Wednesday, January 22, 2014

በቂልንጦ ታስረው ሚገኙት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ሶላት መከልከላቸውና በጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ላይ ድብደባ እንደተፈፀመበት ታወቀ፡፡

January22/2014

በቂልንጦ ማረሚያ ቤት ዞን ሁለት ውስ ታስረው የሚገኙ እስረኞች መካከል በተነሳ ፀብ ምክኒያት በአንድ ታሳሪ ላይ ድብደባ እንደተፈፀመበት የታወቀ ሲሆን ይህን ግለሰብ ያስደበደባችሁት እናንተ ናችሁ በማለት በዞን ሁለት ውስጥ የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴዎችና ሌሎች ወንድሞች የመግሪብ የኢሻና የሱብሂ ሶላት እንዳይሰግዱ ተከልክለዋል፡፡
በዞን ሁለት ውስጥ ኡስታዝ ባህሩ ኡመር ኡስታዝ ሰኢድ አሊ ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው አርቲስት ሙኒር ሁሴን የሚገኙ ሲሆን ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው የእምነት ትዛዛችንን መፈፀም ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው ብሎ በመጠየቁ ለብቻ ተወሰዶ ድብደባ እንደተፈፀመበት ለማወቅ ተችልዋል፡፡ በህግ ጥላ ስር የሚገኙ ታሳሪዎች ተገቢውን ጥበቃና ሰብአዊ ህገ መንግስታዊ መብታቸው መከበር እንዳለበት ህገ ቢደነግግም ይህን መብታቸውን በመጣስ ወከባና ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደ ሆን የቢቢኤን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም በድርድር ለየብቻችሁ ስገዱ የተባሉ ሲሆን በጋራም የመስገድ መብት አለን በማለት የሱፍ ጌታቸውም ሌሎቹም በጋራ እየጠየቁ እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመከላከያ ምስክርነት ቀናት በተቃረቡበት ጊዜ መሰል እርምጃዎችን መወሰዳቸው የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየስ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡም አሉ፡፡ በነዚህ የህዝበ ወኪሎች ላይ የሚፈፀሙ የህግ ጥሰቶች በመላው ህዝበ ሙስሊም ላይ የሚፈፀሙ ናቸውና መንግስትን ለጉዳይ ትኩረት በመስጠት እርምት ማድረግ አለበት ሲሉ የቢቢኤን ምንጮች አክለው ገልፀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment