Thursday, February 6, 2014

በሃረር የህዝብ ብሶት ይገነፍላል የሚል ስጋት አይሏል::የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ በዘር ማንዘር የተሳሰረ የሙስና ሰንሰለት ዘርግቷል::

February 5/2014

የሐረር ሕዝብ ብሶቱ ቀጥሏል፡፡ አዲስ አበባ ያሉ ባለሥልጣናትም ዝምታቸው ቀጥሏል፡፡

በሃረሪ ብሄራዊ ሊግ የሚመራው የሃእርሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት እያለ ራሱን የሚጠራው ወያኔ ሰራሹ የጎሳ ጁንታ በሃረር እና አከባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደሎችን እየፈጸመ እንዲሁም ሃገርን እና ህዝብን እየዘረፈ በሙስና እና በመልካም አስተዳደር አጣብቂኝ ውስት ተዘፍቆ ህዝቡን እያስለቀሰ መሆኑን ከአከባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በሐረር የሚገኙት የክልሉ ባለስልጣናት ዋና ግባቸው ስለልማትና ስለ መልካም አስተዳደር ሳይሆን ዘርፎ ስለመክበር እና በጫት ሱስ እግርን አጣጥፎ ከቤት ተጎልቶ መዋል ከሆነ አመታቶች ተቆጥረዋል፡፡ የክልሉ መንግስት መዋቅር በጎሳ የተቆጣጠረ በዘመድ አዝማድ፣ በዘር የተያያዘ በመሆኑ ማን ለማን ጥያቄውን አቤቱታውን እና ብሶቱን ማሰማት እንዳለበት አስቸጋሪ ሆንዋል፡፡

 ከዚህ ቀደም አዛውንቶችን በመደብደብ ሰውን ከነህይወት በማቃጠል እና ፍርድ በማጓደል እንዲሁን ከባድ ወንጀሎችን በመስራት የተካነው የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ እና አባሎቹ እንዲሁም የኦሕዴድ ተጠሪዎች ማሰር፤ ማባረር በፍርድ ቤት ማስወሰን፣ መቀማት፣ በልዩ ኃይል ማስደብደብ የመሳሰሉትን ድርጊታቸው የእለት እለት ተግባር ስለሆነ ሕዝቡ ለምዷቸዋል፡፡ በሃረር በጎሳ እና ካልተሳሰሩ የገንዘብ ሰንሰለት ካሌለ ባለሀብት የመሆን እድሉ የለም ፡፡ ማንኛውም ነገር የሃሰት እና የይስሙላ ነው፡፡ ለሐረሪ ብሔራዊ ሊግ ገንዘብ ካልከፈለ ባለሀብት መባል ዘበት ነው::

ክልሉ የህዝቡን ትርታ ለማዳመጥ በሚል ለይስሙላ በጠራው ስብሰባ ላይ የተለያዩ ድርጅቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ተሰባስበው ውይይት በተደረገበት፣ የክልሉን ጉድፍ ያጋለጡና የተናገሩ ግለሰቦች በማግሥቱ የሥራ ዕገዳና ማስጠንቀቂያ እንዲደርሳቸው መደረጉ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የህዝብን ብሶት ያሰሙ የመብት ረገጣ ዛቻ እና ስድብ ደርሶባቸዋል እየደረሰባቸውም ነው::

ይህንን ዘገባ ያጠናከረው ምንሊክ ሳልሳዊ እንዳለው ከከተማው የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት በሐረሪ የህግ ትርጉም በተግባር ሳይሆን በሃሰት-የህዝብ እድገት በጋራ ሳይሆን በወረቀት እና በጎሳ ነው፡፡ ከከፍተኛ የክልሉ አመራር ጀምሮ እስከቀበሌ ሹማምንት በውሸት የተሞሉ ናቸው::ዘረኝነትና የጎጥ መጠራራት ገንኖ፣ የጎሳ ፖለቲካ አክራሪነት ተስፋፍቶ፣ የሰው መብት እንደ ትቢያ በሚበተንበት ክልል፣ መልካም አስተዳደር አለ ተብሎ በፌዴራሉ ቱባ ባለስልጣናት መነገሩ የሚያስተዛዝብ ነው፡፡ ከማእከላዊ የመንግስት ቢሮዎች የሚመጡ የፌዴራሉ ባለስልጣናት የሚቀርብላቸውም ሆነ ይዘውት የሚሄዱት ሪፖት እጅግ አስደንጋጭ መሆኑ እየታወቀ የፌዴራል ባለስልታናት ዝምታ የፖለቲካ ስልጣን ማስጠበቂያ አስመስሎታል:: ህዝብን የሚያዳምጥ አስተዳደር ያጣው የሃረር ነዋሪ ቁጣው ገንፍሎ አደባባይ ሊወጣ ይችላል የሚል ስጋቱ አይሏል::የምንሊክ ሳልሳዊ ዘገባ::

No comments:

Post a Comment