December 15,2014
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስን ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።
አቶ ሽመልስ በቅርቡ የታዩት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው በድርጅቱ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው፡፡ የፕሬስ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰብስቤ ከበደ ከአቅም ማነስና የመልካም አስተዳደር ችግር ጋር ተያይዞ በድርጅቱ ጋዜጠኞች እየቀረበባቸው ያለውን ግልጽ ትችትና ቅሬታ በተደጋጋሚ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ከማስተባበላቸውም በተጨማሪ ጥያቄውን የሚያነሱ ጋዜጠኞችን እስከማስፈራራት የደረሰ ንግግር ሲያደርጉ የተሰሙት አቶ ሽመልስ፣ መደበኛ ስራቸውን መተዋቸው በኮምኒኬሽን መ/ቤቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖአል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል በአቶ በረከት ስምኦን ደጋፊነት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ስራአኪያጅ የነበሩ ሲሆን፣ የ97 ምርጫን ተከትሎ የቅንጅት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተከሰሱ ወቅት አቃቤ ሕግን ወክለው ሐሰተኛ መረጃዎች እንዲቀርቡና ሐሰተኛ ምስክሮችን በገንዘብ በመግዛትና በመደለል ለኢህአዴግ ውለታ ለመስራት የጣሩ ሰው መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ አቶ በረከት ከጤና ጋር በተያያዘ ስራቸውን እየተዉ በመምጣታቸው አቶ ሽመልስ ብቸኛው ደጋፊያቸውን አጥተዋል። አቶ ሽመልስ አቶ በረከትን የመተካት ህልም ቢኖራቸውም ሳይሳካላቸው አቶ ሬድዋን ቦታውን እንዲወስዱ ተደርጓል። በሁለቱ ባለስልጣኖች መካከል ባለው ልዩነት የተነሳ፣ አቶ ሽመልስ ከስራቸው የሚባረሩበት ቀን እሩቅ ላይሆን እንደሚችል ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን በመልቀቅ ከአገር ለመውጣት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስ የስልጣን ቆይታ በከፍተኛ ህመም ከሚሰቃዩት ከአቶ በረከት ስምኦን ህልውና ጋር የተያያዘ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ።
ምንጭ ኢሳት ዜና

No comments:
Post a Comment