September 27,2014
• ለስልጠናው 2,345,000 ብር ይወጣል
ለተማሪዎች፣ ለነዋሪዎች፣ ለመምህራንና ለሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሰጥ የቆየውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን በነገው ዕለት እንዲጀምሩ የተነገሩት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን መቃወማቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
ነገ መስከረም 19/2007 ዓ.ም በሚጀምረው ስልጠና 4100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሳተፉ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆነ ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ይህንም ተከትሎ ሰራተኞቹ ‹‹ስልጠናው የዕረፍት ጊዜያችን የሚሻማ ነው›› በሚል መቃወማቸውን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው ለ11 ቀን የሚቆይ ሲሆን ለአበል 50 ብር እንዲሁም ለባነርና ለሌሎች ቁሳቁሶች 90 ሺህ ብር በአጠቃላይ 2,345,000 (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሽህ) ብር የሚወጣበት በመሆኑ ጊዜና ገንዘብ ከማባከን ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም ሲሉ ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment