April 30/2014
ኢሕአዴግ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ፣ በተለይም ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለዉ ሕግ ወጥና ኢሰብአዊ ጥቃት አወገዘ። ዜጎችን የሚያምኑበትን የመናገር ሙሉ መብት እንዳላቸው ያስቀመጠው የአንድነት መግለጫ፣ ተቃዉሞ የሚያስሙ ወገኖች ሊደመጡ እንጂ ሊደበደቡና ሊታሰሩ እንደማይገባም ይገልጻል።
አንድነት፣ በቅርቡ የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መርህ፣ አዲስ አበባን ጨመሮ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢሕአዴግ መሬትን እንደ መጨቆኛና መበዝበዣ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀመበት እንዳለ የሚገልጸው የአንድነት መግለጭ፣ ከድሃው ገበሬ አሥር ብቻ በመስጠት የነጠቀዉን መሬት በ 17 ሺህ ብር በጨረታ እንደሚሽጥ እና ልማት ሳይሆን ገበሬዉን በማፈናቀልና በማደህየት የሚደረግ ዘረፋ እያደረገ እንዳለ ለማሳየት ሞክሯል።

ከጥቂት አመታት በፊት በመቀሌ ፣ በተለይም ከኤርትራ የመጡ ስደተኞች ከሚኖርባቸው ቤቶች፣ የሚኖሩበት አካባቢ ለልማት ያስፈልጋል ተብሎ በሃይል እንዲፈናቀሉ መደረጉ፣ በጋምቤላ ደግሞ ከመሬት ጋር በተገናኘ በሺሆች የሚቆጠር በአገዛዙ በግፍ መገደላቸዉ ይታወቃል። በቤኔሻንጉል ጉሙዝ፣ በአምቦ አካባቢ ፣ በወለጋ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ቦታዎች ፣ ዜጎች «ይሄ አገራችሁ አይደለም» በሚል፣ ከአንድ ብሄረሰብ በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉበት ሁኔታ እንዳለ በስፋት ተዘግቧል።
የአንድነት ፓርቲ በመገለጫዉ፣ የታሰሩ የኦሮሞ ተማሪዎች በአስቸኳይ ተፈተዉ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥይቋል።
በአንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች አካባቢ «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት፣ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት» የሚሉ፣ በአንዳንድ ዉጭ ባሉ አክራሪዎች የሚሰማ መፈክር በስፋት ሲስተጋማ እንደነበረ፣ ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የኦሮሞ ተማሪዎች በሚያነሱት ጥያቄ ላይ ቅሬታ እንዳደረባቸው በመግልጽ እየጻፉ ነው።
በኦሮሚያን እና በአዲስ መካከል ግዛቱ የትና እንዴት መሆን እንዳለበት፣ የአንድነት ፓርቲ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። እንደዚያም ቢሆን ግን ፣ ፓርቲዉ አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሰረተዉ ፌዴራል አወቃቀር፣ ያለ ሕዝብ ፍቃድ በጉልበት በሕዝቡ ላይ የተጫነ በመሆኑ፣ እንደገና ቋንቋን ጨምሮ፣ የሕዝቡን አሰፋፈር፣ ጂዮግራፊን፣ ኢኮኖሚን ፣ የሕዥቡን ፍላጎት እንደኢሁም ሌሎች ነጥቦች ባካተተ መልኩ እንደገና መዋቀር አለበት እንደሚያምን በፖለቲካ ፕሮግራሙ በግልጽ አስቀምጧል። ለፓርቲዉ ቅርበት ያላቸው እንደሚናገሩት፣ አሁን በኦሮሚያና በአዲስ መካከል የተፈጠረው ዉዝግብ አሁን ያለው ፌደራል አወቃቀር ያመጣው ጣጣ እንደሆነ በማስረዳት፣ የፌደራል አወቃቀሩ እንደገና ፣ ሁሉን አቀፍና ዴምክራሲያዊ በሆነ መንገድ ከተዋቀረ፣ ብዙ ችግሮች እልባት እንደሚያገኙ ይናገራሉ።
No comments:
Post a Comment