july 6/2016
በቅርቡ በፆረና ግንባር ወያኔ በቆሰቆሰው ጦርነት በኤርትራ ወታደሮች ተማርከው በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወታደሮች የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም ከተለያዩ ብሄሮች የተውጣጡት ወደዚህ ጦርነት የገቡት በትግሬ የጦር አዛዦች አስገዳጅነት መሆኑን በመናገር የኤርትራ መንግሥት ይቅርታ የሚያደርግላቸው ከሆነ አርበኞች ግንቦት 7ን በመቀላቀል ዘረኛውን ገዳዩን የወያኔ ስርዓት ለመዋጋት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ከኤርትራ ምድር የወጣው መረጃ በታማኝ ምንጮቻችን በኩል ሊረጋገጥ ችሎዋል።
የጦር ምርኮኞቹን ጉዳይ አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዜጠኞች ለቀረበለት ጥያቄ በአቶ ጌታቸው_ረዳ በኩል የተሰጠው ምላሽ
<<ምንም የተማረከ ወታደር የለም እንዲያው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እስከ 200 ሜትር ድረስ ለትንኮሳ የመጡትን የኤርትራን ወታደሮች እያሳደደ አጥቅቷል>>የሚል እንደነበር የሚታወስ ነው።
የነዚህን የኢትዮጵያ ምርኮኛ ወታደሮች የወደፊት እጣ ፈንታ አስመልክቶ የኤርትራ መንግስት ምን ሊወስን እንደሚችል እስካሁን ድረስ ምንም የታወቀ ነገር ባይኖርም በጉዳዩ ዙሪያ የኤርትራ ባለስልጣናት ከአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ጋር ሊነጋገሩበት እንደሚችሉ መረጃውን ካደረሱንታማኝ ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።
No comments:
Post a Comment