Wednesday, December 4, 2013

ማምሻውን በሹክሹክታ የደረሰኝ ብርቱ መረጃ !

December 4/2013

ነቢዩ ሲራክ ke Saudi Arabia
መልዕክቱን አስቀድሜ ዝርዝሩን ላስቀጥል ልቤ ፈቀደ ! ሹክሹክታው የመልዕክቱ አደራረስ እንጅ መልዕክቱ የተጨበጠ እውነት ነው እናም ስሙኝ ... !
ይድረስ ለወገኖቸ ... ህጋዊ መኖርያ ሰንድ ስሌላችሁ ወደ መጠለያ ለመግባት ፈልጋችሁ እስካሁን እድሉን ያላገኛችሁ ወገኖቸ ሆይ! እነሆ ተራችሁ ደርሷል ! በተለምዶ ፖሊስ ለማያዝ ሰው በሚሰባሰብበት በሸረፍያ ድልድይ ስር በመሄድ እዚያው ብትሰባሰቡ በሁለት ቀናት ውስጥ አውቶቡስ እየመጣ ወደ ሽሜሲ መጠለያ እንደሚወስዳችሁ ከአንድ ብርቱ ውስጥ አዋቂ ወዳጀ በሹክሹክታ መረጃ ደርሶኛል! ሽሜሲ እንደደረሳችሁ ወደ መጠለያው ሳትገቡ አሻራ በማድረግ በአንድ ቀን ልዩነት ወደ ሃገር ቤት የምትገቡበት መንገድ መዘርጋቱንና ይህንንም ለማሳለጥ የመጠለያው ሃላፊዎች ፣ የፖስፖርት ክፍል (የጀዋዛት) ሃላፊዎችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ከጅዳ ቆንስል ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር መክረው ዘክረው ውሳኔ መተላለፉ ብርቱ መረጃ ከብርቱው ውስጥ አዋቂ ወዳጀ መረጃው ማምሻውን በስልክ አቀብሎኛል !
መረጃውን ያቀበለኝን አረብ ወዳጀ ለተጠቀሱት መረጃዎች ቅርብ ነው ። እናም መረጃውን አቀብሎኝ ሲጨርስ በራሴ ላይ የሚጉላላውን ጥያቄ አነሳሁና ... ለምን ነዋሪው በጅዳ ቆንስል ተሰብስቦ እንዲሄድ አይደረግም? ስል ጠየቅኩት " እሱን እርሳው! በአካባቢው የኢትዮጵያ ቆንስልን ጨምሮ የተለያዩ ዲፕሎማሲ መስሪያ ቤቶችን በአካባቢው ይገኘኛሉ ። ትልቁ የንጉስ ፉሃድ ሆስፒታል ትምህርት ቤቶችና በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በቆንስላችሁ አካባቢ ምንም እንቅስቃሴ ሊኖር አይፈቀድም! አሁን መውጣት ለሚፈልጉ ብቸኛው አማራጭ ሸረፍያ ብቻ ነው ። እዚያ በመሔድ የአካባቢውን ጸጥታ ሳይረብሹ በረጋ መንፈስ መሰባሰብ ከቻሉ ቢበዛ በ24 ሰአት ውስጥ መሰባሰባቸው ሲታወቅ አውቶቡሶች መጥተው ይወስዷችኋል! አውቶቡስ ላይ እንዳሉ የመጓጓዣ ሰነድና አሻራ እንዲሰጡ ይደረጋል ! በመጡበት አውቶቡስ በመጠለያው ሳይውሉ ሳይድሩ በተዘጋጀው አውሮፕላን ወደ ሃገራቸው ይላካሉ ! ሌላው
የመጠለያ እንግልቱን ፈርተው በራሳቸው ቲኬት መሄድ ለሚፈልጉትም አሁን የሚፈሩት ችግር የለም ። ለቲኬት ገንዘብ አይክሰሩ ፣ ቲኬት በራሳችሁ ከሚቆርጡ ገንዘባቸውን ቆጥበው ሸረፍያ አውቶቡስ ሲመጣ ጠብቀው ተዘጋጅተው ከሄዱ በአንድ ቀን ሰንድ ተሰርቶላቸውና ቲኬት ተቆርጦላቸው ወደ ሃገር ቤት መግባት ይችላሉ ። ይህ ማለት ደግሞ ገንዘብ ቆጠቡ ማለት ነው! ግን በአየር መንገድ በቤተሰብ መሸኘት ከፈለጉ የራሳቸው ምርጫ ነው ። " ሲል የማይዋሸው ብርቱ ወዳጀ የሰጠኝ መረጃ ውሃ የሚያነሳ ምክር ጭምር ነው!
ጥያቄየን ቀጠልኩ ...ከሁለት ቀናት በፊት በአልጋ ወራሹ ልዑል ሰልማን በመሩት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ " ህገወጦችን በማስወጣቱ ረገድ እርምጃውነሰ አጠናክረን ፣ እንቀጥላለን " የሚለውን ጠንከር ያለ መግለጫ አነሳስቸ ፣ ብዙ ነዋሪዎች " ህጉ ይሻሻላል ፣ የምህረት አዋጁ ለአመት ተራዝሟል ! " በሚል ወደ ሃገር ቤት መግባትን አለመፈለግ እንደተጋጨብኝ አጫወትኩት ... ቀጠልኩና በዚህ ዙሪያስ ምን ትላለህ? ስል ወዳጀን የብዙዎቻችሁን ጥቃቄ ጠየቅኩት! ያማይዋሽ የማይቀጥፈው ፣ ብርቱው የመረጃ ምንጨ ፈገግ እንደማት ብሎ መለሰልኝ " ልብ ያለው ልብ ቢል ይሻላል ፣ ዘንድሮ አምናና ካች አምና አይደለም ፣ ሰአቱ ሳይልቅ በተከፈተው መንገድ የወጡ የታደሉ ነው የሚሆኑት! የምክር ቤቱን መግለጫ ሰምተሃል ፣ እኔም ውስጥ ውስጡን እየሆነ ያለውን ገላልጨ አልነግርህም ፣ ህገ ወጥ ሆኖ ፣ ያልተሟላ ሰነድ ይዞ እንደ ቀድሞው " ህግ ይሻሻላል፣ ምህረት አለ !" የሚለውን ተወው! አመነኝ! ያ ጊዜ አሁን አይደገምም!
ልብ ያለው ልብ ይበል ፣ ጓዙን ሸካክፎ ዛሬ በመጣው እድል ተጠቅሞ ወደ ሃገሩ በሰላም ቢገባ ይሻለዋል። ይህ ላልሆነና ተደብቄ ጊዜውን አለወፋለሁ ለሚል ፍርድ ነው! መቀጮውን ከፍሎ በእስር ማቅቆ እንደሚሄድ አትጠራጠር ! ይህ ብርቱ ህግ ነው ፣ ህጉን ለማስፈጸም መንግሰት ከፍተኛ ገንዘብ እያወጣ ነው ፣ ሁሉመ ሆኖ ያለወጣ ሰውዋጋውን ከፋይራሱ ነው የሚሆነው! " ሲል ቀርጥ አድርጎ የሚያውቀውን መረጃ አካፍሎኛል!
በሽሜሲ መካ መጠለያ እና በመዲና ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የጠየቁት በአብዛኛው በያዝነው ሳምንት ወደ ሃገር ቤት መሸኘታቸውን ተጨባጭ መረጃ ደረስኝ መባቻ ወዳጀ ውስጥ አዋቂው ያለኝን ሰምታችኋል። የጅዳ ከተማ ያሉ ወገኖች ተራውየእናንተ ነው ፣ ተዘጋጁ ፣ አማራጫችሁን እናንተው ታውቃላችሁ! ወገኖቸ ሆይ ! ጆሮ ያለው ይህን ሹክሹክታ ይስማ !
መረጃው እንደደረሰኝ ከአደጋ ጊዜ ከተቋቋመው ኮሚቴ አንዳንድ አባላት ጋር በሸረፍያ የሚሰበሰበው ነዋሪ ሊረዳ የሚችልበትን መንገድ ተወያይቻለሁ! ዝርዝሩን እና የምክክሩን መድረሻ እናዎጋለን! እስከዚያው ምከሩ ! አትውጡ እንዳልኳችሁ ውጡ ያልኩት ተጨበጭ መረጃን ይዠ እንደሁ ግን እመኑኝ !
የግርጌ ማስታዎሻ :
ወዳጆች ከላይ ሹክ ያልኳችሁን መረጃ የሚያጠናክሩ መረጃዎች ማምሻውን ለእኛ መንግስት ሃላፊዎች እና ለወገን ወገን ደራሽ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ባልደረቦች መድረሱን ሰምቻለሁ! እናም መረጃውን በሰፊው በማሰራጨት ግንዛቤ እንሰጥ ዘንድ እማጸናችኋለሁ ! እባካችሁ share "ሸር" በማድረግ እንደጋገፍ !
እስኪ እሱ ያቅናው !

No comments:

Post a Comment