ባለቤት ናት። ፈትለወርቅ ደግሞ የስብሃት ወንድም ልጅ ናት። ፈትለወርቅ የአባይ ፀሓዬ ባለቤት ነበረች። አንድ ልጅ አፍርተዋል፤ ከተለያዩ ቆይቶዋል። አባይ ፀሃዬ ወጣት ኮረዳ ተሞሽረው በሙስና የደለበ ኑሮ ይገፋሉ ብለዋል ምንጮች። በአደገኛ ሰላይነታቸው የሚታወቁት ብርሃነ ኪ/ማርያም (በቅፅል ስማቸው ብርሃነ ማረት) ከስብሃት ነጋ ጋር የጋብቻ ዝምድና ያላቸው ሌላው የማ/ኰሚቴ አባል ናቸው።
የአዲስአለም ባሌማ ባለቤት ፀሓይ እቁባይ ትባላለች፤ የአርከበ እቁባይ እሕት ናት። የአርከበ ባለቤት ደግሞ ንግስቲ ገ/ክርስቶስ ስትሆን፡ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ እሕት ናት።
No comments:
Post a Comment