Sunday, April 19, 2015

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም” አለ

April 19 ,2015


ethiopian killed by isil 1











 ሁሌም በዜጎቹ ጉዳይ ከበዳይ ወገን ጋር አብሮ በመሰለፍ ዜጎቹን የሚያዋርደው የሕወሓት የሚያስተዳድረው የኢሕ አዴግ መንግስት በሊቢያ አይሲኤስ የገደላቸውን 28 ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋገጫ አላገኘሁም አለ::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት ባወጣው መግለጫው “አይሲኤስ የተባለው አለም ዓቀፍ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ፈፅሜያዋለሁ በሚል በቪዲዮ ያሰራጨው ዘግናኝ የግድያ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያወግዝ ሲገልጽ” ስደተኛ እንጂ ኢትዮጵያውያን ማለት አልፈቀደም::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዜጎቹን በመካድ በአቶ ሬድዋን ሁሴን በኩል የሰጠው መግለጫ ላይ እንዲህ ይላል:-
“በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድኑ ለህልፈት የዳረጋቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ባይሆኑም መንግስት በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ይህን መሰል አፀያፊና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት አጥብቆ ይኮንናል ብለዋል፡፡”
በግልጽ ኢትዮጵያውያንን የመሰሉ ሰዎች ታርደውና ተገድለው ባህር ላይ ተጥለው መንግስት ገና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላረጋገጥኩም ማለቱ ዜጎቹን በመካድ የታወቀው የሕወሓት መንግስት ዳግም እርቃኑን ቀርቷል:: በቅርቡ እሳዑዲ አረቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ በዜጎቹ ላይ ክህደት የፈጸመው ይኸው አምባገነን መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቹን መካዱ ብዙዎችን አሳዝኗል::
  ምንጭ /ዘ-ሐበሻ

No comments:

Post a Comment