June 20/2014
በሰሜን ጎንደር ምዕ/አርማጨሆ ወረዳ አብርሃጅራ ከተማ የአንድነት ፓርቲ የወረዳ የፋይናንስና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ የሆነው አቶ ደስታው ተገኝ ከአ.አ ዩኒቨርስቲ በ2000 ዓ.ም በቢዝነስ ኢዱኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ካገኘ በኋላ በሐረር፣ በጎንደር ያስተማረ ሲሆን በም/አርማጨሆ ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት የመማር ማስተማር ጉዳይ ፈፃሚ ሆኖ ከ4 ዓመት በላይ አገልግሏል፡፡ በት/ቢሮው ለማስትሬት ትምህርት ዕድል ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበረ ቢሆንም ለ3 ዓመታት ተከልክሏል፡፡ በትምህርት ቤቱ በሚደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶችን የሚፈጸሙ ስህተቶችን በስብሰባ በመግለጹ ኃላፊውን ሰድበሃል፤ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ቁጥራቸው 4 ሆኖ ሳለ 40 እና 80 እየተባለ ሪፖርት ሲደረግ በውሸት መመራት መቆም አለበት በማለቱ የአንድ ወር ደሞዝ ቅጣትና ከነበረው ደሞዝ 2249 ወደ 1400 ብር ዝቅ ብሎ ለ 1 ዓመት ከ6 ወር እንዲሰራ የወረዳው ት/ቢሮ ጽ/ቤት ወስኖበታል፡፡ ት/ቢሮው ያለአግባብ የወሰነበት ውሳኔ ተገቢ ባለመሆኑ ለአቤቱታ ወደ ባህር ዳር ሲቪል ሰርቪስ ሄዶ ሲቪል ሰርቪሱ ለት/ቢሮው ግንቦት 5 እና በድጋሚ ግንቦት 15 ደብዳቤ ጽፎ እንዲቀርቡ ቢልም ለመቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለመጨረሻ ጊዜ ለግንቦት 29 እንዲቀርቡ የተጻፈውን ደብዳቤ አንቀበልም በማለታቸው በፖሊስ ሳጅን ፍቃዱ አማካይነት ደብዳቤውን ተቀበሉ፡፡ ምዕ/አርማጨሆ አብርሃ ጅራ ት/ቢሮ ጽ/ቤት መልስ ሰጪ በዕለቱ በቀጠሮ ቢገኙም አቤቱታ አቅራቢው አቶ ደስታው ተገኝ አልተገኘም፡፡ ከግንቦት 29,2006 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ አቶ ደስታው ተገኝ የእጅ ስልኩ አይሰራም ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ለ14 ቀን ያለበትን ሁኔታ ባለማወቃቸው በድንጋጤ ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት በወረዳው ያሉ የብአዴን አመራሮች “በመለስ ተቃዋሚን ዜሮ ማድረስ” በሚል መፈክር የተቃዋሚ አባሎች ላይ የሚደረግ እስርና እንግልት እንዳለና አቶ ደስታው ተገኝም የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለአቤቱታ በሄደበት ሳይታፈን እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment