April 17/2014
ሶስት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ገብተዋል
“ረብሻውን ያነሱት ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው” የከተማው ኮሙዩኒኬሽን)
“ባህርዳር በተካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎ ተፈጽሟል” በማለት የተቧደኑ ወጣቶች፣ ባለፈው ሐሙስ የሱሉልታ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ ድብደባ ፈፀሙ፡፡
በድብደባ በርካታ ሰዎች ከመጐዳታቸውም በተጨማሪ፤ ቤት ንብረት ላይም ጥፋት እንደደረሰ የተናገሩት ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ጉዳዩን ሕገወጥ ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡ የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ፤ የስፖርት ውድድርን ሰበብ በማድረግ ረብሻ የቀሰቀሱ ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ ወሮበሎች ናቸው ብለዋል፡፡
ረብሻውን ቀስቅሰዋል ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ አራቱን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ገልፀዋል ሃላፊው፡፡
“የቤቴ በርና መስኮት እንዳልነበር ሆኗል፤ አጥር ተገነጣጥሏል፤ መስኮቶች ዱቄት ሆነዋል” ያሉት አንድ የከተማዋ የረጅም ጊዜ ነዋሪ፤ ከ30 በላይ ቤቶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ የስድስት ልጆች እናት እንደሆኑ የገለፁልን ሌላዋ ነዋሪ፤ በቤታቸውና በንብረታቸው ላይ አደጋ መድረሱን ጠቅሰው፤ እንደሌሎች ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ባያጋጥማቸውም በእጃቸው ላይ በደረሰባቸው ጉዳት በከተማዋ አንድ ክሊኒክ ህክምና እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡
“ይህ ህዝቡ በሰላም አብሮ እንዳይኖርና እንዳይግባባ ሆን ተብሎ የሚጫር የነገር እሳት ነው” ያሉት የ56 አመት አዛውንት በበኩላቸው፤ መንግስት መፍትሔ ከላበጀለት በቀር በአሁኑ ወቅት ከየአቅጣጫው የምንሰማው በዘር ተቧድኖ ግጭት የመፍጠር ጉዳይ አስጊ ነው ብለዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ከበደ፤ ከከተማ አስተዳደር በደረሳቸው ሪፖርት ተዘዋውረው እንደተመለከቱ ገልፀው፣ የተወራውን ያህል ባይሆንም የስምንት ቤቶች የበርና የመስኮት መስታወቶች ተሰባብረዋል፤ የቆርቆሮ አጥሮች ተገነጣጥለዋል ብለዋል፡፡ ሰዎች አራት እንደተጐዱና የሶስቱ ሰዎች ጉዳት ከፍተኛ ስለሆነ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሆስፒታሎች ውስጥ በክህምና ላይ መሆናቸውን አቶ መሳይ ጠቅሰው፤ አንዲት እናት በእጃቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው በከተማው ጤና ጣቢያ ታክመው ተመልሰዋል ብለዋል፡፡
“የረብሻው መንስኤ በቅርቡ ባህርዳር የተካሄደው የመላው ኢትዮጵያ ጫዋታዎች ውድድር ላይ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ አድልዎና ተፅእኖ ተደርጓል የሚል ሰበብ ነው” ብለዋል አቶ መሳይ፡፡
“በረብሻው ዙሪያ ህዝቡንና የከተማ ነዋሪውን በመሰብሰብ ረብሻውን ያስነሱት ሰዎች ህዝብን የማይወክሉ እና ህዝብን ለማጋጨት ፍላጎት ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መሆናቸውን ተወያተናል” ያሉት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊው፣ ህዝቡ እንዲህ ዓይነት ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦችን አሳልፎ እንዲሰጥ ተግባብተናል ብለዋል፡፡ ረብሻው ወዲያውኑ በፖሊሶችና ከጫንጮ በመጡ የፀጥታ ኃይሎች መቆሙን ተናግረዋል - ሃላፊው፡፡

No comments:
Post a Comment