Thursday, March 20, 2014

የአዲስ አበባ የዉሃ ችግር

March 20/2014










የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግርን በተመለከተ የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ውሃ በፈረቃ የሚያገኙበት ያልታወጀ አሰራር እየተስተዋለ ነው። ብዙ አካባቢዎች ከ24 ሰዓታት በላይ የመጠጥ ውሃ በተደጋጋሚ በመጥፋቱ ነዋሪዎች መደበኛ ሥራዎቻቸውን ጭምር በመተው ጄሪካን ይዘው ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ የሚንከራተቱበት ትይዕንት አዲስነቱ እየቀረ የመጣ ይመስላል።

አቶ ድሪባ ኩማ ግን በያዝነው በጀት ኣመት ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ የውሃ ምርትን መጨመር መሆኑን ይናገራሉ። “በበጀት ዓመቱ በአቃቂ ዋልፊልድ የ19 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና ተያያዥ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። ከእነዚህ
ጉድጓዶች 70ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማምረት ታቅዶ 80ሜትር ኪዩብ ማምረት ተችሎአል። በቅርቡ የውሃ ማሰባሰቢያ ሪዘርባየር ሥራው እንደተጠናቀቀ ምርቱ ወደ ሥርጭት ይገባል።
ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲ ዊልፊልድ የ11 ጉድጓዶች ሲጠናቀቅ እስከ 40ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት ያስችለናል። እንዲሁም የለገዳዲ ማጣሪያ ጣቢያን በማስፋትና የድሬ ግድብን በማሻሻል የማጣሪያ ጣቢያውን የማምረት አቅም ወደ 195ሺ ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰራ ነው። የድሬ ግድብ ሲጠናቀቅ 30ሺ ሜትር ኪዩብ የውሃ ምርት የምናገኝበት ሲሆን ይህ የማስፋፊያ ግንባታ በ2007 ዓ.ም ክረምት ውሃ መያዝ ጀምሯል። እንዲሁም 70ሺ ሜትር ኪዩብ ማምረት የሚያስችል የ24 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮና ተያያዥ የሲቪል ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በዚህ ፕሮጀክት
እስካሁን ድረስ ከተጠናቀቁ 16 ጉድጓዶች ብቻ 94ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማግኘት ተችሏል።
ይህም ከፕሮጀክቱ ከሚጠበቀው 70ሺ ሜትር ኪዩብ በላይ ነው። ስለሆነም የተጀመሩ የሲቪልና መካኒካል ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ምርቱ ወደሥርጭት ይገባል። በአጠቃላይ ወደ 260ሺ ሜትር ኪዩብ የሚጠጋ ውሃ ማምረት የሚያስችል ሥራ እተሰራ ነው። ይህ ማለት እስከአሁን በቀን በአማካኝ የውሃ ምርታችን 359ሺ ሜትር ኪዩብ ሲሆን አሁን ያገኘነው 260ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደስርጭት ሲገባ የከተማዋ ውሃ አቅርቦት ችግር ይፈታል፤ የውሃ ምርታችንም ወደ610ሺ ሜትር ኪዩብ ያድጋል ብለዋል።
የውሃ አቅርቦት እጥረት ባለባቸው ዳገታማ አካባቢዎች ጊዜ የማይሰጡ አጣዳፊ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ እስከ30ሺ
ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚይዙ 50 ትላልቅ የውሃ ታንከሮችና 20 ቦቴዎችን የማቅረብ ሥራ ተጀምሯል። በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች የውሃ ጉድጓዶች በስፋት በመቆፈር ውሃን ማምረት እንዲቻል 5 ዘመናዊ ሪጎች ከኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ የፌዴራል መንግስት ገዝተው ለከተማ አስተዳደር ድጋፍ አድርጓል።
ከረዥም ጊዜ አኳያ የውሃ አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የገርቢ ግድብ ጥናት ተጠናቆ ለግንባታ ሚሆን ፋይናንስ
እየተፈለገ ሲሆን በቅርቡ ወደግንባታ ይገባል። የአዲስ አበባ ውሃ አቅርቦትን ከ25-30 ዓመት ድረስ የሚቃለልበት ሌሎች ተጨማሪ ግድቦችን ለመሥራት ጥናቶች መጀመራቸውን ከንቲባው በመግለጽ መጪው ጊዜ ብሩህ መሆኑን
በንግግራቸው አመላክተዋል።

No comments:

Post a Comment