Tuesday, December 16, 2014

‹‹እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው›› አቶ ግርማ በቀለ

December 16,2014
Photo: የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

‹‹እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው›› አቶ ግርማ  በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡ 

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ 

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡ 

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

አንድ የሌላ ፓርቲ ደጋፊ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ ምርጫው ውስጥ ስለመግባትና አለመግባት ላይ ባነሳው ክርክር የግል አስተያየቴን ሰጥቼ ነበር፡፡ ይህ የግል አስተያየትም ትብብሩም ሆነ አባል ፓርቲዎች በምርጫው ሂደት ላይ ምንም አይነት ጥያቄ ሳያነሱ ወደ ምርጫው እንደሚገቡ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭቷል፡፡

አንድ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የምርጫ ፓርቲ ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምርጫ ፓርቲ ሆኖ እንደ ስልት በምርጫ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡ ቅድመ ሁኔታ ሊያቀርብ የሚችለው በምርጫው ሂደት ላይ ነው፡፡ በሌላ በኩል አንድ በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለሁ የሚል ፓርቲ ስልጣን ሊይዝ የሚችለው በምርጫ ነውና ምርጫ እገባለሁ ብሎ ሊያውጅ አይችልም፡፡ የምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ደግሞ ከምርጫው ራሱን አገለለ ማለት አይደለም፡፡ እኛ በምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከአሁኑ ራሳችን ከምርጫ ያገለልን የሚመስላቸው አካላት አሉ፡፡ ግን እኛ ራሳችን አላገለልንም፡፡ ከአሁኑ ምርጫ እንሳተፋለን ብሎ ማወጅም አላስፈለገንም፡፡ ከዚህ ይልቅ ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡

ስለሆነም ምርጫው ሂደት ላይ ጥያቄዎችን አንስተን ምርጫው ፍትሓዊ እንዲሆን እየታገልን ነው፡፡ ስለሆነም በምርጫው ሂደት ላይ አለን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በሂደቱ ላይ አለን ማለት ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ምርጫውን እንሳተፋለን ማለት አይደለም፡፡ በምርጫው ሂደት ሲሳተፍ ቆይቶ ሂደቶቹ ፍትሓዊ ባለመሆናቸው፣ የተነሱት ጥያቄዎች ባለመመለሳቸውና በሂደቱ ላይ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው ምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው ራሱን ከምርጫው ያገለለ ፓርቲ አውቃለሁ፡፡

ከአሁኑ ምርጫው ላይ ጥያቄ በማንሳታችን ከምርጫው ራሳችን አግልለናል ማለት አይደለም፡፡ እኛም ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው፡፡ ሂደቱ ፍትሓዊ ካልሆነ አጃቢ መሆን አንፈልግም፡፡ ለዛም ነው ሂደቱን ለማስተካከል ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል እየታገልን ያለነው፡፡ በትግላችን መሰረት ሂደቱን እናስተካክለዋለን ብለን እናስባለን፡፡

No comments:

Post a Comment