march16/2014
ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል:
ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል:
ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል::
ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል::
የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል::
በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል::
የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም::
No comments:
Post a Comment