Wednesday, October 29, 2014

በደቡብ ትግራይ፣ ሃገረሰላም ከተማ ህዝባዊ ኣመፅ ተቀሰቀሰ

October29,2014
አምዶም ገብረስላሴ – ከትግራይ

በትግራይ ደቡብ ምስራቅ ዞን ሃገረሰላም ከተማ በሙስና ምክንያት መሰራት የነበረበት ባለ ሁለት መስመር መንገድ ኣንድና በጣም ጠባብ ኣድርገው የደጉዓ ተንቤን ኣስተዳዳሪዎች ሊያሰሩት ሲሉ ሰኞ 17 / 02 / 2007 ዓ/ ም ህዝባዊ ኣመፁ ሊቀሰቀስ ችለዋል።

የኣመፁ መነሻ ከመቐለ ተነስቶ ሃገረሰላም፣ ዓብይ ዓዲ፣ ዓድዋ የሚደርሰው የፌደራል መንግስት በመደበው በጀት የሚሰራው የኣስፋልት መንገድ ሃገረሰላም ከተማ ሲደርስ የድሮ መንገዱ ጠባብና ኣንድ መስመር የነበረ ሲሆን እንደሌሎች የኣገራችን ከተሞች የሚፈቀደው ስታንዳርድ ባለ ሁለት መስመር የከተማ መንገድ መሆን ሲገባው ባለ ኣንድ ኣድረገው ለመስራት በመሞከራቸው ነው።

ስራው ህብረተሰቡ “…እድሉ ሁለተኛ ግዜ ኣይገኝምና የፈረሱ ቤቶች ፈርሰው ለወደፊቱ የከተማዋ እድገት በሚፈቅድ መሰረት እንዲሆን ፈቅደናል…” የሚል ውሳኔ ኮንትራት ለያዘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን የከተማዋ ህዝብ “..እንኳን ደህና መጣቹ..” የሚል ግብዣ ባዘጋጁበት ወቅት ነበር።

ችግሩ የተፈጠረው ኣንድ የከተማዋ “..ሃብታም ነኝ..” ባይ ሰው በመንገዱ ሁለት ኣቅጣጫዎች ፕላስ ዋን ፎቆች ኣሉበት። ይህ ሰውዬ ከወረዳዋ ኣስተዳደር በመመሳጠር “..ለከተማዋ የሚፈርሱ ቤቶች ይውላል..” ተብሎ የተመደበው ብር ተመላሽ በማድረግ መንገዱ በቂ እንደሆነ ኣድረገው “..የተጠና..” ብለው ለመከላከያ ኮንስትራክሽን በመስጠት በጀቱ ተመላሽ እንዲሆን ኣድረገዋል።

ህዝቡ “..ህገ ወጥ ውሳኔው..” ስለደረሰው ወደ ወረዳ፣ ዞን፣ ክልል፣ ፌደራል መንግስት ኣቤቱታ ቢያቀርብም ሰሚ ጀሮ ኣላገኘም።
“.. ሃብታም ነኝ..” ባይ ሰውዬም 2 ሌሎች ሰዎች ኣስከትሎ እስከ ፌደራል መንግስት የወረዳው ውሳኔ እንዲፀና ተከራከረ።

ብር ይዞ በየ ደረጃው ያሉ ኣቤቱታ ሰሚ ኣካላት ኣፋቸው የለጎማቸው ሰውየ ብር ብቻ ሳይሆን የህወሓት ኣገልጋይና ህብረተሰቡ ሁሌ የሚያነሳው የልማት ጥያቄ በማኮላሸት የሚታወቅ ነው።
ተመሳሳይ የሰውየው ተግባር በ1996 በመላ ተንቤን የተነሳው የመሰረተ ልማት ጥያቄ እንዳይሳካ ኣፍራሽ ተራ የተጫወተ ነው።

የመንገድ ስራውና የሙስናው ግልፅ መሆን ኣስገራሚ የሚያደርገው የድሃ የሚባሉ ቤቶች መሃንዲሱ በቀየሰው መሰረት ከፈረሱ ኣንድ ዓመት ማሳለፋቸው ነው። መንገዱ የወረዳው ባለስልጣናት እንደወሰኑ ተግባራዊ ቢደረግ ዚግዛግ ይሰራል።

ህዝቡ ወደ ኣመፅ የተሸጋገረው መንገዱ መሰራት ሲጀምር ነው። ህዝቡ በኣንዴ በመሰባሰብ ስራው እንዲቆም ኣድርገዋል።

ፖሊስ ኣመፁ እንዲ በትን በወረዳው ኣስተዳዳሪዎች ቢታዘዝም የህዝቡ ቁጣ በመስጋት የወሰደው እርምጃ የለም።
ህዝባዊ ኣመፁ እስከ ኣሁን መፍትሄ ኣልተበጀለትም። የመከላከያ ኮንስትራክሽንም ስራው ኣቁሟል።

ኣዎ…! ህዝቡ ኣይኑ ያፈጠጠ ሙስና ሊሸከም ፍቃደኛ ሊሆን ኣልቻለም። መንግስትም ለስልጣኑ ሲል( ለህብ ብሎ መስራት ካቆመ ብዙ ስላደረገ ነው) ኣወንታዊ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንላለን።

No comments:

Post a Comment