June 5,2015
ዘጋቢ ገዛኸኝ አበበ
ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ መርካቶ በተለምዶ ሸራ ተራ በሚባለው ስፍራ ከባድ የሆነ እሳት ተቀስቅሷል። እሳቱ በሸራ ተራና አብዶ በረንዳ ተብሎ በሚጠረው አካባቢ በአደገኛ ሁኔታ እየተያያዘ ሲሆን የእሳት ቃጠሎው መነሻ ለጊዜው ባይታወቅም በስፍርው የተቀሰቀሰው እሳት ግን በጣም አስፈሪና ከበድ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል ።በአካባቢው የተቀሰቀሰውን እሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ድረስ ጥረቱ እንደቀጠለ ሲሆን የአሳት ቃጠሎውን ግን እስከአሁን ድረስ መቆጣጠር እንዳልተቻለ ታውቋል።
ከሰፍራው ያገኘነው ዜና እንደሚያስረዳን ከሆነ እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ መኪኖች በስፍራው የነበሩ ሲሆን ነገር ግን የእሳት አደጋ መኪኖቹ ውሃ ጨርሰው ሲመላለሱ ታይተው ነበር ።
የአካባቢው ነዋሪና በአካባቢው በንግድ ስራ የተሰማሩት ሰዎች ግን እሳቱን ለማጥፋት በተቻላቸው አቅም ሁሉ በመረባረብ ጥረት ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ መሳሪያ የታጠቁ ፊደራል ፖሊሶች ግን የእሳት አደጋው በተነሳባቸው ሱቆች ምንም ዓይነት ዝርፊያ እንዳይፈፀም ጥበቃ በማድረግ በሚል ሰብብ ከተለያዩ የስፍራ በፍጥነት በመምጣት አካባቢውን ወረውታል።
ህዝቡም በሙሉ አቅሙ እሳቱን ተረባርቡ እንዳያጠፋ በስፍራው የነበሩት የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ችግር የፈጠሩባቸው ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ በነበሩ ወጣቱች ላይም አካባቢውን የወረሩት የወያኔ ፊደራል ፖሊሶች የተለያዩ ወከባ ሲያደርሱባቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በአካባቢው የሚገኙት የእሳት አደጋ ሰራተኞችም አሁንም እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆኑ። የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን በከተማዋ ካሉት ሁሉም ቅርንጫፎች የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪዎቹን በማሰማራት ቃጠሎውን ለማስቆም ጥረት እያደረገ ሲሆን ህብረተሰቡና የባለ ሱቆች ባለቤትም በእሳት ከተያያዙ ሱቆች ውስጥ ሸቀጦችን ለማዳን ጥረት እያደረጉ ሲሆን ሌላው እሳቱን ላለመቆጣጠር አስቸጋሪ ያደረገው ነገር
በእሳት በተያያዙ ሱቆች ውስጥ የፕላስቲክ ምርቶች የሚገኙ በመሆናቸው እና አከባቢው ተሽከርካሪን እንደልብ የማያንቀሳቅስ በመሆኑ እሳቱን የማጥፋት ዘመቻውን አስቸጋሪ ማድረጉ ተመልክቷል። ሌላው የእሳቱን ቃጠሎ እየተባባሰ መምጣት አሳሣቢ ያደረገው ጉዳይ በዛው አካባቢ አንድ ትልቅ የዘይት ማምረቻ መኖሩ ሲሆን እሳቱ ወደዛ ከቀጠላ በአካባቢው ትልቅ ጥፋትና ውድመት ማስከተሉ እንደማይቀር ተሰግቷል።

No comments:
Post a Comment