January 8/2014
በአለም አቀፍ ደረጃ የፋሽን ሾው ስርአት ሲዘጋጅ ዋነኛ አላማው በወቅቱ በዲዛይነሮች የተሰሩ ስራዎቻቸውን እና ሌሎች ተያያዥ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እና በአለም አቀፍ ገበያ ውስጥ በደረጃ ለማስገባት እንዲያስችል እና የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ለወጥ ለማድረግ ሲባል ብቻ የተጀመረ እንደሆነ ይታወሳል ሆኖም ግን ከወደ ኢትዮጵያ የሚሰማው ዜና አላማው ለሌላ እንደሆነ እና አላማውን የሳተ ሪፕርታዥ ተዘግቦ እናያለን ይሄውም በተለያዩ ጊዜያት ዓለም አቀፋዊና አገራዊ የቁንጅና ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ውድድሮቹ በሚካሄዱበት ጊዜም የራሳቸው ዓላማ ይኖራቸዋል። የቁንጅና ወድድሮች በአብዛኛው ለግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ለገቢ ማሰባሰቢያና ሰዎችን ለማዝናናት ይዘጋጃሉ ሲል አቅርበዋል ይህ ከእውነት የራቀ እሳቤ እንደሆነ የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይገልጻል ። ይህንን ዜና የጻፈው የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ በኢን ተርናሽናል አካዳሚ ዲዛይን ትምህርት ቤት (IADT Chicago ) የፋሽን ዲዛይን እና ሞዴሊን ጋይዳንስ ፕሮግራም የወሰደ በመሆኑ ጥልቅ የሆኑ መረጃዎችን በሞዴሊንግ ፕሮግራም ላይ ሊሰጥ እንደሚችል ይጠቁማል እንዲህ አይነቱን የተዛባ የሙያዊ አመለካከት ወደ ጥሩ ጎን ስለማይወስደው ጥልቀት ያላቸው ሰዎች እንደእንዚህ አይነት የዜና ሪፖርቶችን እንዲሰሩ ይመክራል ፣ ሆኖም ግን የዜናውን አጠቃላይ ሪፖርት እንዲህ ስናቀርበው ለገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ስራውን እንደሚያካሂዱበት በግልጽ የጠቆሙት ይሄው የሞዴሊንግ ሾው የማናቸውንም ዲዛይነሮች ምርቶቹን ለማስተዋወቅ እና በቀዳሚነት በሚደረገው የርካሽ ዋጋ ሽያጭ ሊደረግ ሳይሆን ኮብል ስቶን (የድንጋይ ጠራቢ ሴቶችን )ለማስተዋወቅ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ። ዝርዝሩን ይመልከቱ ......
በተለያዩ ጊዜያት ዓለም አቀፋዊና አገራዊ የቁንጅና ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ውድድሮቹ በሚካሄዱበት ጊዜም የራሳቸው ዓላማ ይኖራቸዋል። የቁንጅና ወድድሮች በአብዛኛው ለግንዛቤ ማስጨበጫ፣ ለገቢ ማሰባሰቢያና ሰዎችን ለማዝናናት ይዘጋጃሉ።
ጥር 17ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደው በዓይነቱ ለየት ያለ የቁንጅና ውድድር ታዲያ በኮብልስቶን ሥራ ላይ ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑ ወጣት ሴቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ነው።«ሚስስ ኮብልስቶን» የቁንጅና ውድድርን የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርና ኤም.ቲ.ኤል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን በጋራ የሚያዘጋጁት ነው። በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑትም ከቤት እስከ መኪና ሽልማት ያገኛሉ።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ወጣት መድሃኔ መለሰና የኤም.ቲ.ኤል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተሰማ ሰሞኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የቁንጅና ውድድሩ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑና ቁጠባን ባህላቸው አድርገው ከራሳቸው አልፎ ሌሎችን መጥቀም የቻሉ ሴት ወጣቶችን ለማበረታታት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
የቁንጅና ውድድሩ ለየት ባለ አቀራረብ ወጣቶች የሥራ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ለማድረግ የሚያነሳሳ መሆኑን የሚናገረው ወጣት መድሃኔ ሥራን ሳይንቁ በመሥራት ከራሳቸው አልፈው ሌሎችን እየጠቀሙ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ለሌሎች ምሳሌ እንዲሆኑ ለማስተዋወቅና በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ለማሳየት የሚረዳ መሆኑን ነው የሚያብራራው።
በመወዳደሪያ መስፈርቶቹም ወደ ኮብልስቶን ሥራ ሊሠማሩ የቻሉበት ምክንያት፣የቁጠባ ባህላቸውና ሥራውን መሥራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ያመጡት ለውጥ የሚሉት ይገኙበታል።
የኮብልስቶን ሥራ ብዙ የመነሻ ካፒታል የማይጠይቅና ለውጡን በአፋጣኝ ማየት የሚቻልበት በመሆኑ ወጣቶች ለ21 ቀናት ሥልጠናውን በመውሰድ ብቻ በ22ኛው ቀን ወደ ሥራ እንደሚሠማሩ የሚናገረው የማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ መድሃኔ በሚያዘጋጁት የኮብልስቶን መጠን ክፍያቸው እንደሚያድግ፤ ክፍያቸው በጨመረ ቁጥርም ደግሞ የመቆጠብ ልምዳቸውን በመጨመሩ የወጣቶቹ ሕይወት በመለወጥ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
«የእዚህ ትውልድ ቆንጆ መባል ያለበት ሥራን ሳይንቅ በመሥራት ድህነትን ማሸነፍ የቻለ ነው» የሚሉት የኤም.ቲ.ኤል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ «በአሁን ወቅት ኮብልስቶን ለወጣቱ ሥራን ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሪን ማስቀረት ችሏል። የኮብልስቶን ሥራን ሴቶች አይሠሩትም በሚል የተሳሳተ አመለካከት የነበረ ቢሆንም ፀሐዩንና ሐሩሩን ተቋቁመው ድንጋይ በመፍለጥ ከፍተኛ የሆነ ክፍያን ማግኘት የቻሉ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ነው። መሥራት ማለት መለወጥ በመሆኑ ቆንጆ መባል ያለበት የተለወጠ ሰው» ሲሉም ግንኙነቱን ገልጸውታል።
ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ የሚገኘው የኮብልስቶን ሥራ ጥቂት ሥራ ያልነበራቸው ሰዎች የሚሰማሩበት ብቻ ሳይሆን ቆነጃጅት ለመሸለም የሚወዳደሩበት እንዲሆን ከሚስስ ኮብልስቶን የቁንጅና ውድድር ጎን ለጎን ፕሮፌሽናል የሆኑ ቆነጃጅት የሚሳተፉበት ውድድር እንደሚካሄ ድም ነው አቶ መላኩ የጠቆሙት።
ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርና ከኤም.ቲ.ኤል ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ጋር በመተባበር የአዲስ አበባ የኮብልስቶን ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት፣የጥቃቅንና አነስተኛ ጽሕፈት ቤት፣ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ፣ የቁጠባ ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላት ለውድድሩ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው በመግለጫው ላይ የተነገረው።
No comments:
Post a Comment