january 14,2015
በምእራብ አፍሪካ የተነሳው የኢቦላ ቫይረስ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተላኩት የጤና ባለሙያዎች የኢቦላ በሽታ ተጠቂ እየሆኑ መመለስ መጀመራቸው የጤና ጥበቃ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ገለጹ:;
በዚሁ መሰረት በበሽታው ተይዘዋል ተብለው ከገቡት ውስጥ አንዱ መሞቱ ሲረጋገጥ ቤተሰቡ ከአከባቢው እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ናሙናዎች ተወስደው ወደ አሜሪካን ላቦራቶሪ በመላክ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::በሃገር ቤት ያሉ ሃኪሞች የጭንቅላት ወባ ነው ቢሉም ሕዝቡ ግን የጭንቅላት ወባ ከሆነ ሬሳ ምደባበቅ እና ቤተሰቡን ማገት ለምን አስፈለገ ሲል እየጠየቀ ይገኛል::
No comments:
Post a Comment