May 15,2016
የመከላከያ ሰራዊት የሚገኝበትን ስፍራና አድራሻ ለተቃዋሚዎች መረጃ አሳልፋችሁ ሰጥታችኋል በሚል ወታደሮቹ በጥርጣሬ በወንጀል መታሰራቸው ታወቀ።
መረጃው እንዳስረዳው የተሰጣችሁን አገራዊ አደራ ወደ ጎን ትታችሁ የመከለካያ ሰራዊት ስፍራና አድራሻ ለተቃዋሚ ድርጅቶች ታስተላልፋላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ ወታደሮች ያለ ምንም ማስረጃ በግብረ ሽበራ በሚል በወንጀል ክስ እንደተመሰረተባቸው መረጃው አስረድቷል።
የፊዴራሉ አቃቢ ህግ የላይኛው ፍርድ ቤት የ1ኛው ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ በርከት ያሉ ወታደሮች ሲሆኑ፣ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፣ አስራ አለቃ አጀናው ታደሰ፤ ምክትል አስራ አለቃ ቻሌ ነጋና ሌሎችም የቀረበላቸው ክስ እንዳስረዳው በኢትዮ_ ኤርትራ ዳር ድምበር ትጥቅ ያነገቡ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት በ6ተኛውና በ25ተኛ ክፍለ ክፈለጦር የሚገኙትን የሬጅመንቶች ብዛትና የት እንደሚገኙ መረጃ በዝርዘር አስልፋችሁ ትሰጣላችሁ በሚል በከባድ ወንጀል ቢከሰሱም ፣ለቀረበላችው ጥያቄ ስላልተቀበሉት በህግ ጠበቃ ለግንቦት 15 /2008 ዓ/ም ቀጠሮ እንደተሳጣቸው አስገነዘበ።
በመጨረሻ በአሁኑ ግዜ በመከላከያ ሰራዊት ያለመተማምንና መጠራጠርን እንደ ተፈጠረና በዚህ ምክንያትም ብዙ ወታደሮች አሃድዋቸውን ትተው እግራቸው ወዳመራቸው እየጠፉ መሆናቸውን ታወቀ።

No comments:
Post a Comment