Sunday, April 24, 2016

የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንትና ሪክ ማቻር የተሳፈሩባት መኪና በሰልፈኞች ጥቃት ደረሰባት

April 23,2016
ስለፈ
 በጋምቤላ ክልል ጃዊ በተባለ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በደቡብ ሱዳን ሱደተኞች ተጨፍጭፈው ከ17 የሚልቁ ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
በዛሬው ዕለት ድርጊቱን ለማውገዝ የጋምቤላ ከተማና አካባቢዋ ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቷል፡፡ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያዊያኑን በግፍ በገደሉ ስደተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለመጠየቅ በሞከሩበት ሰዓት ፌደራል ፖሊሶች ሰልፈኞቹን ህገ ወጥ ሰልፍ በመሆኑ እንዲያቆሙ በመንገር ጥይት መተኮስ በመጀመራቸው ሰላማዊው ሰልፍ መልኩ ተቀይሯል፡፡ሰልፈኞቹ ወደ ስደተኞቹ ካምፕ በማምራት ደቡብ ሱዳናዊያን ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ ቢሆንም በወታደሮች ታግተው የተወሰኑት መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሰልፈኞቹ በጋምቤላ የደቡብ ሱዳናዊያን ናቸው ያሏቸውን ሆቴሎች ፣መኖሪያ ቤቶችና መኪኖችን በድንጋይ መደብደባቸው የተሰማ ሲሆን የደቡብ ሱዳኑ ሪክ ማቻርና የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት  ጋትሏክ ቱት የተሳፈሩባት መኪና በሰልፈኞቹ በድንጋይ መደብደቧን ነገር ግን በሰዎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ ተሰምቷል፡፡

No comments:

Post a Comment