Tuesday, September 30, 2014

14ቱ የሰማያዊ አመራሮችና አባላት ለጥቅምት 3 ቀጠሮ ተሰጠባቸው

September 30,2014

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ባደረገበት ወቅት ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በራሪ ወረቀት ሲበትኑ በቁጥጥር ስር ውለው በየካ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት ጣቢያ ውስጥ ደንብ ተላልፋችኋል በሚል በቀበና ፍርድ ቤት ክስ የተመሰረተባቸው 14 የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የቀረበባቸውን ክስ ይከላከሉ ወይስ አይከላከሉ በሚል ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ተስጥቷል፡፡ 

አቃቢ ህግ 14ቱ የፓርቲው አባላት በፖሊስ ጣቢያ እያሉ ‹ፍትህ የለም›፣ ‹ዴሞክራሲ የለም›፣…በማለት ጮክ ብለው ድምጻቸውን በማሰማት የጣቢያውን ደንብ እንደተላለፉ በክሱ ላይ ተመልከቷል፡፡

በሌላ በኩል በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋን ጨምሮ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ሀሙስ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም በአራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ፡፡ በቀጣዩ ቀን መስከረም 23 ቀን ደግሞ የሰማያዊ አርባ ምንጭ አመራሮች በተመሳሳይ ችሎት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment