በጎንደር የአንድነት አመራሮች ሲከበቡ ፖሊስ ካሜራ ነጥቋል
በ30/10/2005 በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ለማከናወን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ የከተማው አስተዳደር በሰነቀራቸው ምክንያቶች የተነሳ ፓርቲው ለህግ ያለውን ተገዢነት ለማሳየት በማሰብ ሰልፉን ለአንድ ሳምንት ማራዘሙ አይዘነጋም፡፡
ፓርቲው ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ የወሰደውን ውሳኔ እ...ንደ ፍርሃት የተመለከቱት አስተዳደሮች የአንድነትን አባላት በመለቃቀም ወህኒ ቤት አጉረዋል፡፡ዛሬ ማለዳ ደግሞ ብዛት ያላቸው የቀበሌ ካድሬዎች ፖሊሶችን በማስከተል የአንድነት የጎንደር ጽ/ቤትን በመክበብ ለቅስቀሳ ስራ ለመውጣት የተዘጋጁ አባላትን አግተዋል፡፡
የቅስቀሳ ስራ የሚሰሩ አባላት በያዙት ካሜራ የፖሊሶቹንና የካድሬዎቹን ህገ ወጥ ድርጊት በካሜራቸው ቀርጸው ለማስቀረት ሲሞክሩ ፖሊስ ካሜራውን ነጥቆ ወስዷል፡፡ከሁሉም አስገራሚው ግን ካድሬዎቹ ለጽ/ቤት ቤታቸውን ያከራዩትን ወይዘሮ ለማስፈራራት መሞከራቸው ነው፡፡ወይዘሮዋም ለአመራሩ ቤቴን ለቅቃችሁ ውጡልኝ በማለት ተማጽንኦ አቅርበዋል፡፡
ፖሊሶችና ካድሬዎች እጅና ጓንት ሆነው የአንድነትን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት የሚፍጨረጨሩ ቢሆንም የጎንደርና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ከሰልፉ የሚያስቀራቸው ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል እንደሌለ እየተናገሩ ነው፡፡የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክርቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ‹‹እኛ ሰላማዊ ታጋዮች ነን የያዝነው ጥያቄ እንጂ መሳሪያ አይደለም››በማለት የሰላማዊ ሰልፉ ተልእኮ ‹‹ሰላማዊነት››ብቻ መሆኑን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
#Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
No comments:
Post a Comment