Sunday, February 9, 2014

አረናዎችን ለመገድል ህወሃት እያሴረ ነዉ ተባለ

February 9/2014

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለመዋሃድ ንግግር እያደረገ ያለው የአረና ፓርቲ፣ ከሕወሃት ጋር ከፍተኛ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ ላይ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ነዉ። በቅርቡ በአዲግራት ሊደረግ ታስቦ በነበረዉ ሕዝባዊ ስብስባ ከሌላ አኡራጃዎች የመጡ የሕወሃት ካድሬዎችና ዱርዬዉን ድንጋይ እየወረወሪ ሲበጠብጡ፣ የአመራር አባላትን ሲደበድቡ እንደነበረ የሚታወስ ነዉ። ህወሃት እነዚህ ዱርዮዎችን አሰማርቶ የሽብር ተግባራትን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ስብሰባዉን ማድረግ ካለመቻሉ የተነሳ፣ የአዲግራት ሕዝብ አማራጮችን እንዳይሰማ ተደርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በሁመራ ሕወሃት በሕግ ተፈቅዶ የተጠራን የአረና ስብሰባ በኋይል ለማጨናገድ ችሏል። አረናዎች ሳይታክቱ በየከተሞቹ የሚያደርጉት ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በሌላ ብኩል ደግሞ ህወሃት እያሳያቸው ያለው ፍጹም ጸረ-ሰለማ እና ጸረ-ዲሞርካሲ ተግብራት አብዛኛዉን የህወሃት ደጋፊ የነበሩትን ሁሉ እያስገረመና እያስቆጣ ሲሆን፣ በርካታ ሕወሃቶች ወደ አረና እየተጎረፉ እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ከዚህም የተነሳ ሕወሃት የአረናን ግለት መግታት ስላልቻሉ የአመራር አባላቱን የመግደል ሴራ አያሴሩ መሆናቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየተነበቡ ናቸው።
የአረና ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አብርሃ ደሳታ በዚህ ጉዳይ ላይ በፌስቡክ የጻፉትን እንደሚከተለዉ አቅርበናል፡
=========================
ሑመራ (ዳንሻ) በነበርኩበት ግዜ ከተወሰኑ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ሁለት ታጋዮችን የነገሩኝ ላካፍላቹ። “ለምንድነው የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው?” አንድ ጓደኛዬ የጠየቀው ነበር። ታጋይ አንድ (ወንድ ነው) ሲመልስ “የትግራይን ህዝብ ፈሪ የሆነው ከድሮ ጀምሮ የህወሓትን ጭካኔ ስለሚያውቅ ነው። ህወሓት ሰው በሊታ መሆኗ የትግራይ ህዝብ በደንብ ያውቃል” አለ። “እሺ የትግራይ ህዝብስ ይፍራ እናንተ ታጋዮችስ ለምን ትፈራላቹ?” ብዬ ጠየቅኩ። ታጋይ ሁለት (ሴት ናት) “እኛ ታጋዮችምኮ የህወሓትን ጭካኔ በደንብ እንረዳለን። ከህዝብ በላይ ህወሓትን የምናውቃት እኛ ነን። አብዛኞቹ የህወሓት ታጋዮችኮ በህወሓት የተረሸኑ ናቸው። በደርግ ከተገደሉብን ብፆት (ጓዶች) በራሷ በህወሓት የተገደሉ ይበዛሉ። በህወሓት እንደተረሸኑ እያወቅንም ‘በጦርነት ተሰውተዋል’ ብለን ነው የምንናገረው። አብዛኞቻችን እናውቀዋለን። ግን እንፈራለን። አሁን ግን ማንን እንደምንፈራ አላውቅም” አለች። “ፍርሓት ፍርሓት … መጨረሻ ድፍረት ይሆናል” ብዬ ተሰናበትኳቸው።
የህወሓት መሪዎች ተስፋ ከመቁረጣቸው የተነሳ የዓረናን መሪዎች እስከመግደል ሊደርሱ እንደሚችሉ አንድ የህወሓት የደህንነት ሐላፊ ዛሬ አጫውቶኛል። ተስፋ የቆረጡበት ምክንያት … የራሳቸው (የህወሓት) አባላትም ዓረናዎች የሚያነሷቸው ሐሳቦች እያነሱ ስለሚጠይቁና በብዛት ከህወሓት አባልነት እየለቀቁ በመሆናቸው ነው። ባሁኑ ግዜ በትግራይ ክልል የሚገኙ የህወሓት አመራር አባላት በየዞኗቸው ተሰብሰበው የሚገኙ ሲሆን ከሚያነሷቸው ሐሳቦች በመነሳት የህወሓት መሪዎች በአባሎቻቸውም እምነት የላቸውም። እስካሁን ድረስ በሰሩት ወንጀል ምክንያት ተጨናንቀዋል። (ሁሉም አመራር አባላት በየዞን ከተሞች የተሰበሰቡ ሲሆን የተምቤኖች ግን ለየት ይላል። ተምቤኖች ጠንከር ያለ ተቃውሞ ያነሳሉ በሚል ስጋት ለብቻቸው በዓድዋ ከተማ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል። ሌሎች የማእከላዊ ዞን አባላት ግን በአክሱም ይገኛሉ)። የህወሓት የ አባላት ለስብሰባ ሲገቡ ሞባይላቸው እንዲዘጉ በጥብቅ ይታዘዛሉ። የመሪዎች ንግ ግር መቅረፅ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ህወሓት እንኳንስ ህዝብ የራሱ አባላትም አይመርጡትም። የሰሩት ወንጀል ራስ ምታት ሁኖባቸዋል። ስልጣን መልቀቅ የሞትን ያህል አስፈርቷቸዋል። በዚሁ አካሄዳቸው ደግሞ በስልጣን ሊቆዩ እንደማይችሉ በሚገባ ተረድተዋል።
ህወሓት ፍፁም አምባገነንነቱን እያጠናከረ ነው። ትናንት ዓርብ በሑመራ ከተማ ሰዓት እላፊ ማወጁ ይታወሳል። በዓረና እንቅስቃሴ በጣም የሰጋ ህወሓት ዛሬ የዓረና አባላትን ሲያስፈራራ ዉሏል። አቶ መሰለ ገብረሚካኤል የተባሉ የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና አባላት አስተባባሪ ዛሬ ታስረው እየተገረፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የዓረና ፓርቲ ቢሮ (በሑመራ) በህወሓት ካድሬዎች ዛሬ ተዘርፏል፤ ኮምፒተሮች ተወስደዋል (የአቶ መሰለ የግል ላፕቶፕም ጭምር በባለስልጣናቱ ተዘርፋለች)። የመንግስት ስልጣን የያዘ አካል እንዲህ የተራ ሽፍታ ስራ ሲሰራ ይደንቃል። ለአምባገነናዊ ስርዓት አንምበረከክም። ማሸነፋችን አይቀርም።

No comments:

Post a Comment