Thursday, April 30, 2015

የሕወሓት ጄኔራሎች እና የደህንነት ሹሞች ዝግ ስብሰባ ተቀምጠዋል::ህዝብን ከፈሩ ስልጣን መልቀቅ::

April 30,2015
ምንሊክ ሳልሳዊ
በወያኔ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ሊድን የማይችል ድንጋጤ እና መበስበስ መከሰቱን እና የህዝብ ብሶት ገንፍሎ መውጣቱ በምርጫው ጋር ተያይዞ የሚመጣው ሕዝባዊ እምቢተኝነት በህዝቡ ቁጣ ከቁጥጥር ውጪ ይወጣል የሚል ፍራቻ እንዲሁም ራስ ምታት የሆነው የሰራዊቱ እና የደህንነቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና አለመግባባት ላይ ለመነጋገር የወያኔ ጄኔራሎች እና የደህንነት ሹሞች ዝግ ስብሰባ መቀምጣቸው ታውቋል::
የሕወሓት ጄኔራሎች እና የደህንነት ሹሞች የተቀመጡት ስብሰባ የቀድሞ ታጋዮችን ብቻ የሰበሰበ ሲሆን ለስብሰባ ከተጠሩት ባለስልጣናት ውስጥ ከሶስቱ በስተቀር በሙሉ የሕወሓት ሰዎች መሆናቸው ሲታወቅ ስብሰባውን በሚያካሂዱበት ወቅት ጠባቂዎቻቸውን ይሁኑ ስብሰባ የሚያስተናግዱ ሰራተኞች በአከባቢው እንዳይደርሱ የተደረገ ሲሆን አከባቢዉን ታማኝ የሕወሓት ደህንነቶች በአይነቁራኛ እይጠበቁት ይገኛል::በአዲስ አበባ በሚገኘው እና ካሮጌው አይሮፕላን ማረፊያ በስተጀርባ ወያኔ አሻሽሎ በገነባው እና በከፍታ አጥር በተከበበው የደህንነት ቢሮ ውስጥ የተሰየመው ይህ ስብሰባ በሃገሪቱ ውስጥ የተከሰተውን ሕዝባዊ ብሶት የወለደውን እምቢተኝነት ለመቆጣጠር እቅድ ለመንደፍ መሆኑ ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::
በስብሰባው ላይ ወያኔ ባወጣው የራሱ ሕግ የውሳኔ ሰጪ የበላይ አካላት ጠቅላይ ሚኒስትር የሚባሉት ሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዳልተጠሩ እንዲሁም በረከት ስምኦን እና ተባባሪዎቻቸው እንዳልመጡ ታውቋል::ይህ በዝግ የተቀመጠው የማፊያ ቡድን ስብሰባ የወያኔን መደናገጥ እና መግቢያ ቀዳዳ ማጣቱን በይፋ ያሳየ እና በባለስልጣናት ፊት ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ መሆኑን ታውቋል::ወያኔ ለህዝብ ስልጣኑን አላስረክብም በማለት በከፍተኛ ደረጃ አምባገነንነቱን አስፋፍቶ የቀጠለ ሲሆን በልማት ስም ሕዝቦችን በመግደል በማሰር እና በማሳደድ ምርጫን ተገን አድርጎ ተጨማሪ አመታቶችን በሕዝብ ጫንቃ ላይ ለመቀመጥ ማቀዱን እየደሰኮረ ይገኛል::
የህዝብ ብሶት መገንፈሉ በፍራቻ ያርበደበደው ወያኔ በሰራዊቱ እና ደህንነቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና አለመግባባት ሌላኛው ራስ ምታቱ ሆኗል::በሽብርተኝነት ሽፋን ምእራባውያንን ማጭበርበሩን ለመቀጠል ቢፈልግም የተነቃበት ወያኔ አሁንም በሃሰት ዲስኩሮች ህዝብ ግብር የሚከፍልባቸውን ሚዲያዎች በመጠቀም ፕሮፓጋንዳ እየረጨ ይገኛል::የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ስለሚፈልግ ህዝባዊ ብሶቱ አሁንም አደባባይ በመውጣት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔ በመደምሰስ በመቃብሩ ላይ ሕዝባዊ መንግስት መመስረት የሁላችንም የጋራ ግዴታ ነው:; የተነቃነቀ ጥርስ ይወልቃል:

No comments:

Post a Comment