January 12/2014
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን በፀረ ሽብርተኝነት ለማንቀሳቀስ ኢሕአዴግ አዲስ ዘመቻ ጀመረ፡፡ ኢሕአዴግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችን ባለፈው ዓርብ ሰብስቦ በፀረ ሽብርተኝነት ወቅታዊ ክስተቶችና በፀረ ሽብር አዋጁ ላይ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
ሥልጠናው በዚህ ሳምንት ቀጥሎ ለዝቅተኛና ለመካከለኛ አመራሮች፣ እንዲሁም ለተለያዩ ማኅበራትና ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ውስጥ ለሚሳተፉ አባላቶቹ ይሰጣል፡፡ ይህ ሥልጠና ለከተማው ነዋሪዎችም እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች በዋናነት ሥልጠናውን የሰጡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረ ሚካኤልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡
‹‹የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ሽብርተኝነትን ከመከላከልና ሕገ መንግሥታዊ መብትን ከማስከበር አንፃር ያለው ገጽታ›› በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ከመሠራጨቱም በላይ፣ አቶ አስመላሽና አቶ ተወልደ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የአመራር አባላት እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
ከዚህ በኋላ ሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች እስከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ድረስ ሽብርተኝነትን መከላከል እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ በዚህ መሠረት በቀጣዮቹ ሳምንታት ሕዝቡን በፀረ ሽብርተኝነት ላይ አቋም ለማስያዝ ተከታታይ ሥራዎች እንደሚካሄዱ ተነግሯል፡፡
አሠልጣኞቹ የአስተዳደሩ መዋቅር አካላት መታወቂያ የሚሰጡትን ሰው ማንነትን በውል መረዳት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ የሃይማኖት አክራሪነትና የአሸባሪነት ዋናው ምንጭ ድህነትና ተስፋ መቁረጥ ነው ያሉት አሠልጣኞቹ፣ ተስፋ የቆረጡና ያልተሳካላቸው አካላት ወደ ሽብር ድርጊት እንደሚገቡ አመልክተዋል፡፡
መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮች፣ እንዲሁም ሥራ አጥነት መቀረፍ እንዳለበት አሠልጣኞቹ ገልጸው፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡
ይህ ካልሆነ ግን የተከፉ ሰዎች ለሽብርተኞች እርሾ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥርጥር እንደሌለው ተብራርቷል፡፡ አቶ አስመላሽ በሰጡት ማብራሪያ ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ጋር ተያይዞ የተነሳው ረብሻ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ምክንያቱም አዲስ አበባ ውስጥ በ54 ቦታዎች የተነሳው ረብሻ ለፀጥታ ኃይሎች አስቸግሮ እንደነበርና ይህም የሆነው ተገቢው ሥራ ባለመሠራቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በመነሳት አመራሮቹ በተጀመሩ የቤቶች ልማት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ እንዲሁም በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠራት እንዳለበት በሥልጠናው ላይ ተገልጿል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት በፍትሕና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ማስወገድ፣ የሕግ የበላይነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መስፈን እንዳለበትና የመልካም አስተዳደር እንቅፋት በመሆን ላይ ያለውን ሙስና እያንዳንዱ ተቋም ከሥራ ባህሪው አኳያ መታገል እንዳለበት ተገልጿል፡፡
አቶ ተወልደ በበኩላቸው፣ የፖሊስና የፀጥታ አካላት የማኅበረሰብ ፖሊስን በማስተባበር የሽብር አደጋዎችን ዜሮ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባቸው ገልጸው፣ ኅብረተሰቡ ከእነዚህ አካላት ጋር እንዲታገል አመራሮች በዚህ ስሌት ሥራቸውን ማከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
አቶ አስመላሽ እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባፀደቃቸው ሦስት አዋጆች የአገር ውስጥ ተቃዋሚዎችና በውጭ የሚገኙ አንዳንድ አካላት ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ሦስቱ አዋጆች የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት አዋጅና የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ናቸው፡፡
እነዚህ አዋጆች ከፍተኛ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም፣ አዋጆቹን ለማስቀልበስ ተቃዋሚዎች ያልተገባ ዘመቻ ከመክፈታቸውም በተጨማሪ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የፀረ ሽብር አዋጅ እንዲሰረዝ ፊርማ እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በወቅቱ በተሰራጨው ጥናታዊ ጽሑፍ እንደቀረበው ኢትዮጵያ የሽብርተኝነት ሥጋት የተደቀነባትና በርካታ ጥቃቶች የተፈጸሙባት አገር ናት፡፡ በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ በተደራጁ ሽብርተኞች የጥቃት ሰለባ ሆናለች፡፡ ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ ኦነግ ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ያደረጉ ሕዝብ በሚዝናናባቸው ሆቴሎች፣ ባቡር ጣቢያዎች፣ ንግድ ቤቶች በፈጸመው የሽብር ጥቃቶች ለንፁኃን ዜጎች ሞት፣ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ማድረሱን የጥናት ጽሑፉ አትቷል፡፡ አቶ አስመላሽ ሲያብራሩም፣ ከ1987 እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ በኦነግ ላይ 106 ክሶች ቀርበዋል፡፡ ጥናታዊ መረጃው እንደሚያብራራውም ኦብነግ፣ አልኢታድ፣ አልሸባብ፣ ግንቦት 7 እና አልቃኢዳ በተለያዩ ወቅቶች የሽብር ጥቃት አድርሰዋል ይላል፡፡
አገሪቱን ከዚህ የሽብር ጥቃት ለመታደግ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን፣ አዋጁን ለማስፈጸም ኅብረተሰቡ ከመንግሥት ጐን እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ሪፖርተር

No comments:
Post a Comment