January 25/2014
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የአረና ፓርቲ አባል በመሆን የትግራይ ወጣቶችን በመቀስቀስ የወያኔ አገዛዝን በመቃወም የሚታወቀው አብረሃ ደስታ በትልላንትናው እለት በትግራይ አካባቢ መደብደቡን ተገለጸ ፣ይህንን ግለሰብ እና ሌሎች የአረና አመራር አባላትን ጨምሮ እንዲሁም ሌሎች በስብሰባው ላይ የተገኙትንም የህብረተሰብ አካላት የመንግስት ባለስልጣኖች በተገኙበት በታጣቂዎች መደብደባቸው ተገልጾአል ። ከ18 ሰአታት በፊት አቶ አብረሃ ደስታ ለመላው የግል ሚዲያዎች አጭር መል እክት እንዲህ ሲል አስተላልፎ ነበር ዓረና ፓርቲ በዓዲግራት ከተማ ለእሁድ ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ጋር በተያያዘ ዛሬ ዓርብ ሁለት የዓረና አመራር አባላት (አቶ ዓምዶምና መምህር ገብረጨርቆስ) በዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ፖሊስ ታስረዋል። የታሰሩበት ምክንያት ህዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ህወሓቶች በተምቤን የፈሩትን ያህል በዓጋመ ፈርተዋል። በተምቤን ተመሳሳይ የእስር ሁኔታ አጋጥሞናል። ስብሰባ ፈቅደው ስለ ስብሰባው ህዝብ እንዳይሰማ ግን ከለከሉ። የዚህ የዜና ስራ ተጠናክሮ ሳይወጣ እንደገና የእርሱ መደብደብ ዜና ደርሶናል ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅጣጫ ወዴት እያዘመመ እንድሆነ ከእንስቃሴው ለመረዳት ይቻላል።

No comments:
Post a Comment