Thursday, November 28, 2013

በኢትዮጵያ የአሳታሚዎች ቁጥር ለመቀነስ የጋዜጣ ህትመት ዋጋ ጨመረ

November 28/2013

በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ከሚገኙት የነጻው ፕሬስ አባላት ባገኘነው መረጃ መሰረት የህትመት ዋጋ ጭማሬ መንግስት በህትመት ላይ ያደረገ ሲሆን አሳታሚውችን እና ጋዜጠኞችን ለማመናመን ያደረገው ትልቁ ጥረት ነው ሲሉ ገልጸዋል ። እንደ ጋዜጠኞቹ አገላለጽ ከሆነ ከምርጫ 97 በኋላ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወረቀት ተወደደ እየተባለ የህትመት ውጤት የበለጠ እንዲወደድ በማድረግ አብዛኞቹን አሳታሚዎች ከአገልግሎት ውጭ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው ። ከዚህም በላይ ደግሞ የአሳታሚ ንግድ ፈቃድ ለማውጣትም ከፍተኛ ዋጋን ለማስያዣነት እንደሚጠየቅ የመገናኛ ብዙሃን ጉዞን በአጭሩ የሚያስቀር ሂደት ተያይዘውታል ሲሉ ገልጸዋል ። በአንድ ነጠላ መጽሄት 10 ብር ዋጋ ህትመት እናትማለን ብለው ማተሚያ ቤቶች ማሳወቃቸውን ጠቁመው አሳታሚዎች ለአከፋፋይ እና ለአዟሪዎች የሚከፈለውን ክፍያ ሲያወዳድሩት የሚሸጠው መጽሄት ትርፋማ ሊሆን እንደማይችል እና ህብረተሰቡም የመጽሄቱን ዋጋ ከ 13 እስከ 15 ብር ዋጋ ደፍሮ ሊገዛ የማይችልበት አቅም ላይ ስላለ አሳታሚዎች በኪሳራ ምክንያት ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ከስራ ውጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገልጸዋል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋዜጠኞች በማስፈራሪያ ዛቻ ላይ እንደሚገኙ እና ለህይወታቸው አስጊ በሆኑበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል ።በዚህ ሁለት እና ሶስት ወራት ብቻ ከሶስት ጊዜ በላይ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ ተብለው ሁለት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ጋዜጠኞች በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተው ታስረው በዋስትና እንደ ተለቀቁ እና ጉዳያቸው በፍርድቤት እንዳለ እና የፍርድ ቤት ቀጠሮአቸውን እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸዋል።
መንግስት በሚያመቸው መልኩ የፕሬሱን ጉዳይ እያንቀሳቀሰው ያለ ሲሆን ከዚህ በፊት የአቶ ክፍሌ ሙላት ይመራ የነበረውን የነጻ ፕሬሱን በሃይል የነጠቁት እና በእነ አቶ ወንደሰን እንዲመራ የአቶ በረከት ስምኦን አመራሮች የሰጡአቸውን እና በአሁን ሰአት የነጻው ፕሬስ ብለው የመሰረቱት ድርጅት በአባልነት ያልተመዘገቡትን እና ከወያኔ መንግስት በኩል ልንሰራ ሳይሆን ነጻ ሆነን ህዝብን ልናገለግል ይገባናል የሚልቱን ጋዜጠኞች ጥቃት እንዲፈጸምባቸው ማድረጋቸው አሳፋሪ እና ለነጻ ፕሬሱ አባላቶች ትልቅ ውርደት ነው ሲሉ ጠቁመዋል ።  

No comments:

Post a Comment