Augest 6/2014
ፍትህ ሚንስትር ያወጣው መግለጫና ክስ ስሰማ ከልብ አዝኛለሁም አፍረያለሁም፤ ያዘንኩት ሁሉንም መፈርጅ ሊያበቃ አለመቻሉ ሲሆን ፤ ያፈርኩት ደግሞ ክስ ቻርጅ ሣይስጥ መግለጫ መውጣቱ ነው፡፡ የሚሆነው ሁሉ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ ነው፡፡
“ስለመከሰሳችን የምናውቀው ነገር የለም”
አቶ ግዛው ታዬ
የሎሚ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር
ክሱን በተመለከተ የምናውቀው ነገር የለም። ከዚህ በፊት ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ይደወልልን ነበር። እዚያ ሄደን ቃላችንን እንሰጥ ነበር።አቶ ግዛው ታዬ
የሎሚ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር
እኛ አሁን መገረም ነው የፈጠረብን። ሕገ-መንግስቱን አከበራለሁ የሚል መንግስት በምን መልኩ ነው የክስ ዝርዝር ሳይደርሰን፣ መጥሪያ እጃችን ላይ ሳይገባ በመገናኛ ብዙሃን ክሳችንን የሚያሰማን።
አሁን ባለው ሁኔታ ማተሚያ ቤት ገብተናል። እንደሚታወቀው ከሳምንት በፊት ነው ወደ ማተሚያ ቤት የምንገባው። ይህም የሆነበት ባለፉት ሃያ ሦስት ዓመት ውስጥ ማተሚያ ቤት ማግኘት ባለመቻላችን ነው። የወደፊቱን ተፅዕኖ ወደ ፊት እናየዋለን።
አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ለመመስረት ዘጠኝ ወር ብሮድካስት መስሪያቤት ተመላልሰን ነው። አሁን ሥራ በጀመርን በሰባት ወራችን ሊዘጉት ነው።
“የሚሆነው ሁሉ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ ነው”
ቶማስ አያሌው የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
ቶማስ አያሌው የአፍሮታይምስ ጋዜጣ ማኔጅንግ ዳይሬክተር
ፍትህ ሚንስትር ያወጣው መግለጫና ክስ ስሰማ ከልብ አዝኛለሁም አፍረያለሁም፤ ያዘንኩት ሁሉንም መፈርጅ ሊያበቃ አለመቻሉ ሲሆን ፤ ያፈርኩት ደግሞ ክስ ቻርጅ ሣይስጥ መግለጫ መውጣቱ ነው፡፡ የሚሆነው ሁሉ ከምርጫ 2007 ጋር በተያያዘ ነው፡፡
source zehabesha
No comments:
Post a Comment