Tuesday, July 5, 2016

የህወሃቱ ሹም ራሳቸውን በራሳቸው ካዱ

July 5,2016

“የአምስት ቀን አራስ ልጄን እንደያዝኩ ጥዬ ሸሽቻልሁ” ተፈናቃይ
save
በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ማንጎ ጨፌ ሌሎች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ መንደሮች ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የወረዳው ሥራ አስፈጻሚ ህይወታቸው እንደጠፋ በይፋ ቢነገርም የዚያኑ ያህል ከዚህ ጋር በተያያዘ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ባቀናበረው መረጃ ላይ እንዳመለከተው “መኖሪያ ቤቶቹ ይፈርሳሉ በመባሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወሰኑት አቤቱታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት የመንግስት አፍራሽ ግብረኃይሎች ቤቱን ለማፍረስ የመብራት ትራንስፎርመር መንቀል እንደጀመሩና በዚህ መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደተፈጠር ነዋሪዎች ይናገራሉ”።
ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶች በዶዘር በሚፈርሱበት ወቅት ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ የአካባቢው ወንዶች እና አባወራዎች ለእስር ተዳርገው አቅመቢስ ህጻናትና ሴቶች ብቻ በግፍ እየተገደዱ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ አንወጣም ያሉትም ቤታቸው ላያቸው እንዲፈርስ በሚደረግበት የመጨረሻ ወቅት ቤታቸውን እየጣሉ እንደወጡ ይናገራሉ፡፡
“የዶዘር ድምጽ እየገፋ ሲመጣ አንድ የ11ዓመት ልጄንና አንድ የ6 ዓመት ልጄን እዚያው ዝናብ ላይ ትቼ የአምስት ቀን ወንድ ልጄን ታቅፌ ሸሽቻለሁ” በማለት በእንባ እየታጠበች የተናገረችው እናት በአሁኑ ሰዓት በጓደኛዋ ቤት ተጠልላ እንደምትገኝ ከቪኦኤ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ ተናግራለች፡፡
የየቤተሰቡ አባወራ በአካባቢው እንዳይገን በማድረግ፤ አብዛኛውንም በማሰር በሐምሌ ክረምት መግቢያ ላይ የተደረገው የግፍ አሠራር ምንም እንኳን ቤቶቹ ህገወጥ ናቸው ቢባልም ቢያንስ ለምን በበጋው ወቅት አይደረግም በማለት ነዋሪዎች በምሬት ይጠይቃሉ፡፡
ስማቸው ካሡ ጎዳፋይ መሆኑን እና የወረዳ አንድ ተወካይ መሆናቸውን በትክክል ካረጋገጡ በኋላ የተደወለላቸው demolishedከቪኦኤ መሆኑ ሲነገራቸው ካሱ ጎዳፋይ እንዳልሆኑና ሲመጣ እንደሚነግሩት እርሳቸው ግን የካሡ ወንድም እንደሆኑ የተናገሩት አነጋገራቸው የሚያሳብቅባቸው የህወሃት ሹመኛ፤ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ እያነጋገረቻቸው ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግተውባታል፡፡
ይህንን ግፍ የተሞላበት ዘግናኝ አሠራር በተመለከተ ገጣሚ ዮሐንስ ሞላ (Yohanes Molla) ከዚህ ፎቶ ጋር በማያያዝ የሚከተለውን ጽፏል፡- “እንኳን እንዲህ የትም ውጡ ተብሎ፥ ቤት ጣሪያው ተበስቶ ሲያንጠባጥብ እንኳን ይጨንቃል። እንኳን እንዲህ የትም ተበተኑ ተብሎ፥ ካፊያ ጥሎ መጠለያ እስኪያገኙ ድረስም ይጨንቃል። እንኳን እንዲህ በየሜዳው ተወርውሮ፥ ጠና ያለ ነፋስ መጥቶ ቆርቆሮ ሲያንጋጋም ይጨንቃል። እስከመቼ ግን ሕዝብ ላይ እንዲህ ይደረጋል?!”
ድልድይ በማፍረስ “ዝነኝነቱ” የሚታወቀው ህወሃት፤ አሁን እንኳን የሥልጣን መንበር ላይ ሆኖ ማፍረሱ ተያይዞታል፡፡ በላፍቶ አካባቢ የተከሰተው ግን አፍራሽ ሁልጊዜ ሲያፈርስ ብቻ እንደማይኖርና ቀኑ ሲደርስ እርሱም እንደሚፈርስ በማስረጃ የተረጋገጠበት ነው፡፡ (የዜናው ምንጭ: ቪኦኤ)

No comments:

Post a Comment