Sunday, June 19, 2016

‹‹በኔ አመለካከት ጀነራል ሣሞራ ለመንግስትና ለህዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፡፡›› ~ሜጀር ጀነራል አበበ ተ/ሃይማኖት

June 19,2016
Abebe ty

ሜጀር ጀነራል ኣበበ ተክለ ሃይማኖት የታጋይዮች ተወዳጅነት ገና ሳይደበዝዝ ነበር በጥሮታ ሰበብ ከመከላከያው የተገለሉት፡፡በሌላ አባባል ጀነራሉ ወታደር ሳይሆኑ ነበር የታጋይነት መዓርጋቸውን እንደጨበጡ ከድርጅቱ የተሰናበቱት፡፡
ይኸው የታጋይነት ትጥቃቸው አሁንም ድረስ ከርሳቸው ጋር ነው፡፡ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ግዜ ሰጥቶ ማንበብ የግድ ይላል፤ ከጊዜ እጥረት የተነሳ ሙሉውን ማንበብ ለማይችሉት ግን አንኳር አንኳሮቹን እንደሚከተለው አቅርቤያቸዋለሁ፡፡
‹‹
☞በዓለም አቀፍ ህግ የአሰብ ወደብን ማስመለስ እንችላለን
☞ለሕገ መንግስቱ በተሟላ መንገድ መተግበር የአቅሜን ያህል እታገላለሁ፡፡
☞እኔ ከመጀመሪያውኑ ስታገልላቸው ለነበሩ አላማዎች፣አሁንም በፅናት ቆሜያለሁ ነው የምለው፡፡
☞ገዥው ፓርቲ ነው ከትግሉ አላማዎች ወደ ኋላ እየተንሸራተተ ያለው፡፡
☞የፓርቲ አባሎች ሲመለምል ከጥራት ይልቅ ብዛት ላይ በማተኮር በሚልዮኖች መለመለ፡፡ ሲቪል ሰርቫንቱ በብቃት ሳይሆን በአባሎቹ ተሞላ፡፡
☞ከዩኒቨርሲቲ “A” ከማምጣት ከኢህአዴግ “C” ማግኘት ይሻላል ተባለለት፡፡
☞የመልካም አስተዳደር ችግር ፖለቲካዊ ነው፤ የዲሞክራሲ ማጣት ውጤት ነው፡፡
☞ችግሩ የሚጀምረው ከላይኛው አመራር ነው፡፡ እላይ ከተስተካከሉ ከስር ይስተካከላል፡፡
☞ኢህአዴግ ውስጥ መተጋገል የለም፡፡
☞ደርግነት የሚመጣው እንግዲህ ሲቪሉ መግዛት ሲያቅተውና “ወታደሩ እኔ እሻላለሁ” ማለት ሲጀምር ነው፡፡
☞ከዚያ በኋላ እየጨለመ የመጣው ዲሞክራሲ፣ ወደለየለት አምባገነንነት ያመራል ማለት ነው፡፡
☞ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ እየጠበበ ደርግነት እያቆጠቆጠ፣ በመንግስትም ከመንግስት ውጪም ማፍያዎች እየታዩ ነው ስል፡ “ብዙ ሰዎች አንተ አትፈራም እንዴ? ሊገድሉህ ሊያስሩህ ይችላሉ” ይሉኛል፡፡
☞በተዘዋዋሪ መንገድ ግን መታገል አለብህ እያሉኝ ነው፡፡
☞መጀመሪያ በ “ካራክተር አሣስኔሽን”፣ ከዚያም የተለያዩ ጥቃቶች ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡ እንግልት… መሞት… መታሰር ያስፈራል፡፡ ያስጠላልም፡፡
☞እኔ ከሁሉም የምፈራው ፈርቶ በቁም መሞትን ነው፡፡ ፈርቶ የህሊና እስረኛ መሆንን ነው፡፡ በተለይ ወጣቶች ከዚህ የህሊና እስርና በቁም መሞት በላይ ምንም እንደሌለ ተገንዝበው መታገል አለባቸው፡፡
☞“የሀገራችን ችግር በህወሓትና በኢህአዴግ ብቻ ነው የሚፈታው” የሚል የምርጫ ቅስቀሳ ለምን እንደጀመሩ አይገባኝም።
☞የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ኢህአዴግ ከሌለ አይኖርም ማለት እብሪት ነው፡፡ ኢህአዴግንም ህወሓትንም የፈጠረው ህዝብ ነው እንጂ እነሱ ህዝብን አልፈጠሩም፡፡
››
ምንጭ – አዲስ አድማስ

No comments:

Post a Comment