Wednesday, May 21, 2014

አቶ ስብሐት ነጋ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ እንዲወያዩ ኢኒሼቲቭ እወስዳለሁ አሉ

May 21/2014

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23 አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል ተቀራረበው መነጋገር እንዳለባቸው ተግባብተዋል።
አቶ ስብሐት ነጋ መንግስትም ድክመቶቹን ማረም አለበት ፣ 1፣ 2፣ 3 እያለን መነጋገር አለብን ያሉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ የሚነጋገሩብት መድረክ ማን ያዘጋጅ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው «እኔ ኢኒሼቲቩን እወስዳለሁ» ሲሉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መድረኩን እንደሚያዘጋጁ ቃል ገብተዋል።
አቶ ግርማ ሰይፉ ና አቶ አበባዉ መሃሪ በበኩላቸው፣ የአቶ ሰብሐትን ኢኒቼቲቭ እንደሚደግፉና በሚደረጉ ዉይይቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመከፈል ዝግጁ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ አቶ ስብሐትን ለወሰዱት ኢኒቼቲቭ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አስራት በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን ድሃ የሆንበት ነገር ቢኖር አንዱ ተቀራረቦ መወያያይ አለመቻላችን መሆኑን አስረድተው፣ በአገር ጉዳዩ ዙሪያ ተቀራረቦ መነጋገሩ ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አበባው የኢትዮጵያ ምሁራን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን የአቶ ስብሐትን ኢኒቼቲቭ እንዲደግፉ ጥሩ አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment