Tuesday, March 4, 2014

የደሴ ሕዝብ በኢሕኣዴግ የግዳጅ መዋጮ ተማሯል::በደሴ ወንጀል በመበርከቱ የሰአት እላፊ ገደብ ተጥሏል:: በከተማዋ ፌዴራል ፖሊሶች በምሽት ወታደራዊ ልምምድ ያደርጋሉ::

February 3/2014

በምንሊክ ሳልሳዊ

የደሴ ሕዝብ ከመለስ ፋውንዴሽን ጋር በተያያዘ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ይፈለግበታል::

 ከደሴ የሚደርሱኝ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሕወሓት አዛዥነት በብኣዴን ሰብሳቢነት የመለስ ዜናዊን አመራር አካዳሚ ሕንጻን ለመገንባት የመለስ ፋውንዴሽን ከህዝቡ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚጠበቅበት እና ለግንባታው የግዴታ አስታውጾ እንዲያደርግ እያስገደዱት መሆኑን እና ሕዝቡም ከኑሮ ውድነት ጎን ለጎን ከአፉ ላይ ሊጎርሰውን ያዘጋጀውን በጉልበተኞች እየተነጠቀ መሆኑን በማማረር አቤቱታውን ማሰማቱን የደሴ የለውጥ ሃዋርያ ወጣቶች አንድነት ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው መረጃ ገልጽዋል::

መረጃዎቹ እንደጠቆሙት የገንዘብ አሰባሰቡ ሂደት በሁሉም ክፍለከተሞች ባሉ የወያኔ ካቢኔዎች ሲሆን እያንዳንዱ የካቢኔ አባል በግል እንዲሰበስብ የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ የተሰጠው ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ለሰበሰበ ሽልማት ስለሚሰጠው የሚል ቅል ስለተገባላቸው የስልታን እና የደሞዝ እድገት ለማግኘት እና ታማኝነታቸውን ለማረጋገጥ በሽፍን ድጋፍ ሕዝቡን በግዳጅ እና በማስፈራራት በዛቻ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያደረጉት ሲሆን ይህንን በተመለከተ ሕዝቡ በቤቱ አሊያም በስብሰባ ካልተገኘ በቅጣት ሁሉ መልክ ተጨማሪ እንዲከፍል ይደረጋል የሉት የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ሕዝቡ በሚሄድበት መስሪያቤት አሊያም ስብሰባ ቀደም ብሎ የከፈለ ሰው ደረሰኙን ካልያዘ ጉዳዩን ለማስፈጸም በድጋሚ እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን እረስቸዋለሁ ሄጄ ላምጣ የሚል ነገር ተቀባይነት የለውም::

እንዲሁም በደሴ የብኣዴን ጽ/ቤት ሃላፊነት ተጨማሪ ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል በግዳጅ ገንዘብ እየተሰበሰበ ሲሆን የጽ/ቤቱ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጌታዊ ይርጋ (የቀድሞ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ) ከዚህ ቀደም በሙስና ታስረው የነበሩ እና ከህግ ውጪ ለፖለቲካው አስፈላጊ ሆነው በመገኘታቸው በትእዛዝ ከተፈቱ በኋላ ሲቭል ሰርቭስ ኮሌጅ ተልከው ሰልጥነው በደሴ የብኣዲን ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው ከተመደቡ ጀምሮ በግዳጅ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖረውን በኑሮ ውድነት የተማረረውን ህዝብ እያስገደዱ የመንግስት ሰራተኛውን ከደሞዙ ላይ 30% እንዲቆረጥ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም በየቤቱ የብኣዴን ካድሬዎች እየዞሩ ከቀበሌ ሰዎች ጋር በመሆን ሕዝቡ 100 ብር እንዲከፍል በበደል ላይ በደል እየፈጸሙበት ይገኛል:: እንዲሁም ባለሃብቱን እያስገደዱት ያሌለን ገንዘብ እንዲተፋ ወጥረው ይዘውታል ሲሉ ለምንሊክ ሳልሳዊ መረጃውን ልከዋል::

በሌላ ዜና በደዜ ከተማ ዙሪያ ጨለማን ተገን አድርገው የሰዎች ግድያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች ከበፊቱ በበለጠ በመበርከቱ የከተማው ፖሊስ መምሪያ ማንኛውም የከተማው ነዋሪ ከምሽቱ አራት ሰአት በኋላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የሰአት እላፊ ገደብ መጣሉን የከተማው ነዋሪዎች ለምንሊክ ሳልሳዊ በስልክ ገልጸውለታል::

ባለፉት ሁለት ቀናት በመላው አገሪቱ የተካሄዱትን ፍተሻዎች በተመሳሰለ መልኩ የሞባይል ቤቶች እና የኢንተርኔት ካፌዎችን እንዲሁም የመረጣቸውን ብሎም የጠረጠራቸውን ግለሰቦች በድንገት ፍተሻ በማካሄድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሞባይሎች ላፕቶፖች ዲስክቶፖች ኮምፒተሮች እና የሚሞሪ ካርዶች ሰብስቦ የወሰደው የደሴ ፖሊስ ሰአት እላፊውን ጥሶ የተገኘ ነዋሪ በጸጥታ ሃይሎች ለሚወሰድበት ማንኛውም እርምጃ መንግስት ተጠያቂ እንደማይሆን ገልጿል::

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ የደሴ ከተማ በፌዴራል ፖሊስ ወታደራዊ ልምምድ ተወጥራ እንደምታመሽ ታውቋል:; ቁጥራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊሶች ከምሽቱ 3 30 ጀምሮ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ በዋናው የከተማዋ መንገዶች በመጠቀም ላይ ሲሆኑ በህዝቡ ላይ ሽብር እየነዙ መሆኑን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ነግረውታል::ይህንን እያደረጉ ያሉት የከተማውን ነዋሪ ለማስፈራራት እና ለማሸበር እየጣሩ እና በሃርቡ አከባቢ የሚንቀሳቀሱ የፌዴራል ፖሊሶች ለሊቱን በወታደራዊ ልምምድቸው ጊዜ ስለሚጮሁ ህዝቡን ከስራ ቤቱ ገብቶ እንዳያርፍ እንቅልፍ እየነሱት ሲሆን ምን ያክል መንግስት ጭንቀት ላይ እንዳለ ያሳያል ሲሉ መረጃውን የላኩት ነዋሪዎች ገልጸዋል::መረጃውን ላቀበላችሁኝ የደሴ ወጣቶች አመሰግናለሁ ::ምንሊክ ሳልሳዊ:

:

No comments: