የአማራን ተወላጆች የገቡበት ቦታ ሁሉ እየገባ ወደ ክልላችሁ ሂዱ እያለና ንብረታቸዉን እየቀማ የሚያፈናቅለዉ የወያኔ አገዛዝ ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አፋር ክልል ዉስጥ በብዛት ሰፍረዉ በሚገኙበት ቦታ እራሳችንን በራሳችን የማስተዳደር መብት የስጠን የሚል ጥያቄ ማቅረባቸዉን ከሰሞኑ ከወደ አፋር ክልል የነፈሰዉ ዜና አስረዳ። በአፋር ክልል የዞን ሁለት ዋና ከተማ በሆነችዉ አብአላ ዉስጥ የሚኖሬት ቁጥራቸዉ 15 ሺ የሚጠጋ የትግራይ ተወላጆች ብዛት ስላለን እራሳችንን የማስተዳደር መብት ይሰጠን ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ የክልሉ ሰብአዊ መብቶች ሃለፊ የሆኑት አቶ ገአስ አህመድ አዎንታዊ መልስ የማያስፈልገዉና አግባብ የሌለዉ ተራ ጥያቄ ነዉ ሲሉ የትግራይ ተወላጆች ያቀረቡትን ጥያቄ አጣጥዉታል።
አቶ ጋአስ በዱብቲ ከተማ በርካታ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ተወላጆች ቢኖርም አንድም ቀን የወረዳ ጥያቄ አለማንሳታቸውን ገልጸው፣ ከመቀሌ በ45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አብአላም ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ያቀረቡት ጥያቄ አሳዛኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፋር ክልል በህወሀት ሰዎች የሚመራ መሆኑን የገለጹት አቶ ገአስ፣ ተወላጆቹ ወረዳ ይሰጠን ከሚሉ ክልሉ የራሳቸው መሆኑን ቢያውቁት ይሻል ነበር ብለዋል። እንደ አቶ ገአስ አባባል አብላ ከተማ ዉስጥ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ከተማዋ በራሳቸዉ ቋንቋ ሸከት ተብላ እንድትጠራና እንዲሁም የአፋር ክልላዊ መንግስት በከተማዋ መሬት ለኢንቨስትመንት መስጠት አይችልም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸዉን ጠቅሰዉ በአሁኑ ጊዜ በአፋር ክልል የህወሀት ባለስልጣናት ግምገማ እያስደረጉና የራሳቸውን ሰዎች እየሾሙ ክልሉን ለውድመትና ለጥፋት እየዳጉት መሆናቸዉን ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment