Thursday, December 3, 2015

የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መገኘት ለኢትዮጵያ ዲሞከራሲ ሀይሎች የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው

December 3,2015

ከዚህ ወዲያ አፍ እንዳመጣ “ሽብርተኛ” ማለት የህወሃት መሩ መንግስት እብደት ሆነ!

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋን የአውሮፓ ፓርላማ ንግግር በተመለከተ የኢሳት ዘገባን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ – የቪኦኤ ዘገባ ለማዳመጥ ደግሞ እዚህ ይጫኑ
ቢላል አበጋዝ – ዋሽግተን ዲሲ
ዛሬ ኢትዮጵያ ለህወሃት መሩ መንግስት ተንፈራጦ መግዛት የምትመች አለመሆንዋን ማንም ዜና መከታተል ለሚፈልግ ግልጽ ነው።የህወሃት ባለስልጣናትም ከወትሮው በተለየ መልኩ እርስ በርስ እየተናቆሩ ነው።ተስፋ የቆረጡት ደግሞ ንብረት እያሸሹ ይገኛሉ።በቀይ ባህር አካባቢ አፍሪካ ቀንድን ሊያምስ የሚችል ደመናም ጥሏል ማለት ይቻላል።ሀብታም አረቦችም ልክ እንደ ህወሃት በስጋት ተወጥረዋል።ኢትዮጵያን ማተራመስ ቅር ሳይላቸው ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽሙ ለመሆናቸው የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ይመሰክራል።Professor Berhanu Nega in Eritrea
ከላይ የጠቀስኩት አደጋ ማንጃበቡ ሳያንስ ዛሬ አስራ አምስት ሚሊዮን ወገናችን ለራብ ተዳርጓል።ይህን መከራ በመካድ የጀመረው ህወሃት ህይወት ለማትረፍ የሚጥር አይደለም።በኢትዮጵያ በያለበት እስራትና ግድያው በርትቷል።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት ስለ ኢትዮጵያ እንዲናገር መጋበዙ ያቀረብኩትን የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመንግስታቱ ተወካዮች መግለጽ ብቻ ሳይሆን አጣዳፊ ሁኔታ መፈጠሩንም የማስስጨበጥ ሁኗል። ኢትዮጵያን የፋሺት ኢጣሊያ መንጋጋ ሲያኝካት የተሰደዱ አርበኞች በዓለም መድረክ ጮሆውላት ነበር። ዛሬም በህወሃት መንጋጋ ስትታኘክ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢትዮጵያውያ ወገኖቹ ጋር ሆኖ ድምጹን ከፍ አድርጎ አሰምቶላታል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን የፈጸመው በግንባር ሆነው ህወሃት መሩን መንግስት ብርክ እያስያዙ ያሉትን የኢትዮጵያን ጀግኖች ከበረሃ ተለይቶ ነው።
የኢትዮጵያ ሁኔታ ጊዜ የማይሰጥ ነው።ህወሃት መሩ መንግስት በመለስ ዜናዊና ጀሌዎቹ አማካይነት ያፈላው የጥላቻ ጥንስስ ድንገት ሳይፈነዳ አደጋውን ሊገታ የሚችል ዝግጅት ማድረግን ይጠይቃል።ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሁሉም የሚወከልበት ጊዜያዊ መንግስት ካልቆመ ወያኔ ፈጽሞ የመግዛት ሀይሉን ሊያጣ የሚችልበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም።ህዝቡ በቃኝ ለማለቱ ምልክቶቹ መበራከታቸው ይህን አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ሃይማኖትን ተቋማት ጣልቃ በመግባት አዳክሟል።የእስልምና ሃይማኖት ተቋማትን ደፍሮ መሪዎችን ለእስር ዳርጓል።ነጻነትና ዜግነት በየፈጁ ተደፍሯል።
የዓለም መንግስታት በተለይ ሃያላን የኢትዮጵያን ጉዳይ ወደጎን በመተው ህወሃት መሩን መንግስት መወንጀል ሳይሆን በስመ ሽብርተኝነትን መቋቋም አብረውት እየሰሩ ነው።በታሪካችንም የፋሺት ኢጣሊያውን ሙሶሊኒንም አይዞህ ያሉት ነበሩ።ሁሉም ለየራሱ ጥቅም በዓለም ዲፕሎማሲ ሰልፉን ያስተካክላል።በየጊዜውም ይለውጣል።ኢትዮጵያን የምንል አንድ መሆን የግድ የሚለን ጊዜ አሁን ነው።ህወሃት መሩ መንግስትማ ለሙግት፡ለመልስ እንኳን ያቆመው ቅጥረኛ የውጭ አገር ተላላኪን ነው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዋለበት መድረክ።የህወሃት ድንቁርና አንድ መገለጫ ምልክት ነው።የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ህብረት መግለጫ መስጠት ህወሃት መሩን መንግስት ለሚቃወሙና ለተራበው ከተሜ ገጠሬ ወገናችን ትልቅ ግምት የሚሰጠው ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው።ኢትዮጵያ በዚህ የመከራ ዘመን ለታደጓትን አላህ ለነሱም ይመስክርላቸው።
ድል ለዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ሁሉ!
ኢትዮጵያ በአንድነትዋ በነጻነት ለዘለዓለም ትኑር!
አላህ ኢትዮጵያ ይጠብቃት!

No comments:

Post a Comment