Thursday, January 30, 2014

አሳሳቢዉ የስነ- ምግባር ጉድለት

January 30/2014

ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባብተዉና ተዋህደዉ በስርዓት የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን በዓለማችን እየታየ ያለዉ ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ይዞት የቆየዉን እምነቱን እና ባህሉን እየተፈታተኑት ነዉ ተብሎአል።
Symbolbild Prostitution
ባለፈዉ ሰምወን «ስነ- ምግባር ለእድገት መሰረት ነዉ» በሚል ርዕስ፤ በአዲስ አበባ የትምህርት ቢሮ፤ የኢትዮጵያ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ ቡድን አዲስ አበባን ጨምሮ ሰፋፊ በሚባሉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ፤ ከአንደኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ- ምግባር ጉድለቶች መጋለጣቸዉን በጥናት በተደገፈ መረጃ ይፋ አድርጎዋል። ቡድኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮችን ጠርቶ ለሁለት ቀናት ባደረገዉ ዉይይት፤ ታዳጊ ወጣቶች በተለይ በከተሞች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ ባሉ ህገ-ወጥ የአልኮል፤ የአደንዛዥ እጽ
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
መጠቀሚያና፤ የወሲብ ፊልሞች ማሳያ ቤቶች በመበራከታቸዉ፤ ለችግሩ መጋለጣቸዉን አፅንዖት ሰጥተዉ ተናግረዋል። ዓለማችን እያስተናገደችዉ ያለችዉ ፈጣን ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ከትዉልድ ትዉልድ ይዞት የቆየዉን ትዉፊትና ስነ- ምግባሩን ወደ አልሆነ አቅጣጫ ሊወስደዉ ይገባልን? የዕለቱ የባህል መድረካችን የሚቃኘዉ ርዕሱ ነዉ ።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባብተዉና ተዋህደዉ በስርዓት የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን በዓለማችን እየታየ ያለዉ ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ይዞት የቆየዉን እምነቱን እና ባህሉን እየተፈታተኑት ነዉ ይላል፤ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ ቡድን አዲስ አበባ ላይ ባወጣዉ የስብሰባ ጥሪ። በስብሰባዉ ላይ በአሁኑ ወቅት ከተማ ያሉ አንዳንድ ወጣቶች ለአልኮል ለጫት እና ለልቅ ወሲብ መጋለጣቸዉን በጥናት የተደገፈ ፅሁፋቸዉን ያቀረቡት መምህርት ጽዮን አክሊሉ፤ በተለይ በዚህ ችግር ላይ ያሉት የገንዘብ አቅምና የተማሩ ቤተሰቦች አሉዋቸዉ የሚባሉ ታዳጊ ወጣቶች እንደሆኑ ተናግረዉናል።
መምህርት ጽዮን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና ከዓለም የጤና ድርጅት ምርምር ተነስተዉ ያቀረቡት የጥናት ጽሁፍ እንደሚያመለክተዉ የታዳጊ ህጻናት ስነ-ምግባር እጅግ እየተበላሸ እንደሆነ ይናገራሉ። ከሀገራዊ ስነ-ምግባር ጋር በተገናኘ በዉይይት መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት አባ በአማን ግሩም እንደሚሉት በቴክኖሎጂ ዓለም እጅግ በጠበበችበት በአሁኑ ወቅት፤ በተለያየ የስራ ዘርፍና የእድሜ ክልል፤ የሀገርን ገፅታ የሚያበላሽ የስነ-ምግባር ጉድለቶች እየታዩ ነዉ።
በእዚህም ይላሉ አባ በአማን በመቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ይህ ሀገራችን ላይ የሚታየዉን አስከፊ የሆነዉን የስነ ምግባር ወረርሽኝ ሊያወግዙና ትምህርት ሊሰጡበት ይገባል። የግብርና ባለሞያ የሆኑትና «ስነ- ምግባር ለእድገት መሰረት ነዉ» በተሰኘዉ የዉይይት መድረክ ላይ የጥናት ፅሁፋቸዉን ያቀረቡት ሌላዉ የመድረኩ ተሳታፊ፤ አቶ ንጉሴ ዘዉዴ፤ በሀገራችን ታዳጊ ወጣቶች ዘንድ የሚታየዉ ፈር የለቀቀ ስነ-ምግባር ካልታረመ ሀገር ተረካቢ ትዉልድ እናጣለን የሚል ስጋት አለኝ ሲሉ ገልፀዉልናል።
የኢትዮጵያ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ደብርነህ በበኩላቸዉ መጤ ልማዶችን ለማስቀረት ሁሉም የማህበረሰብ አካል የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል።
Afrika Simbabwe Prostitution
የኢትዮጵያ የሰላም፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ በሁለት ቀኑ ስብሰባ ላይ ፤ በሃገራችን በተለይ በከተሞች አካባቢ በአንዳንድ ወጣቶች ዘንድ የሚታየዉ የስነ-ምግባር ጉድለት እና የማህበረሰባዊ እሴትች ዉድቀት፤ የሕግ ክፍተት መኖሩ አንዱ እንደሆነ እና የመንግሥት መገናኛ አውታሮችን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለህዝብ የሚተላለፉ የማስታወቂያ መልዕክቶች፤ የቃላት አመራረጥ ላይ ጥንቃቁ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጾዋል። በሌላ በኩል ለአንባቢ የሚደርሱ ስነ-ምግባር የጎደላቸዉ ፅሁፎች፤ ህዝብ አይን ላይ ከመድረሳቸዉ በፊት አራሚ ሊቃኛቸዉ እንደሚገባና፤ በዚህ ረገድ መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ ትኩረት እንዲሰጥ ያሉንን ፤ የዕለቱን እንግዶቻችን ለሰጡን ቃለምልልስ እናመሰግናለን። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ መጫኛዉን በመንካት ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC


No comments:

Post a Comment