July 28,2016
በወልቃይት የአማራ ማንነት ላይ ያነጣጠረውን የህወሓት ጥቃት ለመቃዎም እሁድ ሃምሌ 24 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል ። በጎንደር እና አካባቢዋ ያለ ማንኛውም የአማራ ተወላጅ እና የአማራ ህዝብ ወዳጅ ይህን ሰላማዊ ሰለፍ እንዲቀላቀል ጥሪ ተላልፏል ። ህፃን፣አዛውንት ፣ ወጣት ፣ ሴት ፣ወንድ… ሳይል ሁሉም አማራ በአንድ ላይ ስለ አማራነቱ ድምፁን ለማሰማት ወደ አደባባይ እንዲወጣ የሰልፉ አዘጋጆች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የሰልፉ አስተባባሪዎች አያይዘውም ይህን ሰልፍ የሚመራው እና የሚያስተባብረው ሰፊው የአማራ ህዝብ እንደሆነ ገልፀዋል።
ሰልፉ ፍፁም ጨዋነትን እና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት የሰልፉ አስተባባሪዎች ለአማራ ህዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ህግ አስከባሪዎች ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ጥበቃ እንዲያደርጉም ጥሪ ተላልፎላቸዋል ።
ከባህርዳር ጀምሮ ፣ እስቴ፣ ደብረታቦር፣ጋይንት፣ንፋስ መውጫ ሃሙሲት፣ወረታ፣አዲስ ዘመን፣ እንፍራንዝ፣አርባያ በለሳ ፣ ማክሰኝት ፣ ጠዳ ፣ቆላድባ፣ ጯሂት፣ጎርጎራ፣ደልጊ፣ሻውራ፣ እሰይደብር፣ጎይ፣ አፀደ ማ ሪያም ፣ ጋዝጌ፣ ቁንዝላ፣ሽንፋ፣ደለጎ፣መተማ፣ሽኸዲ፣ነጋዴ ባህር፣ጨው ድባ፣ጫን ድባ፣ ሰራባ፣ጭልጋ፣ ቡሆና፣አይምባ ፣ሁመራ ፣ አብደራፊ፣ሳንጃ ፣ዳንሻ ፣ሰሮቃ፣ሙሴ ባንብ፣ትክልድንጋይ ፣ ሸንበቂት፣አምባ ጊዬርጊስ፣ገደብጌ፣ዳባት፣ደባርቅ ፣ድብ ባህር ፣ ዘሪማ ፣አዲ አርቃይ ፣ ስሜን ጃናሞራ …እና በእነዚህ አካባቢ ያሉ ሌሎች የገጠር ቀበሌ ኗሪዎች ወደ ጎንደር በመዝለቅ የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፎላቸዋል ። ከጎንደር ራቅ ብሎ ያለ ማንኛውም አማራም ቢሆን አቅሙ ከፈቀደለት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀል አማራዊ ጥሪ ተላልፎለታል።
#የአማራ_ተጋድሎ
#AmharaResistance
#ቤተ_አማራ

No comments:
Post a Comment