Feb.4/2014
በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡
ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት ሰሜን ሸዋ በቅንጅት እጩ ሲሸነፍ፣ አያሌው ደግሞ በማርቆስ ከተማ በባሶ ሊበን ወረዳ ሊያሸንፍ ችሏል (አሸናፊነቱ ምንም እንኳ እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ተወዳዳሪዎች በድርጅታዊ የድምፅ ስርቆት የተገኘ ቢሆንም) ከ1998 ዓ.ም አንስቶ እስከያዝነው አመት መጀመሪያ ወራት ድረስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ የቆየው አያሌው ጎበዜ ‹‹ለሱዳን ተሰጠ›› ወይም ‹‹ሊሰጥ ነው›› ከተባለ መሬት ጋር ተያይዞ የማጀገኑና የማንፃቱ ቅስቀሳ የኑፋቄን መንገድ የተከተለ ይመስለኛል (የጉዳዩ ስሁትነት የኛይቷን ‹ፋክት› መፅሄትንም ይጨምራል) በደፈናው ከዚህ ቀደም ‹አያሌው ለሱዳን በሚሰጥ መሬት ላይ አልፈርምም በማለቱ፣ ደመቀ መኮንን ፈረመ› የሚባል ምንጩ የማይታወቅ ወሬ ሁላችንም ጋ ደርሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከብአዴን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት፣ አያሌው ያውም ርህራሄ አልባ የነበረውን የጉልበታሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ውሳኔ ተቃውሞ ‹ፈርም›፣ ‹አልፈርምም› አይነት አንጃ ግራንጃ የሚፈጥር ደፋር ልብ ያሌለው መሆኑን ነው፡፡ በግልባጩ ፖለቲካችን ጉራማይሌ ነውና ለብአዴን ፍቅር በሌላት ባሕር ዳር አያሌው ተወዳጅ እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ የተወዳጅነቱ ሚስጥር ግን ከድርጅቱ ይልቅ ‹‹መረጠኝ›› ለሚለው ሕዝብ ታማኝ በመሆኑ እና በሀገር ጥቅም ከእነ ‹ኦቦ› አዲሱ ለገሰ ተሽሎ ሳይሆን፣ ከራሱ የግል ባህሪና ሰብዕና ጋር ስለሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ካሉ ነዋሪዎች እና አብረውት ከሚሰሩ የበታች ሰራተኞች ጋር የመሰረተው ማሕበራዊ ግንኙነት ዋነኛው ነው፤ በርግጥም የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው ሲሞት ቀብር ላይ ይገኛል፤ ማታም እዝን ይዞ በመሄድ ሲያፅናና ያመሻል፤ ሰርግን በመሳሰሉ የደስታ ዝግጅቶችም ላይ እንዲሁ ይሳተፋል፤ እነበረከት ስምዖን ለሚያቀነቅኑት ግራ ዘመም ፖለቲካም ሩቅ በመሆኑ፣ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ባህሪይ ይስተዋልበታል፤ ለአብነት እምነቱ የሚያዝዘውን (ከመፆም ጀምሮ በቤተ-ክርስቲያን ተገኝቶ እስከ ማስቀደስ ያሉ ጉዳዮችን) እንደ ባለሥልጣን ግብዝ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተራ አማኝ ዕለት ተዕለት ሲፈፅም ይታያል፡፡ በቤተሰብ አስተዳደርም ቢሆን አራት ልጆቹን መንግስት ትምህርት ቤት ከማስተማር አልፎ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ስነ-ምግባር ማሳደጉን፣ ብልሹ አድርገው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ካሉ ከአንዳንድ ኃላፊነት ከማይሰማቸው ባለሥልጣናት ጋር አነፃፅረው የሚያመሰግኑት የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በህክምና በማዕረግ የተመረቀችውን ብቸኛና የመጀመሪያ ሴት ልጁንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡
የሆነው ሆኖ ብአዴን በበረከት ስምዖን፣ በአዲሱ ለገሰ፣ በካሳ ተክለብርሃን፣ በታደሰ ጥንቅሹ እና በከበደ ጫኔ ስም የመሰረተው ‹‹ጥረት›› የተሰኘው ኮርፕሬሽን ዳሽን ቢራ፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ ዘለቀ እርሻ፣ አምባሰል አስመጪና ላኪ፣ ጣና ሞባይል እና ጣና ፍሎራ የተሰኙ የንግድ ድርጅቶችን ያስተዳድራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አትራፊ የሚባለው ዳሽን 49 ፐርሰንቱን እንግሊዝ አገር ለሚገኝ አንድ ቢራ አምራች ድርጅት ሲሸጥ፤ ጣና ሞባይልም በአሜሪካን ሀገር የታወቀው የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው ወልደሉዑል ካሳን ጨምሮ ለአራት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻን አስተላልፏል፡፡ ይህ ሁኔታም ድርጅቶቹ ትርፍና ኪሳራቸውን በውጪ ኦዲተር እንዲያስመረምሩ የሚያስገድድ መደላድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አሰራር የእነ አዜብ መስፍን መቀለጃ ከሆነው ‹‹ኤፈርት›› በተሻለ መልኩ ለዘረፋ እንዳይጋለጥ መታደጉ አከራካሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንግሊዛዊው ድርጅት የዳሽን ቢራ 49 ፐርሰንት ድርሻን ገዝቶ ሲያበቃ፣ ወጪና ገቢውን አይከታተልም ማለቱ ሩቅ ነውና፡፡
በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን፡፡
ጎንደር እና ጥምቀት
የሁሉም መነሻና መድረሻ ዓላማ መንፈሳዊ ይሁን እንጂ እንደ መስቀል፣ ጥምቀትና ሬቻ… ያሉ አንዳንድ በዓላት ከመንፈሳዊነታቸው በተጨማሪ የባሕል መገለጫ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ከዚህ የተነሳም በዓላቶቹ በሚከበሩባቸው ቦታዎች የሚገኘው ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ፣ ሰማያዊውን ፅድቅ ብቻ ሳይሆን፣ በባህላዊው አከባበርም በእጅጉ ስለሚማርክ ጭምር ነው፡፡
የሆነው ሆኖ በወዳጆቼ ጋባዥነት የዛሬ አስራ አምስት ቀን በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል ላይ ተገኝቼ ነበር፤ በወቅቱም የታዘብኩት ጉዳይ ከሺህ ዓመታት በፊት የተፈፀመ አንድ ክስተትን እንዳስታውስ ገፊ-ምክንያት ሆኖኛል፤ ይኸውም በዘመነ ኦሪት የምድረ ባቢሎን ሰዎች አምላካቸውን ከመንበረ ሥልጣኑ ለመገልበጥ አሲረው ወደ ሰማይ የሚያወጣቸውን ታላቅ ግንብ መገንባት የጀመሩ ጊዜ አምላክ በድርጊታቸው ተቆጥቶ ቋንቋቸውን በማደበላለቁ ውጥናቸው በአጭር እንደተቀጨባቸው በመፅሀፉ የተተረከ ነው፡፡ …እነሆም ይህ በሆነ ከሺህ ዓመታት በኋላም የጎንደር ሕዝብ እና መንግስት በአንድ አደባባይ፣ በአንድ ድግስ ላይ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የመግባባት መንፈስ ርቆባቸው፣ ጉራማይሌነታቸው ደምቆ አስተውያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ኢህአዴግ መራሹ-መንግስት ከበረሃ ‹የብሔር ፖለቲካ› የተሰኘ መርዝ ቀምሞ መምጣቱ ሳያንስ፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን (ባንዲራችን) ላይም ኮከብ ይሉት ዲሪቶ ለጥፎ ‹ጨው ቢጠቀለልበት፣ ስኳር ቢቋጠርበት… ምንድን ነው? ያው ጨርቅ ነው!› ማለቱ ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ እጅግ አስቆጥቶት ነበር፡፡ በነዚህና መሰል ድርጊቶቹም የተነሳ ግንባሩ በሀገር ጉዳይ ላይ ዛሬም ድረስ መናፍቅ
ተደርጎ ተቆጥሯል፤ ደግሞም ነው! ምክንያቱም ያቺ ልባችንን በደስታ የምትሞላው ባንዲራ እስከ ደርግ ውድቀት ጧትና ማታ በክብር ስትሰቀልና በክብር ስትወርድ ነው የኖረችው፡፡ ያን ጊዜ በየመንገዱ መኪና ውስጥ ያለው ከመኪናው ወርዶ፣ እግረኛውም የደረሰበት ቦታ ላይ ቀጥ ብሎ ቆሞ፣ ጠዋት ከፍ አድርጎ ሲያውለበልባት፣ አመሻሻ ላይ ደግሞ በዝማሬ አውርዶ በክብር አጣጥፎ ሲያስቀምጣት ማየት በእውነቱ ልብን በከፍተኛ ሃሴት ይሞላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ግና! ዛሬ ዘመን ተቀይሮ፣ ታሪክ ተሽሮ ስንት የደም መስዋዕትነት የተከፈለባት ውድ ባንዲራችን በተሰቀለችበት ዞር ብሎ የሚያያት ጠፍቶ ተበጫጭቃ ሰርግ ቤት የተጎዘጎዘ ወረቀት መስላ መታየቷ በቁጭት አንገብግቦ፣ በሀዘን ልብ ይሰብራል፡፡ እናም ብዙሃኑ ባንዲራ የሚያውለበልብበት አጋጣሚ በተፈጠረ ቁጥር ከፍ የሚያደርጋት ያችኑ ንፅኋን (የድሮዋን) ሰንደቅ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ይሁንና ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ድንገት ከእንቅልፉ የባነነው ኢህአዴግ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሁሉ መውለብለብ ያለበት ኮከብ የታተመበት ባንዲራ ብቻ እንዲሆን በአዋጅ እስከመደንገግ ደርሷል፡፡ ይህንንም አዋጅ ተከትሎ በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በዋና ዋና ከተሞች ባንዲራን በተመለከተ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡
ሰሞኑን በጎንደር ከተማ ያያሁት ግን የዚህን ተቃራኒ ነው፤ ባንዲራችን የባህላዊም ሆነ ኃይማኖታዊ በዓላት ዋነኛ አድማቂ መሆኗ ነባር ልማድ ነው፤ እናም ጎንደር ላይ ዘንድሮ የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት በታቦታቱ ዙሪያ በተለያየ መልኩ የተዘጋጀውም ሆነ ሕዝቡ ያነገበው ሰንደቅ፣ አገዛዙ ‹‹ከዚህ ውጪ…›› ብሎ ለእስር እንደሚዳርግ በአዋጅ የለፈፈለትን ባለ ኮከቡን አይደለም፤ ይልቁንም በብዙሃኑ የሀገሬ ሕዝብ ልብ ላይ የታተመችውን ያችን ንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራ ብቻ ነበር፡፡ …ኩነቱም የፓርቲ ‹ፖለቲካዊ ፍቺ› ሰጥቶ ሰንደቁን ላዥጎረጎረው ኢህአዴግ ‹‹እመራዋለሁ›› ከሚለው ሕዝብ ያለውን ዕርቀት አመላካች ሆኖ አልፏል፡፡
ሌላው የዕለቱ ጉራማይሌ ክስተት በተለያየ ቅርፅ የተሰሩ፣ የኢትዮጵያን መልከዓ-ምድር የሚያሳዩ ሶስት ግዙፍ ካርታዎች በመኪኖች ላይ ተጭነው ለዕይታ አደባባይ መቅረባቸው ነው፤ እነዚህ ካርታዎች የሚያመላክቱት የሀገራችን ሰሜናዊ ድንበር መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ ትግራይ ላይ ተገድቦ እንዲቀር ከሻዕቢያ ጋር የተዋዋሉበትን አይደለም፤ ስመ-ጥሩው ጀግና አሉላ አባነጋ ጦሩን ሰብቆ ‹ቼ ፈረሴ› ብሎ እስከጋለበበት ቀይ ባህር ድረስ የሚዘረጋውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ይዞታ ያካተተ እንጂ፡፡
ይህ መሳጭ ትዕይንትም ሕዝብና መንግስት ያለፉትን ሃያ ሁለት ዓመታት መደማመጥ የማይችሉ (ቋንቋቸው የተደበላለቀባቸው) ሆነው እዚህ እንደደረሱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለዚህ አይነቱ ጉራማይሌ ግንኙነት ገፊ-ምክንያት ደግሞ የጎንደር ሕዝብ ሕገ-ወጥ በመሆኑ አልነበረም፤ ገዥው ፓርቲ ይቺን ሀገር ለመመስረት እልፍ አእላፍ ቀደምት አባቶች የሞቱላትን፣ ታሪክ የተሰራባትን ባንዲራ በማን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አህሎኝነት ያሻውን የለጠፈባት ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ጥቅም ያላስከበረ የሀገር ግንጠላ ላይ መሳተፉ የፈጠረው ቁጭት ነው፡፡…መቼም የዕለቱን ኩነት ቋራ ሆቴል በረንዳ ላይ ከእኛ በጥቂት ሜትሮች ዕርቀት ተቀምጦ ቁልቁል ሲከታተል የነበረው በረከት ስምዖንየተጠናወተው የእብሪት ፖለቲካ አይነ-ልቦናውን ካልጋረደበት በቀር ይህ ጉዳይ የሚያስተላልፍለት አንዳች አገራዊ ምስጢር ያለው መሆኑ አይጠፋውም፡፡
ዛሬም መሬት ማስወሰዱ ቀጥሏልን?
ከእነዚህ ክስተቶች በተጨማሪ በአካባቢው የተመለከትኩት ከባድ ውጥረት አለ፤ ይኸውም ‹ለሱዳን ሊሰጥ ነው› እየተባለ የሚነገርለት የመሬት ጉዳይ ካመጣው ጣጣ ጋር የሚጋመድ ነው፤ በርግጥ በአንዳንዶች ዘንድ መሬቱ ወደ ውስጥ ስልሳ (60)፣ ወደ ጎን ደግሞ አንድ ሺህ (1000) ኪሎ ሜትር ድረስ እንደተሰጠ ይታመናል፡፡ ይሁንና በግሌ ይህ ክስ ማረጋገጫ የሚቀርብበት ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
በጉዳዩ ላይ ምክንያታዊ ለመሆንም በዚህ በተጠቀሰው የመሬት ስፋት ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ ከተሞችን መመልከቱ የተሻለ በመሆኑ፣ በቀጥታ ከሱዳን ጋር ከሚዋሰኑ ሁለት ከተሞች አንስተን እናስላው፤ እናም ከመተማ ከተነሳን ሸህዲን፣ ወህኒ፣ ነጋዴ ባሕር እያልን ጭልጋን እናገኛለን፡፡ መነሻችን ከሌላኛው የወሰን ከተማ ተሂ ከሆነ ደግሞ ምንጁግጁግ፣ ወዲ በርዚን፣ ኩሊት፣ ሸንፋ፣ ማሕበረ-ስላሴ ገዳምን አልፈን ደንገል እንደርሳለን፡፡ እንግዲህ የሰማነው ወሬ እውነት ከሆነ እነዚህ መሬቶች ሁሉ ለሱዳን ተሰጥተዋል ማለት ነው፡፡ ግን ለምን? ኢህአዴግ እንዲህ ሙጭጭ ብሎ የያዘውን ሥልጣን ሊያሳጣው የሚችል ውሳኔ ላይ ለመድረስ (ከተሞቹን ለሱዳን ለመስጠት) የተገደደበት ምን ምክንያት አለ? በነገራችን ላይ ይህ አስተያየት ስርዓቱ ለሀገር ጥቅም ይቆረቆራል እንደማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በሆነ ክፉ ቀን ሥልጣኑን አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ሁኔታ ከገጠመው ሀገር ከመበታተንና ከማፈራረስ የሚመለስ አለመሆኑን የቀድሞው ተሞክሮዎቹ ይነግሩናል፡፡
የሆነው ሆኖ ሊተኮርበት የሚገባው ኢህአዴግ እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሳይሰጥ ያደፈጠበት አንዳች የሸሸገው ሚስጥር ቢኖር ነው የሚለው ይመስለኛል፤ የዚህ መነሻ ምክንያታችን ደግሞ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ በድብቅ ለሱዳን የሰጣቸው (ዛሬ ተወሰዱ ከሚባሉት ውስጥ የማይካተቱ) መሬቶች የመኖራቸው እውነታ ነው፤ ይኸውም ብአዴን የመሰረተው ‹‹ዘለቀ እርሻ›› የተሰኘው ድርጅት በአንድ ወቅት ያስተዳድራቸው የነበሩት አብደረግ እና ደሎል (ሽመል ጋራ እና ምዕራብ አርማጭሆ) ውስጥ በቁጥር ከአንድ እስከ ስምንት የተሰየሙ ግዙፍ የእርሻ መሬቶች ነበሩ፤ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ከቁጥር ሁለት እስከ ስምንት ያሉትን (በድምሩ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ሄክታር የሚደርሱ) መሬቶችን አሳልፎ ሰጥቷል፤ ይህንንም ተከትሎ ‹‹ዘለቀ እርሻ›› እንቅስቃሴ አልባ ሆኗል፡፡ በርግጥ ‹ቆራጦቹ› የብአዴን አመራሮችም ቢሆኑ እንዲህ አይነቱን ጥሬ ሀቅ አይክዱም፤ ይልቁንም ‹ቀድሞውንም ግማሹ ይዞታ የእነርሱ ነበር› ብለው ያስተባብላሉ እንጂ፡፡ …ግና! ማን ነበር ‹‹ከሱዳን ነጥቀን የወሰድነው መሬት አለ!›› ያለው? መለስ ዜናዊ ይሆን?4
እንዲሁም ‹‹ስናር›› የተባለው ከፊል ቦታ ለሱዳኖች መሰጠቱን ከታማኝ ምንጭ ሰምቻለሁ፤ ርግጥ ስናርን ሱዳኖች እንዲቆጣጠሩት በር የተከፈተላቸው የደርግ መንግስት በወደቀበት ማግስት (በ1983 ዓ.ም መጨረሻ) ነው፤ የዚህ ስጦታ መግፍኤ በትግሉ ዘመን ሱዳን ኢህአዴግን ‹አቅፋና ደግፋ› ለድል እንዲበቃ ያበረከተችው ውለታን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ይነገራል፡፡ እናም ሱዳኖች እንደ መና የወረደላቸውን ያልታሰበ ገፀ-በረከት ለመጠበቅ ወደ አስራ ሁለት ገደማ የሚደርሱ ወታደራዊ ካምፖችን መስርተው እስከ 1988 ዓ.ም ድረስ የምድሪቱን በረከት ሲቀራመቱ መቆየታቸው እውነት ነው፡፡ ይሁንና በ1988 ዓ.ም በወቅቱ የሱዳን መንግስት አፈ-ጉባኤ የነበረው ሃሰን አል-ቱራቢ እጅ እንዳለበት የተጠረጠረውን በአዲስ አበባ በቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንነት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ ኢትዮጵያና ሱዳን (በተለይም ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠትና ባለመስጠት ጉዳይ) ግጭት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህን ጊዜም ኢህአዴግ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ‹‹መሬታችሁን አስመልሱ›› በሚል ቀስቅሶ በሱዳናውያን ላይ ያዘምታቸውና ድል ያደርጋሉ፤ ስናርም ተመልሳ በኢትዮጵያውያን ይዞታ ለመጠቃለል በቃች፡፡ ግና! አሁንም እንቆቅልሽ በሆነ ሁኔታ (ከ1999 እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ) እንደገና ወደ ሱዳን ተላልፋ ተሰጠች፤ በነገራችን ላይ ስናር በሃያ ስድስት ‹‹ኮርድኔት›› የተከፋፈለች ስትሆን፣ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ይዞታ ሊባል የሚችለው ‹‹ኮርድኔት 24›› በተሰኘው ውስጥ ባለፈው ዓመት ህይወታቸው ያለፈውና በርካታ
ታጣቂዎችን ማስከተሉ የሰመረላቸው ባሻ ጥበቡ እና አስመሮም መኮንን የተባሉ ግለሰቦች ለሱዳናውያን ሳያስረክቡ፣ በራሳቸው ኃይል ተገዳድረው ያቆዩት መሬት ነው፡፡ በተቀረ በአካባቢው የምናገኛቸው ኢትዮጵያውያን ከሱዳናውያን ላይ በአረብኛና እንግሊዘኛ በተፃፈ ውል በተከራዩት መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡
ታጣቂዎችን ማስከተሉ የሰመረላቸው ባሻ ጥበቡ እና አስመሮም መኮንን የተባሉ ግለሰቦች ለሱዳናውያን ሳያስረክቡ፣ በራሳቸው ኃይል ተገዳድረው ያቆዩት መሬት ነው፡፡ በተቀረ በአካባቢው የምናገኛቸው ኢትዮጵያውያን ከሱዳናውያን ላይ በአረብኛና እንግሊዘኛ በተፃፈ ውል በተከራዩት መሬት ላይ ብቻ ነው፡፡
በአናቱም በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ሊሰጡ ነው እየተባለ የሚነገረው እንደ መተማ-ዮሀንስ፣ ዳፋ፣ ሽመል ጋራ፣ ፎርኹመር፣ አብዱራፊ፣ ነፍስ ገብያ፣ አለቃሽ (በረሃማ አካባቢ ነው)… የመሳሰሉ ከተሞች ስማቸው ተደጋግሞ በመነሳቱ፣ አካባቢውን ውጥረት ውስጥ ከትቶታል፡፡ በርግጥም ከአገዛዙ ያደረ ታሪክ አኳያ መሬቶቹን አይሰጥም ተብሎ አይታሰብም፤ በተለይም ጉዳዩን ለጥጠን የሰሜን አፍሪካ አብዮት በፈጠረበት ስጋት፣ በድንገቴ ውሳኔ እየገነባ ካለው የ‹‹ህዳሴ ግድብ›› ጋር አነፃፅረን ካየነው፣ የሱዳንን ድጋፍ ለማግኘት መሬቶቹን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል ወደሚል ጠርዝ እንገፋለን፡፡ …ግና! ይህ አይነቱ ኢህአዲጋዊ ድፍረት ‹‹አባትየው ቢሞት የለም ወይ ልጅየው?›› በሚል ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ዛሬ ‹‹ተሰጡ›› ወይም ‹‹ሊሰጡ›› ነው ብለን የምንጫጫባቸው መሬቶች‹‹የይገባኛል›› ጥያቄ ያልቀረበባቸው በመሆኑ፣ ኦቦ ሌንጮ ለታ ‹በባሌ ሲጠብቁን፣ በቦሌ ገባን› እንዲል፣ ስርዓቱ ሆነ ብሎ ከእውነታውአርቆ ለማደናገር የሚጠቀምባቸው አጀንዳዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ መጠርጠሩ አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ በርግጥም ጉራማይሌ ፖለቲካ ማለት ይህ ነው፡፡
ሌላው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ኢህአዴግ በእነዚህ አካባቢዎች እያደረገ ያለው የሚከተለው መሆኑ ነው፡- ከኩሊት እስከ ቋራ ድንበር ድረስ ከወሎ፣ ከጎጃም እና ከጎንደር ነዋሪዎች አሰባስቦ የመልሶ ማስፈር ስራ ሰርቷል፤ የሰፈራው ዋነኛ አላማም ለም መሬት ይዘው እያረሱ ቤተሰብ መስርተው እንዲቀመጡ ያማቻቸላቸውን ሰፋሪዎች መሳሪያ በማስታጠቅ በአካባቢው በኩል ሊመጡ የሚችሉ የኃይል አማራጭን የሚከተሉ ተቃዋሚዎችን እንዲከላከሉ እና ከአቅማቸው በላይ ሲሆን ደግሞ አስቀድመው መሬት ለሰጣቸው መንግስት እንዲያሳውቁ ማድረግን ያሰላ ነው፡፡ በዚህም ለሥልጣኑ አስጊ የሆነውን ቀዳዳ ለመድፈን እየሞከረ እንደሆነ መረዳት ይቻላል (በነገራችን ላይ ከጎንደር ተቆርሶ ለትግራይ መሬት ተሰጥቷል የሚል አደገኛ ቅስቀሳም እየተካሄደ ነው፤ በግሌ ይህ ጉዳይ የሚያወዛግብ አይመስለኝም፤ ስርዓቱ ያነበረውን ቋንቋ ተኮር ፌደራሊዝም የማንደግፈው እስከሆነ ድረስ መሬቱ ወደ የትኛውም የሀገሪቱ ክልል ቢሄድ ለውጥ አይኖረውም፤ ምክንያቱም በኢህአዴግ ግብዓተ-መሬት ላይ የሚያብበው መልከዓ-ምድራዊ ፌደራሊዝም (Geographical Federalism) እነዚህን አጨቃጫቂ መሬቶች ለአስተዳደር አመች በሆነ መልኩ ማዋቀሩ አይቀሬ ነውና)
አያሌው ጎበዜና ባሕር ዳር
አቶ አያሌው ጎበዜ ድርጅቱን የተቀላቀለው አስተማሪ ሆኖ እየሰራ በነበረበት አዲስ ዘመን ከተማ በ1984 ዓ.ም ቢሆንም በተፋጠነ ሂደት የሽግግር መንግስቱ የስራ አስፈፃሚ አባል መሆን ችሎ ነበር፤ ከ1987-1992 ዓ.ም የክልሉ አስተዳዳሪ አዲሱ ለገሰ ምክትል ሆኖ ተሹሟል፤ በዮሴፍ ረታ የአስተዳደር ዘመን (ከ1992-97 ዓ.ም) ደግሞ መጀመሪያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ኃላፊ፣ ቀጥሎ አፈ-ጉባኤ ሆኖ ሰርቷል፡፡
ይሁንና በምርጫ 97 ዮሴፍ በተወዳደረበት ሰሜን ሸዋ በቅንጅት እጩ ሲሸነፍ፣ አያሌው ደግሞ በማርቆስ ከተማ በባሶ ሊበን ወረዳ ሊያሸንፍ ችሏል (አሸናፊነቱ ምንም እንኳ እንደ ሌሎቹ የኢህአዴግ ተወዳዳሪዎች በድርጅታዊ የድምፅ ስርቆት የተገኘ ቢሆንም) ከ1998 ዓ.ም አንስቶ እስከያዝነው አመት መጀመሪያ ወራት ድረስ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆኖ የቆየው አያሌው ጎበዜ ‹‹ለሱዳን ተሰጠ›› ወይም ‹‹ሊሰጥ ነው›› ከተባለ መሬት ጋር ተያይዞ የማጀገኑና የማንፃቱ ቅስቀሳ የኑፋቄን መንገድ የተከተለ ይመስለኛል (የጉዳዩ ስሁትነት የኛይቷን ‹ፋክት› መፅሄትንም ይጨምራል) በደፈናው ከዚህ ቀደም ‹አያሌው ለሱዳን በሚሰጥ መሬት ላይ አልፈርምም በማለቱ፣ ደመቀ መኮንን ፈረመ› የሚባል ምንጩ የማይታወቅ ወሬ ሁላችንም ጋ ደርሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከብአዴን የመረጃ ምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት፣ አያሌው ያውም ርህራሄ አልባ የነበረውን የጉልበታሙ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ውሳኔ ተቃውሞ ‹ፈርም›፣ ‹አልፈርምም› አይነት አንጃ ግራንጃ የሚፈጥር ደፋር ልብ ያሌለው መሆኑን ነው፡፡ በግልባጩ ፖለቲካችን ጉራማይሌ ነውና ለብአዴን ፍቅር በሌላት ባሕር ዳር አያሌው ተወዳጅ እንደሆነ ይነገራል፤ ይህ የተወዳጅነቱ ሚስጥር ግን ከድርጅቱ ይልቅ ‹‹መረጠኝ›› ለሚለው ሕዝብ ታማኝ በመሆኑ እና በሀገር ጥቅም ከእነ ‹ኦቦ› አዲሱ ለገሰ ተሽሎ ሳይሆን፣ ከራሱ የግል ባህሪና ሰብዕና ጋር ስለሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ካሉ ነዋሪዎች እና አብረውት ከሚሰሩ የበታች ሰራተኞች ጋር የመሰረተው ማሕበራዊ ግንኙነት ዋነኛው ነው፤ በርግጥም የሚያውቀውም ሆነ የማያውቀው ሰው ሲሞት ቀብር ላይ ይገኛል፤ ማታም እዝን ይዞ በመሄድ ሲያፅናና ያመሻል፤ ሰርግን በመሳሰሉ የደስታ ዝግጅቶችም ላይ እንዲሁ ይሳተፋል፤ እነበረከት ስምዖን ለሚያቀነቅኑት ግራ ዘመም ፖለቲካም ሩቅ በመሆኑ፣ እጅግ መንፈሳዊ የሆነ ባህሪይ ይስተዋልበታል፤ ለአብነት እምነቱ የሚያዝዘውን (ከመፆም ጀምሮ በቤተ-ክርስቲያን ተገኝቶ እስከ ማስቀደስ ያሉ ጉዳዮችን) እንደ ባለሥልጣን ግብዝ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ተራ አማኝ ዕለት ተዕለት ሲፈፅም ይታያል፡፡ በቤተሰብ አስተዳደርም ቢሆን አራት ልጆቹን መንግስት ትምህርት ቤት ከማስተማር አልፎ በኢትዮጵያዊ ጨዋ ስነ-ምግባር ማሳደጉን፣ ብልሹ አድርገው ልጆቻቸውን እያሳደጉ ካሉ ከአንዳንድ ኃላፊነት ከማይሰማቸው ባለሥልጣናት ጋር አነፃፅረው የሚያመሰግኑት የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አጋጥመውኛል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በህክምና በማዕረግ የተመረቀችውን ብቸኛና የመጀመሪያ ሴት ልጁንም እንደ ምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡
በአናቱም የትኛውም ባለ ጉዳይ ቢሮው ሲመጣ ያለ ቢሮክራሲ ማስተናገዱም ሆነ ለሚቀርብለት አቤቱታም ጥያቄ ‹አይሆንም› አለማለቱን እንደ በጎ ተግባር የቆጠሩለት ሰዎች ለሰውየው ገፅታ ግንባታ የራሳቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተቀረ ኢህአዴግ እንደ አሰባሰባቸው በርካታ ባለስልጣናት እርሱም አለቆቹን አብዝቶ የሚፈራ ሽቁጥቁጥ ሰው መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በተለይም የብአዴን ካድሬዎች ‹‹ሽማግሌው›› እያሉ በሹክሹክታ የሚጠሩትን አዲሱ ለገሰን እና ሞገደኛውን በረከት ስምዖንን የ‹መለአኩ ገብርኤል› ያህል እንደሚፈራቸው ሰምቻለሁ፡፡
ይህ ፍራቻውም በፍትሕ እና በሙስና ቢሮዎች አካባቢ ከብቃት ይልቅ ‹‹የራሴ›› የሚላቸውን የትውልድ መንደሩን ሰዎች በመሾሙ ‹‹እመራዋለሁ›› የሚለውን ሕዝብ ለከፋ ብሶትና መከራ አጋልጦ ነው ከሥልጣኑ የተሰናበተው፡፡ ይህም ሆኖ ከኃላፊነቱ ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረበ ከአንድ አመት በኋላ ነው ፓርቲው ያፃደቀለት፤ ያለፈውን ሙሉ ዓመትም በቢሮው ከመገኘቱ እና በትላልቅ ጉዳዮች ላይ ከመሳተፉ ባለፈ፣ ሁሉንም ሥራ ሲሰራ የነበረው ዛሬ በምትኩ የተሾመው የዋድላ ደላንታው ገዱ አንዳርጋቸው ነው፤ ገዱ ድርጅቱን የተቀላቀለው ከአያሌው አንድ ዓመት ቀደም ብሎ ዋድላ ደላንታን ኢህአዴግ ከደርግ መዳፍ በኃይል ነጥቆ በወሰደበት ወቅት ነበር፤ ያን ጊዜ የገበሬ ማሕበር ሕብረት ሱቅ ሠራተኛ የነበረው ገዱ ዛሬ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለመሆን ችሏል፤ በርግጥ ይህ ሰው ጠንካራ ሠራተኛ እና የበላይአመራሮችን ተጋፋጭ እንደሆነ ይነገርለታል፤ እንዲሁም እንደ አያሌው ከሙስና ጋር ብዙም ንክኪ የለውም (በነገራችን ላይ የብአዴን ዋነኛአመራሮች ለሙስና ሩቅ እንደሆኑ በወሬ ደረጃ ይሰማል፤ ግና! ይህንን እንደምን ማመን ይቻላል? …በርግጥ በክልሉ በተዘዋዋሪ መንገድ የጀነራል አበባው ታደሰ ነው ከሚባለው ባለ አራት ፎቁ ‹‹አልዋቅ›› ሆቴል ሌላ በወሬ ደረጃ የአመራር አባላቱ ንብረት የሆነ አላጋጠመኝም፤ ነገር ግን እኔን አላጋጠመኝም ማለት ሰዎቹ ንፁሃን ናቸው እንደ ማለት አይደለም)
አቶ በረከት እና አዲሱ
የሆነው ሆኖ ብአዴን በበረከት ስምዖን፣ በአዲሱ ለገሰ፣ በካሳ ተክለብርሃን፣ በታደሰ ጥንቅሹ እና በከበደ ጫኔ ስም የመሰረተው ‹‹ጥረት›› የተሰኘው ኮርፕሬሽን ዳሽን ቢራ፣ ጥቁር አባይ ትራንስፖርት፣ ዘለቀ እርሻ፣ አምባሰል አስመጪና ላኪ፣ ጣና ሞባይል እና ጣና ፍሎራ የተሰኙ የንግድ ድርጅቶችን ያስተዳድራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አትራፊ የሚባለው ዳሽን 49 ፐርሰንቱን እንግሊዝ አገር ለሚገኝ አንድ ቢራ አምራች ድርጅት ሲሸጥ፤ ጣና ሞባይልም በአሜሪካን ሀገር የታወቀው የሶፍት ዌር ኢንጂነር ባለሙያው ወልደሉዑል ካሳን ጨምሮ ለአራት ሰዎች የአክሲዮን ድርሻን አስተላልፏል፡፡ ይህ ሁኔታም ድርጅቶቹ ትርፍና ኪሳራቸውን በውጪ ኦዲተር እንዲያስመረምሩ የሚያስገድድ መደላድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ በርግጥም እንዲህ አይነቱ አሰራር የእነ አዜብ መስፍን መቀለጃ ከሆነው ‹‹ኤፈርት›› በተሻለ መልኩ ለዘረፋ እንዳይጋለጥ መታደጉ አከራካሪ አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንግሊዛዊው ድርጅት የዳሽን ቢራ 49 ፐርሰንት ድርሻን ገዝቶ ሲያበቃ፣ ወጪና ገቢውን አይከታተልም ማለቱ ሩቅ ነውና፡፡
በትግራይ ሕዝብ ስም እየነገደ፣ ለህወሓት አመራር አባላትና ቤተሰቦች ብቻ መምነሽነሺያ የሆነው ‹‹ኤፈርት››ም በእንዲህ አይነት መልኩ ለውጭ ድርጅቶች ድርሻ እንዲሸጥ ካልተገደደ በቀር ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ እውነታ ነው፤ ይህ ሁኔታም የፖለቲካ ሥልጣን የጨበጠ ሁሉ የቻለውን የሚዘግንለት ከመሆን የሚተርፍበትን እድል ያመቻችለታል (በነገራችን ላይ እንደሚወራው የብአዴን አመራሮች ወደ ሙስና አለመግባታቸው እውነት ከሆነ፣ ምክንያቱ ጠፍጥፎ የሰራቸውን ህወሓት በመፍራት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በግልባጩ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የሚፈራው የለምና እንዲህ እንደቀለደ በሚቀጥለው ወር የተመሰረተበትን 39 ዓመት ለማክበር ሽር-ጉዱን ከወዲሁ ተያይዞታል)
ሌላው የብአዴን አመራሮች አስገራሚ ታሪክ ከዋነኞቹ መካከል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ሕላዊ ዮሴፍን… የመሳሰሉት የትዳር አጋራቸውን ያጩላቸው አንዲት ሴት መሆናቸው ነው፡፡ እኚህ የዋግ ኡምራ ተወላጅ በታጋዮች ዘንድ ‹‹ማዘር›› እየተባሉ ሲጠሩ፣ ኢህአዴግ ውስጥ ባሉ አንዳንድ አሽሟጣጮች ደግሞ ‹‹ጣይቱ›› በሚል ቅፅል ስም ይታወቃሉ፤ ይህ ስያሜ የአጼ ምንሊክ ባለቤት የነበሩት እቴጌ ጣይቱ ታላላቅ መኳንቶችን እየመረጡ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ጋር ያጋቡ ነበር ከሚለው ትርክት የሚነሳ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ኩነት ጉራማይሌ የሚያደርገው የ1993ቱን የህወሓት ክፍፍል ተከትሎ የብአዴን መሪዎች ‹‹ቦና-ፓርቲዝም››ን በአደባባይ ሲያወግዙና ሲተቹ መስማታችን ነው፡፡
(ቀሪውን ጉራማይሌ የፖለቲካ ወጋችንን በሚቀጥለው ሳምንት እመለስበታለሁ)
ከ ዘ -ሐበሻ የተወሰደ
No comments:
Post a Comment